ልጥፎች

የክብርት ቀዳማዊት እማቤት ርህርህና ከህሊና ነው።

ምስል
„ድህነትን ባንቀበለው ደስ ይለኛል - ዕንባ እዬተናነቃቸው። „አቤቱ እናመሰግንህአለን፤ እናመስግነሃለንነ፣ ስምህንም እንጠራለን፣ ታአምራትህን ሁሉ እናገራለሁ። ገዜውን ስቀበል እኔ በቅን እፈርዳለሁ።“   (መዝመረ ዳዊት ምዕራፍ ፸፪ ቁጥር ፩)    ከሥርጉተ ©ሥላሴ 26.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።)   v መግቢያ። „ድህነትን ባንቀበለው ደስ ይለኛል“ ይህን እንባ እየተናነቃቸው የተናገሩት ክብርት ቀዳማይ እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው በህፃናት መርጃ አንባ ጎንደር ከተማ ለጉብኝ በተገኙበት በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ ነው። እርግጥ ነው ቀደም ብለው ሂደውበት በነበረው የባህርዳሩም ሆነ የጎንደር ጉብኝታቸው የቢዲዮ ቀረፃ ከፍተኛ ችግር አለበት፤ ድምጹን በትክክል መስማት አይቻልም፤ ፊልሙም የ17ኛው መቶ ክ/ ዘመን ምስጋን ይንሳው። ይህን የአማራ ማስ ሚዲያ በባለቤትነት ውሰዶ እንዴት ጥራት ያለው ተግባር እንደማይከውን ይገርማል።   ኦሮምያ ላይ የኦህዴድ የጽ/ ቤት ሃላፊ እና የመስተዳደሩ ምክትል ፕሬዚዳንት ሴቶች ናቸው ሁለቱም። የሚሰጣቸው ትኩረት ይህ ነው አይባልም። መልዕከቶቻቸው ጥረቱ እጅግ ይደንቃል፤ በሌላ በኩል የፌድራል ምክር ቤቱና የፓርላማው አፈ ጉባኤም ሁለቱም ሴቶች ናቸው፤ እነሱ በተገኙበት ቦታ ሁሉ የቀረጻ ሆነ የድምጽ ጥራት ችግር የለበትም።   የቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታዬቸው የተግበር መስክ ግን የግብር ይውጣ ነው። የኢትዮጵያ የመንግሥት ሚዲያ ሆነ ሁለት ጊዜ የተገኙት በክልሉ ነበር አጀንዳውም አልነበረም የአማራ የብዙሃን ሚዲያ ለዚህ ካልሆነ ለመቼ ሊሆን ይሆን? እጅግ ይገርማል።   ይህ እኮ የኢትዮጵያ ሴቶች አንጡ...