ዓለም ዓቀፍ #ሸላሚ ድርጅቶች ይህን ትጋት፤ ደግነት በትህትና ልግስና በትዕግሥት የደግነት ተግባር ሲጎመራ ምን ያደርጉ ይሆን???
ዓለም ዓቀፍ #ሸላሚ ድርጅቶች ይህን ትጋት፤ ደግነት በትህትና ልግስና በትዕግሥት የደግነት ተግባር ሲጎመራ ምን ያደርጉ ይሆን??? "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም።" (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱) ለትውልድ የሆነ #መሰጠት ። ለአደራ ያበቃ #አጽናኝነት ። ባለ አሻራ #አይዟችሁባይነት ። ድንቅ - የሚያስቀና - የሚመስጥ ሰብዕና። ዕጣ ነፍስ #በይቻላል መንፈስ ችግርን የመጋፈጥ ልዩ ተጋድሎ። አንድ መጸሐፍ ይወጣዋል። የፕለይ ፀሐፊወች ይህን የዕውነተኛ ታሪክ ጭብጥ ትዘሉት ይሆን??? የእዮር #መሰጠት ። ዓለም ዓቀፍ ሸላሚ ድርጅቶች አሜሪካ እና ካናዳ ያሉትም የኢትዮጵውያን ተቋማትም ይህን ብቃት #ባሊህ ይሉት ይሆን ወይንስ #ያገሉት ??? እምናዬው ይሆናል። አብነትትነት ይህ ነው። #አሻራ ይህ ነው። የአገር #ካስማነት ይህ ነው። #የትውልድ መሆን ይህ ነው። #ሰዋዊነት ይህ ነው። #ተፈጥሯዊነት ይህ ነው። እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ #መክሊት ይዞ ይወለዳል። እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ #ጥሪ ይዞ ይወለዳል። እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ #መልዕክት ይዞ ይወለዳል እላለሁ። መፃህፍቶቼ ላይም አበክሬ እገልፀዋለሁ። ይህ ጥሪ፤ ይህ ለደግነት ፖስተኝነት፤ ይህ ችግርን ተቋቁሞ ለመፍትሄው የመምራት የማስተዳደር ብቃት እንዳይሰወር ስለምሰጋ ነበር እንደዛ እምተጋው። እንዲህ በጥሪ ልክ ሆኖ መገኜት #መታደልም - #መመረቅም - #መሰጠትም ነው። አንድ ሰው ይህን ያህል ችግርን የመቋቋም አቅም ከዬት አገኜ? #ከእዮር #አደባባይ ። #ቅንነት የሰራው #ደግነት ነው። ሁሉም ለአንዱ ፦...