የጠቅላይ ሚር ሄሮድስ አብይ አህመድ አሊ #የአስተምህሮት ጥሰት ጎርፍ #ሦስት በኽረ ምሶሶወችን ነጣጠሉት። ተረተሩት።

 

የጠቅላይ ሚር ሄሮድስ አብይ አህመድ አሊ #የአስተምህሮት ጥሰት ጎርፍ #ሦስት በኽረ ምሶሶወችን ነጣጠሉት። ተረተሩት።
ሌላው ……
ዬኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት #ቁሰገብ አይደለችም። ፈፅሞ። በገብያ ህግም አትመራም።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"


 
ከልብ ሆናችሁ ታነቡት ዘንድ በትህትና እገልፃለሁ። ከእርዕሱ ጋር ተያያዥ ዬሆኑ አመክንዮችንም አነሳለሁ።
ሄሮድስ አብይ አህመድ አሊ ያደረጉትን ንግግር ለሦስተኛ ጊዜ ዛሬ አዳመጥኩት። ለእኔ #ብሄራዊ የሆነ #አስቸኳይ #ጊዜ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ላይ #ዓውጀዋል። የኮማንድ ፖሱቱም ቲም፤ መሪም እሳቸው እንደሆኑ ተረዳሁኝ። ቃልበቃል፤ ሥንኝበሥንኝ ዬመታበይ፤ ዬማናህኝነት ዬምፃዕት ማት ነው ዬወረደው። ሊያለማምዱ ዬፈለጉትም ሁነት አለ። ዬገዘፈ ግድፈት ህፃጽ አመክንዮ።
፩)
#ዬኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ሲኖዶስ፦
#ዬኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት #መንበረ ፓትርያርክ፦
#ዬኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት #ፓትርያርክ
#ዬኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት #ቤተክርስትያን
#ዬኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት #ዶግማ
#ዬኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት #ቀኖኖ
እንዲህ ሊገለጽ ሲገባ የፊቱን እና የማህሉን ነጥለውታል። ክብሮቼ እናንተም እንዳትጠለፋ ይህ ድፍርስ ማዕበል እንዳይውጣችሁ አጥርታችሁ ፃፋ፤ አሟልታችሁ ተናገሩት። እኔ ዬቁም ንባቡን ነው እምጽፈው። ትርጉም እና ሚስጥራቱ ለእኔ ዬተገባ ስላልሆነ፤ ስላልተሰጠኝም ለዕድምታ ሊቀ - ሊቃውንት ልተወው። እነሱ ይፈቱታል።
ዬኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን
#----------? "ኦርቶዶክስ" #----- ? "ሃይማኖት" ነው ያሉት።
ዬኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ነው መጠሪያዋ ቅድስት ዕምነታችንም፦ ቤተክርስትያናችን። ዬንጉሦች ንጉሥን ዬዓጤ ሚኒሊክንቤተ መንግሥት "አንድነት" እንዳሉት ለእኛም ሥም ለማውጣት ዳር ዳር እያሉ ነው። የሚገርመኝ ድፍረታቸው እና የሚንጠራሩበት ጣሪያ ነው።
ይህ እንደለመዱት "መጤ፤ ጁንታ፤ ዬቀን ጅብ" እያሉ እዬተቀበለ ዬገደል ማሚቶ ለሚሆንላቸው አዲስ ቦይ መቅደዳቸው ነው።
#በኦርቶዶክስ ሃይማኖት
እና
#በኦርቶዶክስ #ተዋህዶ ሃይማኖት መካከል ያለውን ዕድምታዊ አመክንዮ ደፍጥጠው ነው ያቀረቡት።
