የክብርት ቀዳማዊት እማቤት ርህርህና ከህሊና ነው።

„ድህነትን ባንቀበለው

ደስ ይለኛል - ዕንባ እዬተናነቃቸው።

„አቤቱ እናመሰግንህአለን፤ እናመስግነሃለንነ፣

ስምህንም እንጠራለን፣ ታአምራትህን ሁሉ እናገራለሁ።

ገዜውን ስቀበል እኔ በቅን እፈርዳለሁ።“

 

(መዝመረ ዳዊት ምዕራፍ ፸፪ ቁጥር ፩) 

 

ከሥርጉተ ©ሥላሴ

26.07.2018

(ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።)



 

v መግቢያ።


„ድህነትን ባንቀበለው ደስ ይለኛል“ ይህን እንባ እየተናነቃቸው የተናገሩት ክብርት ቀዳማይ እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው በህፃናት መርጃ አንባ ጎንደር ከተማ ለጉብኝ በተገኙበት በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ ነው።


እርግጥ ነው ቀደም ብለው ሂደውበት በነበረው የባህርዳሩም ሆነ የጎንደር ጉብኝታቸው የቢዲዮ ቀረፃ ከፍተኛ ችግር አለበት፤ ድምጹን በትክክል መስማት አይቻልም፤ ፊልሙም የ17ኛው መቶ ክ/ ዘመን ምስጋን ይንሳው። ይህን የአማራ ማስ ሚዲያ በባለቤትነት ውሰዶ እንዴት ጥራት ያለው ተግባር እንደማይከውን ይገርማል።

 

ኦሮምያ ላይ የኦህዴድ የጽ/ ቤት ሃላፊ እና የመስተዳደሩ ምክትል ፕሬዚዳንት ሴቶች ናቸው ሁለቱም። የሚሰጣቸው ትኩረት ይህ ነው አይባልም። መልዕከቶቻቸው ጥረቱ እጅግ ይደንቃል፤ በሌላ በኩል የፌድራል ምክር ቤቱና የፓርላማው አፈ ጉባኤም ሁለቱም ሴቶች ናቸው፤ እነሱ በተገኙበት ቦታ ሁሉ የቀረጻ ሆነ የድምጽ ጥራት ችግር የለበትም።

 

የቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታዬቸው የተግበር መስክ ግን የግብር ይውጣ ነው። የኢትዮጵያ የመንግሥት ሚዲያ ሆነ ሁለት ጊዜ የተገኙት በክልሉ ነበር አጀንዳውም አልነበረም የአማራ የብዙሃን ሚዲያ ለዚህ ካልሆነ ለመቼ ሊሆን ይሆን? እጅግ ይገርማል።

 

ይህ እኮ የኢትዮጵያ ሴቶች አንጡራ ታሪካችን ነው። የኢትዮጵያ ቤተ መንግሥትም ታሪክ ከመሆኑም በላይ የነገ የትውልዱ መሠረት ልዩ ተልዕኮ ነው። እጅግ ከምር አዝኛለሁኝ።  

 

ኦህዴድ በሁሉም ዘርፍ በ100% ይመራል፤ በሁሉም መስክ ብአዴን ደግሞ ያፏሽካል። ቢያንስ ይህን ኮኦርድኔት ለማድረግ እንዴት ይሳናል? ታሪኩን ድርጅቱ ዛሬ መጀመር ካልቻለ መቼ? ያሳፍራል። የተሰጠው ትክዩረትም ከዜሮ በታች ነው።
  • ·       የታደለው የኢትዮጵያ ቤተመንግሥት።

የኢትዮጵያ ቤተ መንግሥት እጅግ የታደለ ነው። እጅግ በቀደመው ጊዜ ቢሆን ከሁለት አንስቶች በስተቀር ሁሎችም እጅግ ጨዋ የነበሩ፤ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉልህ ሚና የተጫወቱ፤ በውጪ መንግሥታትም ቀድመው የዴፕሎማሲ ሥራ የሠሩ፤ ለስኬትም የበቁ ነበሩ።

የውጪ መንግሥታትም ከተብዕት ነገሥታት ይልቅ ለአንስታት ሰፊ አትኩሮት የነበራቸው፤ በዛው ልክም የሴቶችን ውሳኔም የሚያርዳቸው እንደ ነበረ ዝክረ ታሪካቸው ይነግረናል።

በ19ኛው መቶም ክፍለ ዘመን በዐጤው ዘመን የነበሩት አንስቶችም እንዲሁ ብቁ እና ንቁ፤ አብዝቶ ፈርኃ እግዚአብሄር የሚያጠቃቸው ስለመሆኑ መዋለ ንግሥናቸው ይገልጣል።

በዚህ በእኛ ዘመን ካዬናቸው ውስጥ ባልተገባ ሁኔታ ቤተመንግሥቱን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን አንስት የፖለቲካ አቅም፤ የሞራል ደረጃ ዝቅ ያደረጉት  ወ/ሮ  ሄሮዳይድ የሄሮድስ መለስ ዜናው ባለቤት አከርካሪ ወ/ ሮ አዜብ መስፍን ብቻ ናቸው። እሳቸው ቅርስም፤ ውርስም ሊሆን በማይችል ሁኔታ የበላይነት ዘመናቸው ከንቱ ሆኖ ተጠናቋል፤ ለዛውም በለነቆጠ ጥቁር ታሪክ ተዥጎርጉሮ።
  • ደልዳዋ እመቤት!

