ልጥፎች

#ስለጣምራው #ተጋድሎ የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ የዬትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ማኒፌስቶ #ጥገኛ፤ #ተቀጥላ ሊሆን አይገባም።

  #ስለጣምራው #ተጋድሎ የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ የዬትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ማኒፌስቶ #ጥገኛ ፤ #ተቀጥላ ሊሆን አይገባም።  በተለይ ሙሉ 50 የነቀለውን #የሶሻሊዝም ጠንቀኛ ርዕዮት እስከ እንጥፍጣፊው #አክ ሊለው ይገባል። ይህ ራሱን የቻለ የህሊና ብስለትን #የውስጥ #መረጋጋትን የሚጠይቅ ስለመሆኑ ይረዳኛል። ሕዝባችን ቋያ ላይ ስላለ። አንዱን ባነሳስ ስለአሰጋኝም እርስ በርስ #ዬመጠፋፋት ጉዳይ ሊታሰብበት ይገባል። አማራን ሙሉ በሙሉ የበቀሉ መሪወችን የቀጠፈውም ይህ ዕሳቤ ነው።  ባለቤት አልባ አድርጎ ማህበራዊ መሠረቱን ያጣው ሁሉ የተመመበትም። የአማራ ፖለቲካ ከተኖረበት የሴራ እና የአድማ፤ የሳይለንት ኒግሌሽን ወዘተ እራሱን ሊያጠራ ይገባል። ይሄ አድመኝነት፤ #በቀለኝነት ።  አንድም የአማራ ሚዲያ ሁሉንም አማራ #ሲያቅፍ አላዬሁም፤ አንድም የአማራ ድርጅት ሁሉንም የአማራ አቅም #ማዕከል አድርጎ ሲነሳ አላዬሁም።  የአማራ ፖለቲካ ሳያውቀው የሶሻሊዝም ጠረን ተጠቂ መሆኑን አስተውያለሁኝ። #ጣምራ #ተጋድሎው ፦ የነጠረ ውስጡን ያዬ የርዕዮተዓለም አቅጣጫን መንደፍ ይገባል።   #ሶሻሊዝምን እስከ #ዝክንትሉ #ሃራም ሊለው ይገባዋል የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ።  ሥርጉ2024/07/022

#መተንፈስ #ለተገደበበት ቅን የአማራ ህዝብ፦ #መፀነስ አይገባህ ለተባለ ደግ የአማራ ሕዝብ፤

  #መተንፈስ #ለተገደበበት ቅን የአማራ ህዝብ፦ #መፀነስ አይገባህ ለተባለ ደግ የአማራ ሕዝብ፤ #መማር አይገባህም ለተባለ ትዕግስተኛ የአማራ ህዝብ?  ዌልካሚንግ ለሆነ የአማራ ሕዝብ ማረስ - መነገድ - መታከም - #መጓጓዝ - ሃብት ማፍራት በፍፁም ሁኔታ ማዕቀብ ለተጣለበት ህዝብ?  ልጆቹ #እንደወጡ ለሚቀሩበት ሩህሩህ የአማራ ሕዝብ? በመላ ኢትዮጵያ በፖለቲካ፤ በዕድል፤ በዕውቅና ስልታዊ ጥቃት ለሚደርስበት የህግ አምላክ ተገዢ ለሆነው የአማራ ህዝብ፤ #ካቴና ቤቱ ትዳሩ፤ #ድሮን ኑሮው ለሆነ ትሁት የአማራ ሕዝብ?  ሙሉ 8 ዓመታት #በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሚሰቃይ የአማራ ሕዝብ? #በግሪደር ለሚቀበር ምንዱብ ሕዝብ? ከአንተ #ደን ይበልጣል ለሚባል የተገፋ ሕዝብ? መሪወቹን ሰርክ #በሸፍጥ በሚያጣ ግን የመቻቻል ፀጋ ለተሰጠው የአማራ ሕዝብ 6 ዓመት በመላ ኢትዮጵያ ያደራጃቸው ተቋማት፤ ከተሞች የዶግ አመድ ለሆኑበት የአማራ ሕዝብ የህልውና እና የማንነት ግዙፍ ተጋድሎ #አቃቂር ፤ #ቅልጣን ? #መሞላቀቅ ? #ዝነጣ ?  #ሌግዠሪ ያስፈልገው ይሆን???? ሥርጉትሻ 024/07/22

From America to Ethiopia || ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ | Ari Floyd || Manyazewal Esh...