#ኢትዮጵያ ዬሚለውን ገናና የቃለወንጌል ዬተጋድሎ ዓርማን ሥያሜም ተጠይፈውታል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ነው መጠረያዋ ቤተእግዚአብሄራችን፤ ዕምነታችን። ሆን ብለው እንዳደረጉት ይሰማኛል። #ተዋህዶ ዬሚለውን ነጥለዋል። #ኢትዮጵያ ዬሚለውንም ነጥለዋል። ዬፊቱን እና ተከታዩን ( Prefix and Suffix)መጠሪያ እንደ ዶሮ ገነጣጥለው ነው ያቀረቡት። ከፍተኛ ትርምስ ነው የፈጠሩት። #ዬጥሰት #ጎርፍ። ያቋቋሟቸውም እስከሚገባኝ የኦሮምያ እና የብሄር ብሄረሰቦች ተብለዋል። "#ኦርቶዶክስ" ብቻ እንዲባሉም ዬተለመ ይመስለኛል።
ይህምብቻ አይደለም በክልሎች ልክ ለመሸንሸን አስበዋል። ደቡቡን #እንደመተሩት
ሌላ " ሁለቱ ጉሩፕ" ነው ያሉት። ይህ ድፍረት ዬት እንደሚያደርሳቸው ዬላይኛው ይዳኜው። የኳስ ይሁን የሩጫ ጉሩፕ አይታወቅም። የዘመቻ ይሁን የፓርክ ጉሩፕወይንም ዬጉዞ ጉሩፕ እንዴት ቀሏቸው እንደሚያዋርዱት በጥሞና እዩት።
ቀናዒ ልቦና እና ህሊና ያላችሁ ወገኖቼ በጥሞና ሆናችሁ ሳትበሳጩ አዳምጡት ደጋግማችሁ። ንደት፤ ጥሰት ነው የፈፀሙት። ዬኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን #ቁሰገብ አድርገው፤ በገብያ ህግ እንደምትተዳደር አድርገው ነው ያቀረቡት። በትዕግስት ስታዳምጡት እንጥፍጣፊ የመሪነት፤ ዬአስተዋይነት ንጥረ ነገር አታገኙም። ይልቁንም በሙሉ ኃይላቸው ወረራ፤ ድጠት፤ ጭነት ለመፈፀም ሙሉ ዬአካልም ዬመንፈስም መሰናዶ እንዳደረጉ ተረድቻለሁ። የሚሊተሪ ልምምዱም ለዛ ይመስላል። በዋዜማው ነበርና።
፫)
የፖለቲካ ዝንባሌ ዬሚሉት ነገር። ቢኖርበት እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ዘው አልልበትም ነበር። ሂደቱን ከ2010 ጀምሮ ስለተከታተልኩት እና የዘመኑን የፖለቲካ ባህሪ አስቀድሜ ስላዬሁት የህሊና ወረራ - ነቀላ ተከላ፤ ዬመንፈስ - ነቀላ እና ተከላ፤ የታሪክ ሽሚያ፤ የኮፒ ራይት ጥድፊያ ዘመቻው እንደሆነ አውቃለሁኝ። ብቻቸውን ብቻም እንዳልሆኑ አስባለሁ። የገቡት ቃል አለ። ያን የመፈፀም፤ ዬማስፈፀም ሂደት ነው። ህዝብ የመቀነስም ፕሮጀክት አላቸው።
ዬኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ከምንም እና ከማንም ነገረ ፖለቲካ ድርጅት መሻትም ዬላትም። ጉዳዩ እንደ በግ ሊነዷት፤ ሊጭኑባት፤ ሊወጧት በጠራራ ጠሐይ ሊወሯትስለ አሰቡ፤ እያስፈፀሙም ስለሆነ ከመንግሥት የባህል እና ዬቱሪዝም ምደባ ጀምሮ የከወኑትን እናውቃለን። በሌላ በኩል ቅይጥ፤ ዝንቅንቅ አስተምህሮ ዋጪ ነው፤ ግን ልትቀበል አትችልም። የራሷ ሰማያዊ ራዕይ አላትና። ቀደምት ናት። አቻም ወደርም ዬላትም። የሚያዳብላት፤ ውራጅ ፍለጋ የሚያማስናት አንዳችም ነገር ዬለም። #ሙላት ናትና።