ቀደም ባለው ጊዜ ደልዳዋ እመቤት ክብርት ወ/ሮ ውብአንቺ ቢሻው የአደባባይ ሰው ባይሆኑም ሚስትም፤ እናነትም መሆን የሚለውን የፈጣሪን ጸጋ እና በረከት በሙሉ አቅሙ የተረጎሞ ስለመሆናቸው ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚስማማበት አምክንዮ ነው። ድምጻቸው ሳይሰማ ኖረው ድምጻቸው ሳይሰማ ነበር የተሰደዱት።

እርግጥ ነው በነበረው ሥርዓት ውስጥ የነበረውን ወጣ ገብ የፖለቲካ ምስቅልቅል  መልክ ለማስያዝ፤ ሚዛናዊ ለማድርግ የነበራቸው የፖለቲካ ተሳትፎ ምንም ስለነበር፤ በክፉም በደጉም የሚነሱበት አንዳችም ነገር አልነበርም።

በባለቤታቸው በኮ/ መንግሥቱ ሃይለማርያምም ቤተሰቦች ዘንድ ግን እጅግ የተከበሩ እና የሚወደዱ እንደ ነበሩም፤ በተለያዩ ቃለ ምልልሶች ላዳምጥ ችያለሁኝ። ክብርት ውብአንቺ ቢሻው የአደባባይ ሰው ሳይሆኑ እውነተኛ ሚስት እና እናት የቤት ልጅ እንደ ነበሩ ያሉት መረጃዎች በሙሉ ይመሰክራሉ። በዚህ ዘርፍ ማለትም ቤተሰብ በመምራት እና በማስተዳደር ልዩ መክሊት እንዳላቸውም ተዘውትሮ ይገለጻል።

በኢትዮጵያ በቀደመው ባህል መሰረት ባለቤታቸውን „እርሰዎ“ ብለው አክብረው፤ ብድግ ቁጭ ብለው የሚያስተናግዱ የትዳር ልዕልት፤ እምቤትም ናቸው። ባለቤታቸው በእሳቸው እጅ በተመጠነ መሰናዶ መባም ነው የሚኖሩት እንደ ውስጥ አዋቂዎች ገለጣ።

የቤተ መንግሥት ኑሯቸው እጅግ ዝቅ ያለ እንደ ነበረ ከሰሞናቱ የቤተ መንግሥት ጎብኝ አርቲስቶች ቃለ ምልልስም አዳምጫለሁኝ። ስለዚህም በምንም የሥነ - ምግባር ግድፈት የቤተ መንግሥቱን ቅርስ እና ውርስ ትውፊትም አላስጠሩም። ጨዋነታቸው ትውፊታችንም ነው።
  • ·       የመፍትሄ ቅኔ።

ሌላዋ ክብርት ወ/ሮ  ሮማን ተስፋዬ ሲሆኑ እሳቸውም ቢሆኑ በቀለም ዕውቀት የተማሩ እና በቤተሰብ አማራር እና አስተዳደር ሚስት በመሆን አቅም፤ ለልጆቻቸው እናት በመሆን አቅም ላይ ብቁ ሴት እንደ ነበሩ መረጃዎችን ስከታተል ቆይቻለሁኝ። ልጆቻቸው የደረሱበትን ቁምነገርም የክብርትነታቸው ታላቅ ድርሻ ስለመሆኑ አመናለሁኝ።  

አብሶ በዚህ በበጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ የልብ የሆነ ተግባር በመከወን ላይ እንደ ነበሩ ቤተ መንግሥቱን ሲለቁ በነበረው መረጃ በዝርዝር ለማወቅ ችያለሁኝ።

ከሁሉ በላይ ሽግግሩ ሰላማዊ እንዲሆን፤ የባላቤታቸውን የቀድሞው ጠ/ ሚር አቶ ሃይለማርያም ደስ አለኝ ሥነ - ልቦናን በማዘጋጀት እና በማስወሰንም እረገድ እንደ ሴት እኔን እንደሚገባኝ ወሳኙን ሚና ተጫወታዋል ብዬ አምናለሁኝ።