ምስል

"አለምን ይወቁ EP 28: Seychelles│ሲሼልስ" እኛ የት ላይ ነን፧

ምስል

ልቅና በልዕልና፨ ቢስ አይይብን፨ አሜን፨

ምስል

ሰው ኖሯል የሚባለው ምን አድርጎ ሲያልፍ ነው? || ዶ/ር አብርሃም አምሃ እና ገነት አህፈሮም

ምስል

መሪነት፦ #ተጠናቆ #መፈጠርን ይጠይቃል። በተለይ ሰውን ማዕከል በማድረግ።

 መሪነት፦ #ተጠናቆ #መፈጠርን ይጠይቃል። በተለይ ሰውን ማዕከል በማድረግ።   እንዴት ነው ሪኮመንድ የሚደረገው?  እራስን #በመምረጥ ?  የራሱን ከተንቆናጠጠ በኋላ ሌላውን እንደ ሥልጣን #ጥመኛ በማዬት?  ለምን?  ሌላው እኔ #እመጥናለሁ ወይ ተብሎም እራስ አይጠየቅም።   #ፕሮቶኮሉንስ እችለዋለሁን ብሎ ማሰብም ይገባል። አሁን ጠቅላይ ሚር አብይ ንግሥናውን ሲመኙ #ፕሮቶኮሉን ጭራሽ አላሰቡበትም። ለዚህ ነው ብዙ ነገር #ልቅ የሆነው። ይህን የሚከታተል አካልም ያላቸው አይመስለኝም። #ሲነሪቲም አለ ሥርዓት ባለው መንግሥታዊ አወቃቀር።  ይህን ጠሚር አብይ ልብ ያሉት ይመስለኛል። #ቀደምቶችን #ይሸኛሉ ። የሳቸውን ተሿሚወች መርጠው #እንዲያመልኳቸው ያደርጋሉ። አዲስ ነገር ፈጥረው። " #ፊልድ ማርሻል" እንደ ምሳሌ መውሰድ እንችላለን።  ልቅና በልዕልና የነበራቸው ቀደምት የኢትዮጵያ ጀግና መኮንኖች መ እንኳን ያልተሰጣቸውን ነው የተከወነው።  የሆነ ሆኖ መሪነትም እራስን፦ አቅምን እመጥናለሁ ወይ? ብሎ መጠዬቅን ይጠይቃል። ተያያዥ ጉዳዮችም።  ሥርጉትሻ 2024/07/20

#ብልጠት እና #ስልት።

  #ብልጠት እና #ስልት ።   በ2014 እ.ኤ.አ በደጉ ሳተናው ድህረ ገጽ ከሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ጋር ነጥቡን አንስቼ ሞግቼበት ነበር። ጽፌበት ነበር።  የሆነ ሆኖ ለመቆናጠጫ #ብልጠት ደራሽ፤ ቅጽበታዊ ሲሆን ለእኔ ሳላሞላቅቀው ቁልጭ ያለ #ማጭበርበር ነው። ታሪክም አልቦሽ።  መስዋዕትነቱም የገዘፈ አስታዋሽ አልቦሽ የውሻ ደም ሆኖ ቀሪ። ስልት ግን በጠራ ዓላማ እና ፍላጎት የታነፀ፦ በቀነሰ መስዋዕትነት፤ እንዲሁም መስዋዕትነቱን #ዕውቅና #በሰጠ በተደራጀ የሃሳብ #ብቃት በስክነት የሚከወን የአቅም ልዕልና ከፍ ያለ ደረጃ ነው።  ስልት የላቀ የሥራ ባህል ጥበብ ነው። የታወቅም // የተሰወረም ታክቲክ እና ስትራቴጂ በጊዜ፤ በሁኔታ፦ በአቅም የሚታሰቡ ትልሞች የሚቀመርበት።   አቅም መዋለ ንዋያዊ ብቻ ሳይሆን የሰውን የህሊና እና የጉልበት ችሎታን፦ በተጨማሪም ልምድን፦ ተመክሮን፦ ክህሎትንም ሁሉ ያካትታል። የነፃ አገልግሎትንም ይጨምራል ተመን የለሽ ቢሆንም።  ሥርጉትሻ2024/07/20

