ልጥፎች
Ein Geschenk ist ein Diplomat.
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
Ein Geschenk ist ein Diplomat. Auch eine Schenkung ist ein Zeugnis. Ein Geschenk ist eine Unterschrift. Ein Geschenk ist auch die Menschheit. Ein Geschenk ist Grosszügigkeit. Eine Schenkung ist ein organisierter Ausdruck des guten Willens. Ein Geschenk ist eine positive Bastelei. Ein Geschenk ist aufrichtig. Ein Geschenk ist das Geben im Inneren. Ein Geschenk ist weise und klug. Ein Geschenk bereitet sowohl dem Absender als auch dem Empfänger friedvolle Freude. Ein Geschenk gibt auch Gesundheit. Schenken ist Heiligung. Auch ein Geschenk ist ein Segen. Der Abschluss ist auch ein Geschenk. Ein Geschenk ist für mich Menschenrechtsaktivist. Schenken respektiert die Natur. Ein Geschenk ist ein einzigartiges Naturphänomen, das zum Lachen anregt. Ein Geschenk ist auch eine Vereinbarung. Vertrag, Versprechen. Ein Geschenk ist eine Säule der Natur der Liebe. Herzliche. Sergute©Selassie (Switzerland, Wintertur.) 20.12.2024.
"የኢትዮጵያ መንግሥት ጥሰት የፈጸሙ ኃላፊዎችን ከስልጣን እንዲያነሳ የአሜሪካ የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ መከሩ BBC" በማስተዋል ይደመጥ።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
https://www.bbc.com/amharic/articles/cvg69094qgeo "የኢትዮጵያ መንግሥት ጥሰት የፈጸሙ ኃላፊዎችን ከስልጣን እንዲያነሳ የአሜሪካ የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ መከሩ" "የኢትዮጵያ መንግሥት፤ በሰብአዊ መብት ጥሰት የሚከሰሱ ባለስልጣናትን፤ "በተለይም የሠራዊት አባላትን በአስተዳደራዊ ፈቃድ" ከስልጣን እንዲያነሳ የአሜሪካ የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አምባሳደር ቤዝ ቫን ስካክ መከሩ። በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች "የሚፈጸሙ ያሉ ጥሰቶች" በቀጠሉበት ሁኔታ ሁሉን አቀፍ የሽግግር ፍትህን መተግበር "አስቸጋሪ" ካልሆነም "የማይቻል" እንደሆነ ተናግረዋል። እንደ የጦር ወንጀል እና በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል ያሉ የሰብአዊ መብት ጉዳዮች በተመለከተ የአሜሪካውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን የሚያማክረውን ቢሮ የሚመሩት አምባሳደር ቤዝ ይህንን የተናገሩት ረቡዕ ታሕሳስ 9፤ 2017 ዓ.ም. ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ነው። የትናንቱ መግለጫ፤ አምባሳደር ቤዝ ከሕዳር 29 እስከ ታህሳስ 2፤ 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ የነበራቸው ቆይታ ላይ ያተኮረ ነው። "በኢትዮጵያ እና በመላው አፍሪካ የተጀመሩ የሽግግር ፍትህ እና ተጠያቂነት ሂደቶችን ለማጠናከር" ወደ ምስራቅ አፍሪካ ተጓዙት አምባሳደሯ፤ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት ጋር መገናኘታቸውን እና የፍትህ ሚኒስቴር ባዘጋጀው የሽግግር ፍትህን የተመለከተ ውይይት ላይ መካፈላቸውን ገልጸዋል። የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍትህ ቢሮ ኃላፊዋ፤ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የኢትዮጵያን የሽግግር ፍትህ ሂደት ለመደገፍ ፍላጎት እንዳለው የገለጹ ሲሆን "እስካሁን ባለው ...