ስለሆነም ለኢትዮጵያ ህዝብ ያለተነገራላቸው ታላቅ የመፍትሄ ቅኔም ናቸው። ሁልጊዜም እኔ አሳስባቸው ነበር። እባካዎትን ባለቤተዎትን ይርዷቸው እና ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው እንዲለቁ ያድርጉ እያልኩኝ። ምክንያቱም አቅም እና ፍላጎት ባለመመጣጠን የመከራው ሰንሰለት ከዕለት ዕለት ስለተበራከት።
የሆነ ሆኖ በዛ ሰላማዊ የመንግሥት የሽግግር ጊዜ ያሳዩት ሙሉ ሥነ - ምግብር እና ቅንነት የበለጠ ቀዳማዊ እምቤትነታቸው ጎልብቶ ለሁልጊዜ በልቤ እንዲቀመጥ አድርጎልኛል። 

ፍጹም የሆነ ጨዋነት፤ ፍጹም የሆነ ሞራላዊ ትህትና፤ ፍጹም የሆነ ፈቃድ እና መቀበል፤ ፍጹም የሆነ አዎንታዊነት ነበር ያዬሁት የሽግግሩን ሆነ የእርክክቡ ሥነ ምግባራዊ ሂደት እና እድምታው።

ክብርት ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ ከምንም አልቆጠሩትም ነበር ቤተ - መንግሥቱንም ሆነ ቀዳማዊነትን ለመልቀቅ። በዚህ ሂደት ታሪክ የማይረሳው ታዕምራዊ ተልዕኳቸውን ፈጽመዋል። Proud!

ያን የመከራ ዘመን ለማሳልፍ ጽናትን ይጠይቃል፤ መወሰን ከባድ ነው። ባለቤታቸውን በሙሉ አቅም አሳምነው፤ ሥልጣን እንዲለቁ ማድርግ ብቻ ሳይሆን ሥልጣናቸውን ከለቀቁ በኋዋላም በሙሉ ሰብዕናቸውን ሳይታመሙ፤ ሳይጎሳቁሉ ማስቀጠልም ሌለው ጉዳይ ነው።

እንዲያውም አዲስ ፋውንዴሽን እንደሚከፍቱ በጋራ አዳምጫለሁኝ። በዚህ ላይ እንደ እኔ ምኞት እና ተስፋ ሥልጣናቸውን ደስ ብለው ስለለቀቁ ሞዖ ኢብራሂም ፋውንዴሽን ለዚህ ዘመን መርጦ ይሸልማቸዋል ብዬም አስባለሁኝ።

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ትበልጠኛለህ፤ እኔ ብለቀው የተሻለ አቅም እና ዕድል ያለው አገሬን ኢትዮጵያን ይምራ ማለት ፈጽሞ በህልም እንኳን ታስቦ አይታወቅም። ያን በመሰለ ሳቅ እና ፈግግታ፤ በሙሉ ሐሤት ቤተ መንግሥታዊ ክብርን መልቀቅ በኢትዮጵያ የታዬው የዘመን ገድል ነበር።

ከዛ በቀደመውም ዶር ለማ መገርሳ፤ ዶር አብይ አህመድን ወደ ፊት ያመጡበት መንገድ፤ ከዚህ ሌላ አቶ ደመቀ መኮነን እራሳቸውን ከእጩ ጠ/ ሚር ለማግለል የወሰዱት ቆፍጣና እርምጃ፤ የላቀው የኢትዮጵያ እዬራዊ ታሪክ ነበር። ይህ ክንዋኔ ለታሪካችን አዲስ ምዕራፍ ብቻ ሳይሆን አዲስ ዘመን ላይ እንዳለን ያበሠረ ሙሉ ወቄታም ዕንቁችን ነው። ፈጣሪ ያስቀጥልልን እንጂ …

የቀደሞው ጠ/ ሚር አቶ ሃይለማርያም ደስአለኝ ለአዲሱ አመራር ያላቸው ቀጣይ ቅናዊ ዕሳቤ እና ዕድምታ በዚህ ዘመን የሆነ ነው ወይ ብሎ ለማመን ይቸግራል። ሌላው ይህን  አዲስ ተስፋ ለመንቀል፤ ለማጎሳቆል፤ ጥቁር ልብስ ለማልበስ ይተጋል፤ እሳቸው ደግሞ ህይወቴን እሰጥለታሉሁኝ ይላሉ። እውነት ለመናገር ይህ ትውልድን የሚያስተምር ልዩ ተቋም ነው።

  • ·       ክብረትን በፈቃደኝነት ሲለቁ እንደ አዱኛ ስለመቁጠር … 

ከሁሉም የከበረው ጉዳይ ደግሞ አዲሱ የቤተመንግሥት ቤተሰብም ጋር ጤናማ ግንኙነትን ማስቀጠል ሌላው የብልህነት አድማስ ነው። ለዘመናች የተሰጠ ልዩ ሽልማትም። ኮሽ ያለች ነገር አልተደመጠም።

እጅግ በሚገርም፤ እጅግም በሚመስጥ፤ እጅግም በሚያስመካ ሁኔታ ነበር አፈጻጻሙ የተከወነው። በሳቅ፤ በደስታ፤ በፍሰሃ፤ በቤተሰባዊነት ስሜት። ይህ የወ/ ሮማን ተስፋዬ አብነታዊ ጉዞ ውርስና ቅርስ ነገም ይሆናል ብዬ አስባለሁኝ። ይህ አቅም ምንጩ ከወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ የተቀዳ ነው ብዬ አስባለሁኝ።
  • ·       አዲሷ ቀዳማዊት እመቤት እቴጌነት እርጋታ እና ዕሴታዊነት!

