ልጥፎች

መሪነት፦ #ተጠናቆ #መፈጠርን ይጠይቃል።

 መሪነት #አቅም #መፍጠር ነው ታላቁ ተልዕኮው።  የፈጠረውን አቅምም በቅጡ ለመምራት የራሱን የምምራት #አቅም ፦ #ክህሎት ማሰልጠንም ይገባዋል።  ይህን አዋዶ ህዝብ ጠቀም ማድረግም ሌላው የመሪነት የጥበብ ዘይቤ ነው።  ሥርጉትሻ 2024/07/17   መሪነት፦ #ተጠናቆ #መፈጠርን ይጠይቃል። እንዴት ነው ሪኮመንድ የሚደረገው? እራስን #በመምረጥ ? የራሱን ከተንቆናጠጠ በኋላ ሌላውን እንደ ሥልጣን #ጥመኛ በማዬት? ለምን? ሌላው እኔ #እመጥናለሁ ወይ ተብሎም እራስ አይጠየቅም። #ፕሮቶኮሉንስ እችለዋለሁን ብሎ ማሰብም ይገባል። አሁን ጠቅላይ ሚር አብይ ንግሥናውን ሲመኙ #ፕሮቶኮሉን ጭራሽ አላሰቡበትም። ለዚህ ነው ብዙ ነገር #ልቅ የሆነው። ይህን የሚከታተል አካልም ያላቸው አይመስለኝም። #ሲነሪቲም አለ ሥርዓት ባለው መንግሥታዊ አወቃቀር። ይህን ጠሚር አብይ ልብ ያሉት ይመስለኛል። #ቀደምቶችን #ይሸኛሉ ። የሳቸውን ተሿሚወች መርጠው #እንዲያመልኳቸው ያደርጋሉ። አዲስ ነገር ፈጥረው። " #ፊልድ ማርሻል" እንደ ምሳሌ መውሰድ እንችላለን። ልቅና በልዕልና የነበራቸው ቀደምት የኢትዮጵያ ጀግና መኮንኖች መ እንኳን ያልተሰጣቸውን ነው የተከወነው። የሆነ ሆኖ መሪነትም እራስን፦ አቅምን እመጥናለሁ ወይ? ብሎ መጠዬቅን ይጠይቃል። ተያያዥ ጉዳዮችም። ሥርጉትሻ 2024/07/20     መሪነት #በችሮታ ወይንም #በይሉኝታ ወይንም #በቤተሰባዊ ትስስር ወይንም በማህበራዊ ኑሮ #ቅርበት እና #ርቅት አይቸረቸርም። መሪነት #በሥርዓት - ጥልቅነት፤ በሃሳብ - #ብሩህነት ፤ በተመክሮ - #ብቃት እና #ስኬት ፤ በማድመጥ እና በማደራጀት ልዩ #ስልታዊ አቅም፤ በችሎታ እና በሃሳብ ግልፅነት እና...

ልበልሽ ይሆን ውዳሴ? ይመቸዋል እና ለነፍሴ፨

ምስል
·        https://www.lora.ch/programm/alle-sendungen?list=Tsegaye ·        https://www.facebook.com/sergute.selassie/ https://sergute.blogspot.com/2021/02/blog-post.html?spref=tw

ፍትህ ፈላጊ ቅድሚያ #ለራሱ ፍትህ ይስጥ።

  ፍትህ ፈላጊ ቅድሚያ #ለራሱ ፍትህ ይስጥ።  ፍትህ ፈላጊ በቅድሚያ ለሚፈልገው የትግል #አቅጣጫ ፍትህ ይስጥ።  ፍትህ ፈላጊ ለሚያራምዳቸው #ሃሳቦች ፍትህ ይስጥ።  ፍትህ ፈላጊ የሌሎችን #የፍላጎት አቅጣጫም ያድምጥ።  ይህን ሳያደርግ ፍትህ #ጠማኝ መሆን አይችልም።  ምክንያት ፍትህ አሰጣጥ ከራስ ስለሚጀምር።  ሥርጉትሻ2024/07/19