ጥንካሬ + ስኬት= ድንቅነት። "ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ አቶ አምሳሉ ፀጋዬ ካሳው BBC"
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ጥንካሬ + ስኬት= ድንቅነት። https://www.bbc.com/amharic/articles/cr7v49kxg24o ባሕር ዳር የተወለዱት ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሪፐብሊካን እጩ በኮሎራዶ ግዛት የከተማ ምክር ቤት ምርጫ አሸነፉ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ አቶ አምሳሉ ፀጋዬ ካሳው 18 ታህሳስ 2024 ትውልደ ኢትዮጵያዊ-አሜሪካዊው አቶ አምሳሉ ፀጋዬ ካሳው በኮሎራዶ አገረ ግዛት፣ የአውሮራ ከተማ ምክር ቤት ምርጫን ከትላንት በስትያ አሸንፈዋል። ይህም በኮሎራዶ አገረ ግዛት የመጀመርያው ትውልደ ኢትዮጵያዊያዊ ተመራጭ እንዲሁም የመጀመሪያው አፍሪካዊ ስደተኛ የምክር ቤት አባል ያደርጋቸዋል። የተካሄደው ምርጫ የማሟያ ሲሆን አቶ አምሳሉ ለአንድ ዓመት የሚያገለግሉ ይሆናል። የተመረጡበትን አራት ዓመት ሳያጠናቅቁ ከኃላፊነት የለቀቁት የምክር ቤት አባል ፕሮ ተም ደስተን ዘፋነክን ተክተው ይሠራሉ። የአውሮራ ከተማ ምክር ቤት ከ37 ተወዳዳሪዎች መካከል ሦስት እጩዎችን ለመጨረሻ ዙር ውድድር አቅርቧል። ሦስቱ እጩዎች ዳንኤል ሌሞን፣ ጆናታን መክሚለን እና አምሳሉ ካሳው በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ ምልልስ ተደርጎላቸዋል። የአውሮራ ከተማ ከንቲባ ማይክ ኮፍማን ካቀረቧቸው እጩዎች መካከል እንደሆኑ አቶ አምሳሉ ተናግረዋል። ቃለ ምልልሱን ጨምሮ ከማኅበረሰቡ አስተያየት የመቀበልና ሌሎችም ሂደቶች ሁለት ወር ገደማ ወስደዋል። ድምጽ ሰጥተው አሸናፊውን የለዩትም የከተማዋ ምክር ቤት አባላት ናቸው። 'ዘ ዴንቨር ጋዜት' ባወጣው ዘገባ መሠረት፣ ከ10 የምክር ቤቱ አባላት 6ቱ በሰጡት ድጋፍ አቶ አምሳሉ አሸናፊ ሆነዋል። የተመረጡበትን አራት ዓመት ሳያጠናቅቁ ከኃላፊነት የለቀቁትን የምክር ቤት አባል ተክተው ለአንድ ዓመት ከሠሩ በኋላ በቀጣይ ምርጫ እ...
እውነት ነውን የካፒቴን ማስረሻ ሰጤ #ወላጆች #ታስረዋልን?
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
እውነት ነውን የካፒቴን ማስረሻ ሰጤ #ወላጆች #ታስረዋልን ? "የቤትህ ቅናት በላኝ።" እንዴት ሰነበታችሁ ማህበረ ቅንነት? ዕውነት ነውን የካፒቴን ማስረሻ ወላጆች ታስረዋልን??? ይህ ከሆነ #እርግማንን ትውልዱ ተጎንብሶ ያፍሳታል። የአማራ ወላጆች በአማራ ልጆቻቸው ከመታሰር፤ ከመንገላታት በላይ ምን #እርግማን አለና። ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ በዘመነ ህወሃት እስር ቤት አሳሩን ያዬ መከረኛ ወጣት ነው። በእስራት ዘመኑ ሁሉ ቤተሰቦቹ አብረው ተንገላተዋል። በዘመነ አብይዝም መቅድም ላይ ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ መላ ኢትዮጵያን #ተንከራቶ የአማራን ወጣቶች በአካል ተገኝቶ #በመንፈስ አደራጅቷል። በዚህ ንቅናቄው ስጋት የገባው የአብይዝም አገዛዝ አፍኖ ሊወስዳቸው ካሰባቸው ወጣቶች አንዱ እንደነበር ነብዬ ብጄ አሳምነው ጽጌ ነግረውናል። በኋላም ከእነ ዘሜ ጋር ወጣቶችን በማሰልጠን መጠነ ሰፊ ተግባር ፈጽሟል። በአንድ ቃለ ምልልሱ ላይ ወደ አማራ ትግል ለምን እንደገባ ሲጠዬቅ #አታጋይ ጠንካራ #የዜግነት የፖለቲካ ድርጅት ባለመኖሩ ስለመሆኑ ሲናገር ሰምቸዋለሁ። ሚሊተሪ የሚቀድምበት ብሄራዊ ጉዳይ ነውና። በዚህ ምክንያት ይመስለኛል #ባልደራስን የተቀላቀለው። ምንም እንኳን ባልደራስ በአደረጃጀቱ የአዲስ አበባ ቢሆንም። የአደረጃጀት መርሁ ፈጽሞ ባይፈቅድም። የሆነ ሆኖ ሶስቱ ዘሜ፤ ማስሬ፤ አስረሱ የሚያስደስት አንድነት፤ ብቃት እና ችሎታ ያላቸው ወጣቶች የአማራን ትግል ችግር በጥንቃቄ ቀድመው የተረዱ ወጣቶች ናቸው። የአባት አደሩን ፋኖ #በማዘመን እረገድም #ባልተበላለጠ ተሳትፎ ተመክሯቸውን በእኩልነት ያጋሩ ድንቅ ወጣቶች ናቸው። በመሃል ክፍፍል የፈጠሩባቸው በተደራጁበት፤...