ቀደም ብዬ መግቢያው ላይ እንዳወሳሁት፤ ከሰሞናቱ ክብርት ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ጎንደር ለግብረ ሰናይ ጉዳይ ነበሩ። ቀዳማዊት እምቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ከወ/ሮ በላይነሽ ደምለው እና ከአባታቸው አቶ ታያቸው ብሬ ጎንደር ከተማ እንደተወለዱ፤ እናታቸው በህይወት እንደሌሉ ሲገልጹ፤ ከ1ኛ እስከ 5ኛ ት/ ቤት ከተማሩበት ት/ ቤት ሲገቡ ሟች አናታቸውን ወ/ሮ በላይነሽ ደምለው እንዳስታወሱ ገልጸዋል። ዕንባዬን መቆጣጠር እስኪያቅተኝ ድርስ ነበር ፈተናው።

ዘግይቼ እንጽፈውም የፈቀድኩት በዚኸው ምክንያት ነው። ዕንባዬ ተግ እስኪልልኝ ድረስ። ችግር አለብኝ። ሆዴ ቡቡ ነው። አሁን እኔን የሚያውቅ ሰው ለዚህን ያህል ዘመን እንዲህ ተለይቼ ብቻዬን መኖሬን ሲያስበው የሚያምነው አይሆንም።
  • ·       ምራቁን የዋጠ ሰብዕና ለእኔ።

እኔ ምራቁን የዋጠ ሰብዕናን የምወደው እርጋታውን - ስክነቱን ደልለዳነቱ ነው። ከእኒህ እመቤት የፈለግኩትን ሙሉውን አገኝቻለሁኝ ብዬ አስባለሁኝ። እኔም ብቻ ሳልሆን በኢሜልም፤ በስልክም እማገኛቸው የእኔ መስል ስሜት ያላቸው መሆኑን ጓደኞቼ ገልጠውልኛል። ቤተሰቦቼን ውጪ ያሉትንም ስንገናኝ ይህንኑ አንስተን እንጫወታለን።  Proud!

አብሶ ለሴት ልጅ ይህን መሰል ሰብዕና ስጦታ ነው። ወደ አምስት ጊዜ ሚዲያ ላይ አዬዋኋቸው፤ እርጋታቸው ይመስጣል። በልክ ነው የያዙት። ሁልጊዜም አንደበታቸው ሲከፍት „ከእግዚአብሄር ጋር፤ እግዚአብሄርም ይረዳናል“ አይለያቸውም። ይህ መቼም መታደል ነው። መታመንን ለፈጠረ መስጠት። የሰጠን መታመንን ማክብር። በመታመን ውስጥ ሰጭውን ተስፋ ማድረግ። 

እርግጥ ነው ቀደም ብሎ ከወጣው መረጃ እንደተረዳሁት ከዚህ ቤተመንግሥታዊ ሥርዓት ጋር ስለማደጋቸው ፍንጭ አግኝቻለሁኝ። ሰብዕናቸውም የተመቼ ነው። እና ልዑል እግዚአብሄር በሁለቱም በባላቤታቸው በባለቅኔው ጠ/ ሚር አሜኑ አብይ አህመድ በኩል ሆነ በክብርት ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው አንገታችን እንዳንደፋ አድርጎ ባርኮ አመቻችቶ ሰጥቶናል። ተመስገን!

Ethiopia: የቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ ቤተሰብ ሙሉ የጎንደር ቆይታ እና ንግግር

  • ·       ቊጥብንት

ለአንዲት አንስት ውበቷ ትልቁ ጸጋዋ  ቊጥብነቷ ነው። በዚህ ሰብዕና ውስጥ ብዙ ነገር ማትረፍ ይቻላል። ከሁሉ በላይ አዲሱን ትውልድ በሞራል በመገንባት እረገድ እናት የመጀመሪያዋ የህይወት ት/ ቤትም፤ መምህርም ስለሆነች ለነገም ተስፋን ያሰንቃል። የነገ ነገር ዋና መሠረቱ ቤት ስለሆነ።
  • ·       ርህርህና!

