ደስ ይበልህ ጐጃም።
ደስ ይበልህ ጐጃም። ከሥርጉተ ‚ ሥላሴ 09.06.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። „ብርና ወርቅ አገር ያጸናሉ፤ ከሁለቱ ምክር በ ጐ ምክር ደስ ታሰኛለች።“ (መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፵ ቁጥር ፳፭) የሁነኛ ማተብ የመሆን አብነት የልብ አድርስ ኑሮ፤ የህሊና ባዕት የቁርጥ ቀን ግማድ የመሠረት ጽናት፤ ደስ ይበልህ ጎጃም የኪዳን ጉልላት! ጐ ትንግርተኛው የሰማይ ቅስቱ የአማራ ምስባኩ የናፍቆት ስስቱ ዕውቅናው ፈለቀ በገዱ በእትብቱ። የደምመላሽ አንቱ የአድባራት ቅኝቱ፣ የበካፋ ህይወት የአድም ሰገድ ጥሪኙ የጥንት የጥዋቱ የንግሥ ቱሩፋቱ፤ ዘመኑን አጎላው በውስጥ ሽልማቱ። እስኪ ልጠይቅህ „ጣና ሆይ!“ ሚስጢርህ ምንድነው? እስኪ ልጠይቅህ „ግዮን ሆይ!“ ሚስጢርህ የቱ ነው? የተመሰጠርከው በህብሬ ደማሙ ፈቅደህ የሰጠኸው፤ በጨለመበት ለት፣ ሁሉ ፊት ሲነሳው፣ ...