#እራህብ። " የሞት አፋፍ ላይ።" #ዛሬን ማኖር #በዛሬ ድርጊት #ፍሬ ነገን ማስቀጠል።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
#እራህብ ። " የሞት አፋፍ ላይ።" #ዛሬን ማኖር #በዛሬ ድርጊት #ፍሬ ነገን ማስቀጠል። የኢትዮጵያ መንግሥት ሳቢያ ሳያስፈልገው ለሰባዕዊነት የሚደረገውን ተግባር መደገፍ ይገባዋል። ሰው የጀንበር ሥራ አይደለምና። የክልሉም አስተዳደር ይህን ጉዳይ ባሊህ ሊለው ይገባል። ለፋኖም ይህ ጉዳይ ጉልላቱ ሊሆን ይገባል። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" እንዴት አደራችሁ ማህበረ ቅንነት? ትናንት የምችልበት ሁኔታ ላይ ስላልሆንኩ ነበር ሼር አድርጌ አስተያዬት ያልፃፍኩት። የሆነ ሆኖ በዋርካው ምሬ ጉዳይ እኔ እንደታዘብኩት የተረጋጋ መንፈስ እንዳለ ነው። ስለሆነም ይህን የሰባዕዊ ጉዳይ አፈፃፀም ዕውን ይሆን ዘንድ የሚተጋበት ይሆናል ብዬ አስባለሁ። #ዋርካው ምሬ ደሴ፤ ኮንበልቻ፤ ወልድያ፤ ወረባቡ፤ ሐይቅ ከትልቅ እስከ ትናንሽ ከተሞች ብርቱ ጥንቃቄ ያደርግላቸዋል። ለተዋህዶ በዓላት ሆነ ለረመዳን ፆም ፍቺም #ጥንቁቅ እና ብልህ ብቻ ሳይሆን #ምስጉን ነው። ስለሆነም ይህን ቀን የማይሰጠውን የራህብ ጉዳይ በሚመለከት ተገቢው እገዛ ለወገኖቻችን ይደርስ ዘንድ ምቹ ሁኔታ ዋርካው ምሬ ይፈጥራል ብዬ አስባለሁኝ። መሆንም ያለበት ይህ ነው። ለነገ #ነፃነት ዛሬን #መኖር ፤ ዛሬን #ማኖር ቀዳሚ በኽረ ጉዳይ ስለሆነ። በትናንት ውስጥ ዛሬ ነበር። በዛሬ ውስጥም ነገ እንዲኖር ዛሬን የማኖር ጥበብ በሁሉም ዘርፍ ዕውቅና ሊያገኝ ይገባል። የትግል ማዕከሉ ሰባዕዊነት ለሆነ የግል ሆነ የወል ማንነት። በራህቡ ምክንያት መቋቋም የተሳናቸው የትውልድ ዕንቡጥ ህፃናት ማለፋቸውን ሰምቻለሁኝ። እጅግ አዝናለሁ። ጣር ላይ ያሉም ይኖራሉ። ጉዳዩ ከአቅም በላይ፤ ከቁጥጥር ውጪ ከመሆኑ በፊት #ፈጣን የሆነ የፋኖ ውሳኔ ያስፈልጋል። በህይወታቸው ወስነው እርዳታውን ለማድረስ የ...