ርህርህና የሰው ልጅ በተፈጥሮ የተሰጠው ነው። ለሁሉም በእኩልነት። በፆታ የሰማይ መንፈሳዊ ጸጋዎች አይለኩም። እርግጥ ነው የርህርህናው አፈጸጻም እና አገላለጽ ሊለያይ ይችላል። ርህርህናን በመቀበል ፍጥነት እና ሂደትም እንዲሁም መበለላጥ ሊኖር ይችላል። ነገር ግን እንደ ጸጋ ለሁላችንም እኩል የተሰጠን የቸርነት አንባ ነው ርህርህና። 

ቀዳማዊት እመቤት ባዩት ነገር እጅግ ውስጣቸው ተጉድቷል። ድህነታችን ምን ያህል ውሰጣችን እንደበደለው አሳዝኗቸዋል። ለዚህም ነው "ድህነትን ባንቀበለው ደስ ይለኛል" ከዛ ለመወጣት ተጋድሏችን እንቀጥል የሚሉት። ርህርህት ናቸው ለዛውም በውስጥ፤ ከውስጥ፤ ከመንፈስ ከህሊና። በዛን ሰሞን ባህርዳር ላይ የርህርህና ተምስጦ አዩሁኝ፤ ዛሬም እንዲሁ። ጥሞና ያለው ርህርህና እድምታ ያለው ሆደ ሰፊነት መታደል ነው። 

ቀደመው ባለው ሰሞናትም ክብርት ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው በባህርዳርም ተገኝተው ነበር። ለተመሳሳይ ሰብዕዊ ተግባራት። እዛም ርህርናቸውን ጉንብስ ብለው ልጆቻውን ሲያስተናግዱ ተመልከቻለሁኝ።

„ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የተቀደሰ ተግባር ማከናወን ጀመሩ“

 

ፈጣሪ አምላክ ይህን ተልዕኳቸውን ያስቀጥል ዘንድ ህይወታቸውን ይጠብቅልን። ምክንያቱም እኔ ተጀምሮ እስኪጨረስ ድረስ ፍርሃት አለበኝ። ሴራ የኢትዮጵያ እናቶች ተስፋ ቀመኛ ስለሆነ። ሴራ የኢትዮጵያ ሚስቶች ፈግጋታ ቀማኛ ስለሆነ፤ ሴራ የኢትዮጵያ ልጆችን ራዕይ ቀማኛ ስለሆነ።
  • ·       „ድህነትን ባንቀበለው ደስ ይለኛል።“

ይህንን ቃል ክብርት ቀዳማይ እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ከ1ኛ እስከ 5ኛ በተማሩበት ት/ ቤት ውስጥ በጎንደር ከተማ የገለጹት ነው። ሲናገሩት ዕንባ ያንቃቸው ነበር። „ድህነትን ባንቀበለው ደስ ይለኛል“ ሲሉ በቋሚ ተረጅነት ሳይሆን ተረጅነትን በዘላቂ ፈቶ ራስ በሚያስችል ተቋማት ላይ ትጋት እና ጥረት ይኑረን መለታቸው ነበር።

ክብርት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ንግግራቸው የተመጠነ አጭር ነው ሁለት ሦስት ስንኝ ነው፤ ግን በነገሮች ሁሉ ፍሬ ነገሩ ሲመረመር ከ6 ሰዓት ንግግር ወይንም ከአንድ መጸሐፍ በላይ የአመክንዮ አቅም አለው በልብ ውስጥ ለመቀመጥ።
የንግግራቸው ጭብጥ በአንዲት ስንኝ ውስጥ ሆኖ፤ ግን ጉልበቱ ህሊናን እንዲፈትሽ ለመፍቀድ፤ አርቆ ማስብ እንዲቻል ስለማስገደድ፤ ዜግነትን በመቀበል ብቻ ሳይሆን ትውልዳዊ ድርሻን በቋሚነት ስለመወጣት ታላቅ ተልዕኮ አለው ንግግራቸው።

ንግግራቸው ቤተሰባዊም ነው። ተፈጥራዊም ነው። ከልብ ይገባል። ሰፊ ህልም እና ምኞት አላቸው፤ ራስን ስለመቻል፤ ከጥገኝነት ስለመውጣት፤ ስለመርዳት እና መረዳዳት፤ ስለማገዝ እና መተገጋዝ አብሶ አካላቸውን በተለያዬ ሁኔታ ላጡ ህፃናት ቅርብ ያለ መንፈስ አላቸው።

ፈገግታቸው ውስጣዊ እና በማቅርብ በትሁትናም ነው። አክብሮታቸውም ልባዊ ነው። ልዑል እግዚአብሄር  የኢትዮጵያን አመድ ምሰሶ የሆኑትን ባለቤታቸውን ባለቅኔውን ጠ/ሞር፤ እሳቸውንም ያኑርልን። አሜን! መልካም ማሰብ፤ መልካም ለመሆን መፍቀድ፤ መልካምነትን ማውረስ ከምርቃት የሚገኝ ነው።

