ዕውነት አያፍርም 01.01.2023

·        ዕውነት አያፍርም

·        መርኃዊነት አይዝግም

·        በመሆኔ ውስጥ ያለሁት እኔ ብቻ ነኝ።

·        ፍቅር ዬፊደል ገበታ ነው።

·        ዬፍቅር ፖስተኛ ዓይን ነው።

·        ጉርሻ ዬፍቅር ጆሮ ነው።

·        ዬነፃነት እርቦ፤ ዬነፃነት ሲሶ ዬለውም።

·        ጥላቻ ስንቁ የሆነ ሰብዕና አልቋል።

·        ታማኝነት ብራ ነው።

·        ቅንነትም ጎህ

·        ዬማሰብ ሚስጢር ማስተዋል ነው።

·        ህሊናዊነት ከቅንነት ይመነጫል፨!

·        እኛን ስለሰጠን አምላካችነን እናመስግን፨

 

እኔ ….

ምን ያህል እንደተጓዝኩ አላውቅም፨

ምን ያህል እንደሚቀረኝም አላውቅም።

 አለማወቄን ስጠይቀው አለማወቁን ገለጸለኝ።

ተስፋን እጠብቃለሁኝ።

 

ልስሉስ ዓውደዓመት ይሁንልን። አሜን።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።