መሪነት፦ #ተጠናቆ #መፈጠርን ይጠይቃል።

 መሪነት #አቅም #መፍጠር ነው ታላቁ ተልዕኮው።  የፈጠረውን አቅምም በቅጡ ለመምራት የራሱን የምምራት #አቅም ፦ #ክህሎት ማሰልጠንም ይገባዋል።  ይህን አዋዶ ህዝብ ጠቀም ማድረግም ሌላው የመሪነት የጥበብ ዘይቤ ነው።  ሥርጉትሻ 2024/07/17   መሪነት፦ #ተጠናቆ #መፈጠርን ይጠይቃል። እንዴት ነው ሪኮመንድ የሚደረገው? እራስን #በመምረጥ ? የራሱን ከተንቆናጠጠ በኋላ ሌላውን እንደ ሥልጣን #ጥመኛ በማዬት? ለምን? ሌላው እኔ #እመጥናለሁ ወይ ተብሎም እራስ አይጠየቅም። #ፕሮቶኮሉንስ እችለዋለሁን ብሎ ማሰብም ይገባል። አሁን ጠቅላይ ሚር አብይ ንግሥናውን ሲመኙ #ፕሮቶኮሉን ጭራሽ አላሰቡበትም። ለዚህ ነው ብዙ ነገር #ልቅ የሆነው። ይህን የሚከታተል አካልም ያላቸው አይመስለኝም። #ሲነሪቲም አለ ሥርዓት ባለው መንግሥታዊ አወቃቀር። ይህን ጠሚር አብይ ልብ ያሉት ይመስለኛል። #ቀደምቶችን #ይሸኛሉ ። የሳቸውን ተሿሚወች መርጠው #እንዲያመልኳቸው ያደርጋሉ። አዲስ ነገር ፈጥረው። " #ፊልድ ማርሻል" እንደ ምሳሌ መውሰድ እንችላለን። ልቅና በልዕልና የነበራቸው ቀደምት የኢትዮጵያ ጀግና መኮንኖች መ እንኳን ያልተሰጣቸውን ነው የተከወነው። የሆነ ሆኖ መሪነትም እራስን፦ አቅምን እመጥናለሁ ወይ? ብሎ መጠዬቅን ይጠይቃል። ተያያዥ ጉዳዮችም። ሥርጉትሻ 2024/07/20     መሪነት #በችሮታ ወይንም #በይሉኝታ ወይንም #በቤተሰባዊ ትስስር ወይንም በማህበራዊ ኑሮ #ቅርበት እና #ርቅት አይቸረቸርም። መሪነት #በሥርዓት - ጥልቅነት፤ በሃሳብ - #ብሩህነት ፤ በተመክሮ - #ብቃት እና #ስኬት ፤ በማድመጥ እና በማደራጀት ልዩ #ስልታዊ አቅም፤ በችሎታ እና በሃሳብ ግልፅነት እና...

ልበልሽ ይሆን ውዳሴ? ይመቸዋል እና ለነፍሴ፨

ምስል
·        https://www.lora.ch/programm/alle-sendungen?list=Tsegaye ·        https://www.facebook.com/sergute.selassie/ https://sergute.blogspot.com/2021/02/blog-post.html?spref=tw