ስማቸው እራሱ ትንቢት ያለው የነብያት ሥም ነው። „ዝናሽ ታያቸው“ ይገርማል። ቤተሰቦቻቸው ምን ታይቷቸው ይህን ሥም እንዳወጡላቸው ይገርመኛል። „የልጅ እና የጭስ መውጫው አይታወቀም“ እንዲሉ ነው የሆነው። „ሥምን መላዕክ ያወጣዋልም“ ብቻ ሳይሆን „ባል እና ሚስት ከአንድ ወንዝም“ እንዲሉ ነው …

እርጋታን በሚመለከት የመጀመሪያ ልጃቸውም ሰከን ያለ መንፈስ እንዳላት ለማሰተዋል ችያለሁኝ። መጨረሻውን ያሳምረው …. አሜን!

v  ማከያ።
ይህን በግንቦት 24 ቀን በ2018 እጅግ ከማከብረው ሳተናው ድህረ ገጽ ላይ አግኝቼው ነበር። ዝርዝር መረጃ ስለሚሰጥ አብሬ አያይዤ ለጥፌዋለሁኝ። ቤተሰብ፤ አስተዳደግም የሚሰጠው የራሱ የሆነ የክህሎት ማዕዛ ስላላው፡፤ የክብርት ቀደማይ እመቤት የወ/ሮ ዝናሽ ታያቸውን የበለጠ በጥልቀት ወስጣቸውን፤ መሠረታቸውን ታገናዝቡት ዘንድ ለጥፌዋለሁኝ። በዚህ አጋጣሚ መረጃውን የሰጡንን ጸሐፍት እና መረጃውን ያገኘሁበትን የሳተናው ድህረ ገጽንም እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁኝ። የፊደል ግድፈትን እርማት እንኳን አላደረኩበትም እንዳለ ማቅረብ ግድ ስለሚል።