፬) በካቢኔው ውስጥ በርከት ያሉ የሴት ሊሂቃንን አዬሁኝ። መልካም ነገር ነው። የእስልምና ዕምነት እህቶቼ ከእነ ሙሉ ሃይማኖታዊ ክብር አዬሁኝ። ቀሪወቹ ላይ አንድም ማተብ ያላት እህት አላዬሁም። ይህ ማለት በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት በዚህን ያህል ዘመን አንዲት የካቢኔ አንስት አባል ማፍራት አልተቻለም ማለት ነው። ተተኪ ለማፍራትም ልሙጥ ነው። ተተኪወች አብነት ይሻሉና። የአማራ ሴት እጩ ሊቃናት በደንቪደሎ ሲታገቱ የአማራ ወላጆች ሴት ልጆቻቸውን ለትምህርት እንዳይልኩ ለማሸማቀቅ፤ መቀጣጫ ለማድረግ ነበር። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትም ይህ በደል ትውልድን ያመክናል።
እኔ በዓለም ዓቀፋ ማህበረሰብ፤ በአህጉራዊ ድርጅቶች፤ በአገሮች በጽናት ስታገል ዬኖርኩት ስለ ድምጽ አልባወቹ ዬኢትዮጵያ እናቶች ነበር። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዬገበርዲን እና የሱፍ ነው። ስለዚህ ዬኢትዮጵያ እናቶች ለዕንባ ዘመን ተዳርገዋል ነበር። በፖለቲካ አቅም ዬሚመክቱ ሚዛን ዬሚያስጠብቁ እህቶች ይኖሩኛል ብዬ አስብ ነበር።
ለምን 50% ካቢኒያቸውን ዶር አብይ እንዳደረጉትም ያውቁታል። ሴቶች 50% ሆነው አዬኋቸው። መጀመሪያ ደስ አለኝ። መሬት ላይ ግን ተጋድሎዬ አላተረፈም። ጭራሽ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስማ መላጣ፤ ወና ዬሆነ ገጠመኝ ነው ያስተዋልኩት። ቢኖሩም ባይኖሩም ኡስ ትንፍሽ እንትሉ ተብለው በሚመሩት ህዝብ ሲዋረዱ፤ ሲሳቀቁ ማዬትም ህመም ቢሆንም፤ ድካሜ ጥቅመ ቢስ ቢሆንም፤ የዶር አብይ አህመድ ስልታዊ፤ ረቂቅ ጉዞ ግን ማስተዋል ችያለሁኝ። በሁሉም ዘርፍ የጠሉትን ማፅዳት።
፭) በማግሥቱ ህወሃትን ሊያገኙ ብፁዑወቅዱስ ፓትርያርከ ዘኢትዮጵያ አባታችነን ደጋግመው አነሱ። እዬጎመዘዛችው። "እምመክረው እንደ አባ ማትያስ ሁኑ" ቦሌ አውሮፕላን ምን አደራጅተው ምን እንደፈፁሙ ህሊናቸው ያርቀዋል። ሙሉ ፭ ዓመት ውሎው ቀራንዮ ነበር። ብቻ ግን አረንዛ ሰብዕና ገፁ እና ጭብጡ ገፀ ባህሬው እና ውስጠቱን አስተዋልኩበት።
#ዕርገት ይሁን።
ሁሉንም አድቅቀው ምርኮኛ እንዳደረጉት ያውቃሉ። ተፅዕኖ ፈጣሪውን ሁሉ አሟምተውታል። አዲስ ማዋለድም አልተቻለም። ቢፈጠርም ይሸኛል፤ በአሁኑ ሰዓት እንኳንስ ተቀናቃኝ የፖለቲካ ድርጅት ጉልበታም የጠራ የፖለቲካ መስመር፤ የተደራጀ ሃሳብ በሌለበት መፈንቅል እያሉ ባይባትቱ ጥሩ ይመስለኛል። ከፈነቀሏቸውም ማህበረ ኦነጎች ቤተኞቻቸው ይሆናሉ። ከላይ እሰከ ታች ቲፍ ያደረጓቸው። ያው ለመጨባረቅ።
ውዶቼ ሂደቱን ተጠሙናችሁ አዳምጡት ስል በትህትና አሳስባለሁኝ። አትበሳጩ። እንፀልይ። ፈጣሪ ይርዳን። ደግ የሆነ ለስላሳ ፆመ ነነዌ ይሁንልን። አሜን። ዮናስን ከዓሳ ነባሪ ያወጣ አምላክ ቅድስት፤ ክብርት፤ ርህርህት ቤተክርስትያናችን ከዘመነ ደራጎን ያውጣት። አሜንወአሜን።
ወስብኃት ለእግዚአብሄር።

 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
05/02/2023

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።