በሰሜን ወሎ ህጻናትን ጨምሮ 10 ሺህ ገደማ ሰዎች በከፍተኛ የምግብ እጥረት መጎዳታቸው ተገለጸ በሰሜን ወሎ በምግብ እጥረት ምክንያት የተጎዳ ሕፃን BBC
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
https://www.bbc.com/amharic በሰሜን ወሎ ህጻናትን ጨምሮ 10 ሺህ ገደማ ሰዎች በከፍተኛ የምግብ እጥረት መጎዳታቸው ተገለጸ በሰሜን ወሎ በምግብ እጥረት ምክንያት የተጎዳ ሕፃን የፎቶው ባለመብት, BUGNA HEALTH BUREAU 17 ታህሳስ 2024 በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በተከሰተ ድርቅ እና የምግብ እጥረት ከአምስት ዓመት በታች ያሉ ህፃናትን ጨምሮ 10 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች መጎዳታቸውን ወረዳው አስታወቀ። በክልሉ ባለው ግጭት እና ተፈጥሯዊ ተፅዕኖ ምክንያት ወረዳው ለድርቅ እና የምግብ እጥረት መጋለጡን የቡግና ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ገ/መስቀል ዓለሙ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በአማራ ክልል የተነሳው ግጭት አንድ ዓመት ከመንፈቅ ያለፈው ሲሆን ከግጭቱ ባለፈ ወረዳው "ዝናብ አጠር እና በተፈጥሮ የተጎዳ ነው" ያሉት ኃላፊው በተደራራቢ ችግሮች ምክንያት የምግብ እጥረት መከሰቱን አስታውቀዋል። "ማኅበረሰቡ ምርት ባለማግኘቱ እናቶች ልጆቻቸውን በአግባቡ መግበው የተሻለ የጤና እድገት እንዳይኖራቸው [አድርጓል]" ሲሉ ተፈጥሯዊውን ተጽዕኖ የገለጹት አቶ ገ/መስቀል፤ "ረድኤት ድርጅቶችም ለማኅበረሰቡ አልደረሱለትም" ብለዋል። በወረዳው ብርኮ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ የካባ የአንድ ዓመት ከሦስት ወር መንታ ወንድና ሴት ልጆቻቸው በምግብ እጥረት "ስቃይ" ውስጥ እንደሆኑ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ምን አግኝተን እንርዳቸው? እስካሁን ድረስ በተቻለን ይዘናቸው ነበር። ከአዲስ ዓመት ወዲህ ግን ምንም ነገር የለም። ተያይዞ ቁልጭልጭ ሆነ እኮ?" ሲሉ ስላሉበት ሁኔታ አስረድተዋል። "ጡጦ የምልበት ጎን [አቅም] የለኝም። ጡቴን ብቻ ነው ሳጠባቸው የከረምኩት። የጡት...
"የአሜሪካ ትራንስፖርት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የገንዘብ ቅጣት አስተላለፈ" BBC.
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ኦኦ። " የአሜሪካ ትራንስፖርት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የገንዘብ ቅጣት አስተላለፈ" BBC. https://www.bbc.com/amharic/articles/cq8qzgn19ylo ከ 3 ሰአት በፊት "የዩናይትድ ስቴትስ ትራንስፖርት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኢቲሀድ ኤርዌይስ ሕግ በመጣሳቸው በገንዘብ እንዲቀጡ ወስኗል። ሚኒስቴሩ ባለፈው ሐሙስ ባወጣው መግለጫ መሠረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሜሪካው ዩናይትድ ኤርላይንስ መለያ (ኮድ) በመብረሩ 425 ሺህ ዶላር እንዲቀጣ ተወስኗል። የተባበሩት አረብ ኤምሬቶቹ ኤቲሀድ አየር መንገድ ደግሞ ጄትብሉ በተባለው የአሜሪካ አየር መንገድ መለያ ቁጥር በመብረሩ 400 ሺህ ዶላር ተቀጥቷል። ሚኒስቴሩ በድረ-ገፁ ባወጣው መረጃ እንዳለው ሁለቱ አየር መንገዶች፤ በፌዴራል አቪዬሽን ባለሥልጣን (ኤፍኤኤ) የአሜሪካ አየር መንገዶች እንዳይበሩ በተከለከሉባቸው የአየር ክልሎች በመብረራቸው ነው ሕግ የጣሱት። ሁለቱ አየር መንገዶች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸውም ተዘግቧል። አቪዬሽን ኮንሲዩመር ፕሮቴክሽን የተባለው የዩናይትድ ስቴትስ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ቢሮ ባደረገው ምርመራ ከአውሮፓውያኑ የካቲት 2020 እስካ ታኅሣሥ 2022 ባለው ጊዜ ነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጥፋቱን ፈፅሟል የተባለው። በዚህ ጊዜ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዩናይትድ ኤርላይንስን ኮድ ተጠቅሞ ከኢትዮጵያ ጂቡቲ በርካታ በረራዎችን አድርጓል፤ ይህ የአየር ክልል ደግሞ የአሜሪካ አየር መንገዶች እንዳይበሩበት በፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር ክልከላ የተደረገበት ነው ይላል። የአፍሪካ ግዙፉ አየር መንገድ ይህንን ድርጊት የፈፀመው ከዩናይትድ ስቴትስ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ፈቃድ ውጭ መሆኑን መግለጫው ያ...