„ስለ ክቡር ደጃዝማች ብሬ ዘገየ (አባ በጥብጥ) አጭር ማስታዋሻ“

„ክቡር ደጃዝማች ብሬ ዘገየ የወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ብሬ አያት አገራችን ኢትዮጵያ ብዙ አገር ወዳድ አርበኛ ዜጎችን አብቃይ መሆኗ ይታወቃል፡፡ በተለይ 5 የፋሽስት ጣሊያን ወረራ ዓመታት አያሌ አርበኞች አገርን በመከላከል ሕያው ታሪክ ሰርተው አልፈዋል፡፡ ከነዚህ ብርቅ እና እውቅ ፋና ወጊ አርበኞች መሀከል ቁንጮው ክቡር ደጃዝማች ብሬ ዘገየ አንዱ ነበሩ፡፡ 
ክቡር ደጃዝማች ብሬ አገራችን ፋሽስት ጣሊያን በወረረበት ወቅት እምቢ ለነፃነቴና ለሀገሬ ብለው ወንድሞቻቸውን በማስተባበር  የጣሊያን ፋሽስት ሰራዊት እና ባንዶችን በጦርነት እንጂ በሰላም ላለማየት ወስነው በሚያዝያ ወር 1928 . . በረሀ ወረዱ፡፡
ወሳኙን ትግል ለመጀመር በመስከረም 1929 . .  ክቡር ደጃዝማች ብሬ ዘገየ ከአርማጭሆ ወደ ጠገዴ በመሻገር የፋሽስት ጣሊያን ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት ከኤርትራ  ተነስተው በሑመራ በኩል በሞተር ሳይክል እና በብዙ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ታጅበው ወደ ጎንደር ከተማ ጉዞ ላይ እንዳሉ ሹመሪ ላይ ሸምቀው ተኩስ በመክፈት የፋሽስቱን ሰራዊት ድል በማድረግ ወደመጣበት መልሰዋል፡፡ 
 በዚህ ውጊያ  የተለያዩ የጦር መኮንኖች ሞት እና ቁስለኛ ሲሆኑ፣ ብዛት ያለው የጦር መሣሪያ ተማርኳል፡፡  በዚህ ውጊያ የተማረከውን የፋሽስት የኮሎኔል እና ሌሎች ወታደራዊ የማእርግ  ልብሶች፣ እና የጦር መሣሪያዎችን አርማጭሆ ላይ በምርኮኝነት ለህዝብ አበረከቱ፡፡ ሕዝብም ! ብሎ ተነሣ። በሌሎች አካባቢዎች የነበሩ ጀግኖችም ይህን ተጋድሎ በምሳሌነት በመውሰድ ቆርጠው ተነሡ፡፡ ጸረ ፍሽስት አርበኝነቱ  በየቦታው ተቀጣጠለ።
ክቡር ደጃዝማች ብሬ ዘገየ፣ ትግላቸውን በመቀጠል፣  የጣሊያን ሰራዊት፣ሳንጃ እና ሥፍራ-ጣሊያንካምፕ ላይ ከፍተኛ ሰራዊት አስፍሮ  ስለነበር፣ የአርማጭሆን አርበኞች አስተባብረው  የሳንጃውን ካምፕ በመክበብ በተደረገው ወሳኝ ውጊያ ብዙ የፋሽስት ጦር መሪዎችንና ባንዳዎችን ሲገደሉ ጦር ካምፑን ሙሉ በሙሉ ደምስሰው ብዙ የጦር  መሳሪያና ጥይቶች፣ ቦምቦች ማርከው ነፃ በማውጣት የጠላትን ሀይል እና ሞራል ሰበሩ። የአርበኞችን ሞራል አነቃቁ።
በአማራ የኢጣሊያን ገዥ ኮርፓ ዳርማታ (እዚህ ላይ ወያኔ ትዝ ይሏል) በደጃዝማች ብሬ ክፉ ብትር ስለአረፈበት፣ የአርማጭሆን አርበኞች ለማጥፋት መጠነ ሰፊ ዝግጅት አድርጎ ዘመቻ ከፈተ። ሁኖም ግን፣ በወገራ በኩል የመጣውን የፋሽስት ሰራዊት የመረባና የጃኖራ አርበኞች ደመሰሱት፡፡ በወልቃይት አቅጣጫ የተንቀሳቀሰውን የፋሽት ጦር ጠገዴ ላይ በአዴት አርበኞች ሲደመሰስ፣  በመተማ በኩል ወደ ታች አርማጭሆ የመጣውን ጦር በግንባሩ በተሰለፉ የታች አርማጭሆ አርበኞች ተደመሰሰ።
በዋናነት `ተመርጦ እና በልዩ ዝግጅት ተደራጅቶ ወደ መሀል አርማጭሆ የተንቀሳቀሰው የፋሽስት ጦር፣ ደብረሲና ላይ ሲደርስ  አርበኞች በሰነዘሩት ጥቃት  መንቀሳቀስ ሳይችል ቀረ። በዚህ ግንባር ውጊያ አርበኛው ወደ ምሽጉ በመግፋት በተደረገው እልህ አስጨራሽ የጨበጣ ውጊያ ዋናው የፋሽስት ሰራዊት ጦር መሪ ጣላያናዊው ዲፋሶ ቲንንቲ ከብዙ የጦር መሪዎችና ወታደሮች ጋር ተገደለ፡፡  ብዙ የጦር መሣሪያ፣ ጥይት፣ ቦምብ ሲማረክ  ከሞት እና ቁስለኛ ከመሆን  የተረፈው ባንዳ  ሰራዊት ወደ መጣበት ተበታትኖ ተመለሰ።
የጣሊያ መንግሥት ከሑመራጎንደር የሚወስደውን መንገድ መልሶ ለመቆጣጠር ሳንጃ ላይ ጦሩን አጠናክሮ መሽገ። ክቡር ደጃዝማች ብሬ ዘገየ አርበኛውን አስተባብረው ምሽጉን በመክበብ 12 ቀናት ያልተቋረጠ ጦርነት አካሂደው ብዙ የጣሊያ የጦር መሪዎችና ባንዳዎች ሲገደሉ፣ ቁጥሩ  ብዛት ያለው ጠብመንጃ፣ ጥይትና ቦንብ ተማርኮ የጦር ካምፑን ተጣቆጥረውታል። ከዚህ ውጊያ በኋላ ፋሽስት ጣሊያን  በደረሰበት ተደጋጋሚ ሽንፈት ምክንያት ከጎንደር ከተማ ውጭ መንቀሳቀስ ተሣነው።
