ዕውነት አያፍርም 01.01.2023
· ዕውነት አያፍርም ። · መርኃዊነት አይዝግም ። · በመሆኔ ውስጥ ያለሁት እኔ ብቻ ነኝ። · ፍቅር ዬፊደል ገበታ ነው። · ዬፍቅር ፖስተኛ ዓይን ነው። · ጉርሻ ዬፍቅር ጆሮ ነው። · ዬነፃነት እርቦ፤ ዬነፃነት ሲሶ ዬለውም። · ጥላቻ ስንቁ የሆነ ሰብዕና አልቋል። · ታማኝነት ብራ ነው። · ቅንነትም ጎህ ፨ · ዬማሰብ ሚስጢር ማስተዋል ነው። · ህሊናዊነት ከቅንነት ይመነጫል፨ ! · እኛን ስለሰጠን አምላካችነን እናመስግን፨ እኔ …. ምን ያህል እንደተጓዝኩ አላውቅም፨ ምን ያህል እንደሚቀረኝም አላውቅም። አለማወቄን ስጠይቀው አለማወቁን ገለጸለኝ...