ልጥፎች

ከ2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የዴሞክራሲ ጽንሰት ውርጃ {ዘለግ ያለ ሙግት ከምርጫ ቦርድ ጋር}

ምስል
  እንኳን ወደ ቀንበጠ ብሎግ በሰላም መጡ። „ድሆች ግን ዳግመኛ በመኝታቸው ያስባሉ፣ ባለ ጠጎች ባይቀበሏቸው ግን ልምላሜ እንደሌለው እንደ ደረቅ እንጨት ይሆናሉ፤ ርጥበትም ከሌለ ዘንድ ሥር አይለመልምም፤ ሥርም ከሌለ ቅጠሉ አይለመልምም።“(መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ ምዕራፍ 26 ቁጥር 1) የ ዴሞክራሲ ጽ ንሰት ው ርጃ። ከሥርጉተ©ሥላሴ Seregute©Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። 29.12.2019 ·          መ ቅድም። አምላክ አለቀሰ መርኽ አለቀሰ የቃልኪዳን ሰነድ ሰለተቦደሰ የህሊና ልኩ ስለተቀደደ። ·          እ ፍታ። በዚህ ጹሑፍ የፖለቲካ ድርጅት አፈጣጠርን የሥርዓት ግሽበትን እንመለከታለን። መግቢያ ላይ ያለው ቃለ ወንጌልም ያመሳጥረዋል። ጉዳዬ ሥር ከሌለው ፍሬ ሰብል ጥበቃ ተስፋው ሩቅ ስለመሆኑ ያስተረጉማል። ተስፋ መውደቅ ሲያምረው እንዲህም ይፈተናል። የምርጫ ቦርድ አዲሱን የብልጽግና (ፓርቲ?) ህጋዊ ዕውቅና እንደ ሰጠ፤ በቱማታ እንደ መዘገበው ከሰሞናቱ ጠቅሷል። በዚህ አያያዝ የዴሞክራሲ ችግኝ ማብቀያ ተብሎ የታሰበው  የመጀመሪያ የጽንስ ውርጃውን አሳይቶናል። በአብን ላይ ያለው እምቅ ጫናን ቆዬን ብለን ማለት ነው። እሱ እራሱን የቻለ የታመለ የአምክንዮ ሽፍጥ ስላለበት።   ግን የአገሬ ቅኔዎች እንዴት ናችሁ? ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ ይህን የብልጽግና(ፓርቲ?) አመሰራረት የግድፈት አካሄድ በሚመለከት በፌስቡኬ ላይ አጫጭር ጹሑፎችን ሳቀርብ ሰነባብቻለሁኝ። አሁን ጫን ያለ የመርኽ ይፋ...