ክቡር ደጃዝማች ብሬ ዘገየ የትግል አድማሳቸውን በማስፋት  ጦርነቶች ባየሉባቸው ሁሉ በሚያቀርቡላቸው ጥያቄ መሰረት እየተዘዋወሩ በብዙ የጦር ሜዳዎች ላይ ማለትም በጠገዴ፣ በወልቃይት፣ በወገራ፣ በጭልጋ አውራጃዎች እና በሌሎችም እጅግ አኩሪና አስደናቂ ውጊያዎችን በመምራት ብዙ ድሎችን በአሸናፊነት ደምድመዋል፡፡ የጣልያን ጦር የአርበኛውን የደጃዝማች ብሬን  ስም ሲሰማ በፍርሀት መሸሽት የተለመደ ነበር፡፡
ያለ እዳው ዘማች ብሬ ደጃአዝማች”  እየተባለ በባንዳዎች ዘንድ ይቀነቀን ነበር።
ክቡር ደጃዝማች ብሬ ዘገየ በአርበኝነታቸው ወቅት፣ በውስጣቸው ብዙ ፊታውራሪዎች፣ ቀኛዝማቾች፣ ግራዝማቾች፣ ብላታዎች፣ ባለአምባራሶች  እንዲሁም የፖለቲካ እና ፍርድ ሰጭ ዳኞች ነበሯቸው።
ትግሉ አየጎመራ ሲመጣ እና  አብዛኛው ጎንደር ከፋሽስት ጣሊያን ነፃ መውጣት ሲጀመር፣ በስደት ሱዳን የነበሩ ወገኖች ትግሉን ለመርዳት ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ወደሚገኙ አርበኞች በመዘዋወር ቅስቀሳ ማካሄድ ጀመሩ ይህ በሱዳን በኩል የሚመጣውን እንቅስቃሴ  ለማስተባበር ስብሰባ ተደረገ ፡፡ 
ሁኖም በዚህ ስብሰባ ወቅት፣ ደጃዝማች ብሬ ዘገየ የተለየ ሀሳብ አነሱ፡፡ነጭን ጠልተን እየተዋጋን እንደገና ከኋላችን ሌላ ነጭ ማስገባት ለምናደርገው ትግል አደጋ አለው በማለት በእንግሊዞች የሚደረገውን እንቅስቃሴ እንደማይስማሙ ግልጽ አደረጉ ሆኖም ብዙ ውይይት ከተካሄደ በኋላ ደጀዝማች ብሬ ዘገየ እንግሊዞች ትብብር የማድረጋቸውን ሃሳብ ተቀበሉ። የእንግሊዙ ሻለቃ በንቲክ እና ጸሐፊ ትእዛዝ ኃይሌ ወልደሩፋኤል ግን በክቡር ደጃዝማች ብሬ የመጀመሪያ አቋም ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እንደተሰማቸው ቀረ።
1933 . . አርበኛው በጎንደር ከተማ ላይ የሰፈረውን የጣሊያ ምሽግ ሰብሮ ለመግባት ወስኖ አባ-በጥብጥ ብሬ ሠራዊታቸውን ይዘው ከፍተኛ ውጊያ አደረጉ፡፡ ሁኖም፣ ፋሽስት ጣሊያን ያለ የሌለ ተጨማሪ ሰራዊቱን ከሌላ አካባቢዎች ሁሉ በማሰባሰብ ጎንደር ከተማን መከላከል ሲጀምር፣ በአንጻሩ አርበኛው የውጊያ ስልቱን በመቀየር፣ የጣሊያን ሰራዊት ከጎንደር ከተማ እንዳይወጣ  እየተከላከለ እንዲቆይ ተደረገ። ጣሊያንም ጎንደር ከተማ ውስጥ ብቻ ተወስኖ ከረሞ 1934 . . ሕዳር ወር መጀመሪያ ላይ እጁን ሰጥቶ የጎንደር ከተማ ነፃ ወጣ።
አገር ነጻ ከወጣ በኋላ እነ ጸሐፊ ትእዛዝ ኃይሌ ወልደሩፍኤል፣ ክቡር ደጃዝማች ብሬ ዘገየ በትግሉ ጊዜከነጭ ጋር እየተዋጋን ሌላ ነጭ አንቀበልምያሉትን በማስታወስ በሥራ ድልድል ወቅት ለደጃዝማቹ  ለአርበኝነታቸው የሚመጥን የስራ ድልድል በመንሳት ይልቁንም ከጣሊያን ጋር ወግነው ሲወጓቸው ከነበሩት ባንዳዎች በታች መድበዋቸው ነበር፡፡ መላው አርበኛም በነ ኃይሌ ወልደሩፍኤል ድርጊት በጣም ቅሬታ ተሰማው። ክቡር ደጃዝማች ግን እኔ የተዋጋሁት ለአገሬ እንጂ ለነኃይሌ ወልደሩፋኤል አይደለም፣ ለጃንሆይም ስልጣን አነሰኝ ብየ ቅሬታ አላቀርብም በማለት  ቅር ሳይላቸው ቀረ፡፡
በዚህ ሁኔታ በተለያየ ጊዜ ክቡር ደጃዝማች ብሬ ዘገየ፡-
1.        የላይ አርማጭሆ ምስለኔ
2.        የጎንደር አውራጃ ነጭ ለባሽ ጦር አዛዥ
3.        የአርማጭሆ ወረዳ ገዥ
4.        የስሜንና በጌምድር ጠቅላይ ግዛት ነጭ ለባሽ ጦር ዋና አዛዥ ሆነው አገራቸውን በቅንነት አገልግለዋል።

በመጨረሻም 1959 . ከንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘንድ ተጠርተው ከልዩ ልዩ ሽልማቶች ጋር አንድ ላንድሮቨር መኪና ተሸልመው ወደ ጎንደር ሲመለሱ በደረሰባቸው  የመኪና አደጋ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በዚሁ . . አንድም ለቤተሰብ የሚተርፍ ንብረት ሳይኖራቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ክቡር ደጃዝማች ብሬ ዘገየ የወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ብሬ አያት ናቸው፡፡
ሊቁ እጅጉ
አዳነ አጣናው
ህዝብ የማወቅ መብት አለው !“
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!
ህፃናት የነባቢት ጸሐይ ናቸው!
የኔዎቹ ቅኖቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።