#ስኬት የሰማይ #መና አይደለም።

ዕውነት ዬሕይወት #ውበት ነው።  ዕውነት ከህይወት ጋር ሲዋህድ ጠረኑ ለሰው ልጅ #ቅርብነት ነው። ዕውነት ሲኖር ቅርብ የሆነ የሰው ልጅ #ሽታ #በጣዕም ይከሰታል። ዕውነት ስለሰው ልጅ #ቅርፅ አይደለም። #እእ ።  የሰው ልጅ ሰብዕና የይዘቱ ፍልስፍና የዕውነት ውበት ነው።  ሥርጉትሻ2024/07/19   #ስኬት የሰማይ #መና አይደለም።  ስኬት የአመራር #ብቃት ውጤት ነው። #ልቅናም የአመራር ጥበብ ሥልጣኔ ከከፍተኛ እርከን ሲደርስ የሚገኝ ውጤት ነው።    #የአመራር #ብቃት + የአመራር ጥበብ #ልቅና = #የአመራር #ልዕልናን ብራንድን ይፈጥራል።  ይህ እንግዲህ ለታደሉት የሚሰጥ ፀጋ ነው። መማር ብቻውን ለዚህ የሚያበቃ አይመስለኝም።  የማስተዋል፤ የአትኩሮት፤ የማቀድ፦ የመረጋጋት ተመስጦ እና የመፈፀም ክህሎታዊ አቅምን ይጠይቃል።  ከሁሉ የፈቃደ እግዚአብሄር እና የፈቃደ አላህ መቅደም፤ ጥሞናዊ ራስን የመግራት ሂደት የስኬትን #ደርባባ #ቋሚ #አሻራን ይወልዳል የሚል ሙሉ እምነት አለኝ። ሥርጉትሻ2024/07/19  

ክህሎት ...

 ክህሎት በሂደት የሚገኝ የተመክሮ አወንታዊ ቅምረት ነው በእኔ ዕይታ። ክህሎት የሚገኘው ተሰጥዖን በማዳበር እና #ስሜት እና ህሊናን #በማሰልጠን ነው የሚል ሙሉ ዕምነት አለኝ። ሥርጉትሻ 2024/07/19

ሰው #ከዕንቁ በላይ የከበረ ነው።

  ሰው #ከዕንቁ በላይ የከበረ ነው።  ለሰው ልጅ #ስሜት እና #ህሊና #ቅርበት እና #ትርጉም መስጠት ነው መሪነት። መሪነት ማዕከሉ #ሰው ሊሆን ይገባል።  ይህም ልሙጥ ሊሆን አይገባም። #ሰብዓዊ መሆን ይገባዋል።  የሰው ልጅ መከፋት ሆነ መደሰት #ውስጡ ሊሆን ይገባል።  በምድራችን ካሉ ድንቅ ነገሮች በላይ የሰው ተፈጥሮ #ዕፁብ #ድንቅ ነው። ዕፁብ ድንቅ ተፈጥሮው የሰው ልጅ ምድርን በጥበቡ ለመኖር ብቁ አኗኗሪ ፈጥሮ ይጠበብባል።  ስለሆነም ከሰው የሚነሳ ዕሳቤ #ሰዋዊ እንጂ #ሸቀጣዊ ሊሆን አይገባም። ሰዋዊነት እንደ ሸቀጣ ሸቀጥ #በገቢያ ህግ ስለማይገዛ። ሥርጉትሻ 2024/07/19

ሕይወት

  ሕይወት #የጥያቄ እና የመልስ #ጭማቂ ናት የሚል ዕምነት አለኝ። ይህ ማለት ህይወት በዬራሳቸው የአፈጣጠር አንባ የሰሉ ሁለት የማይጣጣሙ ተቃራኒ ነገሮች ጥምረትም ናት እንደ ማለት። ሥርጉትሻ 2024/07/19

እንዳሻህ ሂድብኝ ...

  ግድዬለም፦ ግድዬለም እንዳሻህ ሂድብኝ አዬር ካልቸገረኝ፦ እኔ ምን ሲገደኝ ብቻማ --- ብቻማ /// ምልሰትህ አይራቀኝ ሰባዕዊነት ጥራኝ።  ጠረንህም ይጥማኝ!  ሥርጉትሻ024/07/19