ልጥፎች

ሃይለመድህን አበራ።

ምስል
        የጀግና ውለታው ሁልጊዜም ያሰበለ ነው።                    ተግባሩም ምንጊዜም መሪ ነው                  ከሥርጉተ – ሥላሴ 11.04.2018 ( ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ) „ የእግዚአብሔርም እሳት ወደቀች፣ የሚቃጠለውን ምሥዋዕቱንም እንጨቱንም ድንጋዮቹንም አፈሩንም በላች፣ በጉድጓዱ ውስጥ                   ያለውን ውሃም ላሰች ( መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ ምዕራፍ ፲፰ ቁጥር ፴፰ እስከ ፴፱ “) ጀግናዬን ሳስበው። እንዴት አላችሁልኝ ውዶቼ የሐገሬ ልጆች፣ —- ዛሬ ላይ ሆኜ ጀግናዬን ሳስበው ይህቺን የብርሃን ማዕለት ለማምጣት ነበር ያን ያህል ማይልስ ርቆ ሰማይን ቀዝፎ፤ ጉሙነን ተሻግሮ መነኮሲያዋን ሲዊዝን ራፊ፤ ብጣሽ፤ የሰላም መሬት የጠዬቀው። በሐገሩ መቀመጫ በማጣቱ፤ በሐገሩ በመሳዳዱ ምክንያት። ይህ ጀግና አዬር ላይም ባልተለመደ ሁኔታ በሌሎች ሐገሮች ተመሳሳይ አውሮፕላን ታጅቦ ነበር መሬት ላይ ያረፈው። አፈፃፀሙም ዓለምን በእጅጉ ያሰደደመመ ነበር። እትዮጵውያን አርበኝነታቸውን በባእድ ሐገር ሲፈጽሙ አምደ እርሰ ጉዳይ ሆነው...