ልጥፎች

አቤቱታ ለዶር ገዱ አንዳርጋቸው ከቆሰለው ማህጸኔ!

ምስል
ሲከር ይበጠሳል ሲሞላም ይፈሳል! “አቤቱ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል? በተቀደሰው ተራራህስ ማን ይኖራል?” መዝሙረ ዳዊት ፲፬ ቁጥር ፩ ይድረስ ለዶር ገዱ አንዳርጋቸው የአማራ ክልላዊ መስተዳደር ፕሬዚዳንት፤ ባህርዳር ·        ጠ ብታ። ጤና ይስጥልኝ ዶር ገዱ አንዳርጋቸው እንዴት ከረሙ? በቅድሚያ በእርስዎ የተመራው ልዑክ ከስሜን አሜሪካ ወደ ባዕት በሰላም ስለገባ ህሊናዬ አርፏል። እኔ የተፈጥሮ አየሩን እራሱ አላምነውምና። መንፈሴ በሰላም ወጥታችሁ ስለመመለሳችሁ ይሰብ እናንተ ደግሞ ስለ ተልዕኳችሁ ሆነ ስኬታችሁ ትጉ፤ እንዲህ ሥራ መከፋፈል … አቨው እና እመው በጸሎት ይርዷችሁ ...  ·        መነ ሻ። https://ethiov.com/single-video/TAoDl6l50Yz የከተሞች መድረክ በወረታ ከተማ ክፍል ሁለት https://www.youtube.com/watch?v=uAhWefWo6V0 የከተሞች መድረክ በወረታ ከተማ ክፍል ሶስት https://www.youtube.com/watch?v=10lqnruXJP8 የከተሞች መድረክ በወረታ ከተማ ክፍል ሶስት ·        የ ቆሰለ ትዝብት ከማህጸን ዕንባ። ትናንት የአማራ የብዙሃን ሚዲያ የወረታ ከተማ ነዋሪዎችን አሰባስቦ ሲያነጋግር የነበረውን ዝግጅት አዳምጥኩኝ። እንዲህ የወለጋ የወ/ሮ ታደሉ መሰል ዕጣ ፈንታ እናቶች ወረታ ላይ እንደሚኖሩ ከገመትኩት በላይ ነው የሆነብኝ። አማራ መሬት ላይ ለ50 ዓመት የሆነውን አውቃለሁኝ። አዲስ አይደለሁም። የወያኔ ሃርነት ትግራይ የ...

ህወሃት ከትከሻ ኦነግም ከአንቀልባ ወርደዋል።

ምስል
ህውሃት ከትከሻ ኦነግም ከአንቀልባ ወርደዋል። “ለአመጸኞች ልጆች ወዮላቸው!  ይላል እግዚአብሔር”  ትንቢተ ኢሳያስ ፴ ቁጥር ፩ ከጸሐፊ አቶ መስፍን ማሞ ተሰማ ታህሳስ 2011 ዓ/ም (ዲሴምበር 2018) ሲድኒ አውስትራሊያ mmtessema@gmail.com                     ሠላም ለናንተ ይሁን! የትግላችንና የመሥዋዕትነታችን የመታሰራችንና የመሰደዳችን ውጤት የሆነው አብያዊው መንግሥት በኢትዮጵያ መንበር ላይ ሲቀመጥ ለ 27 ዓመት በምድሪቱ ላይ የሰቆቃና የርኩሰት የጥፋትና የዝርፊያ ሁሉ ቁንጮ የሆነው አሸባሪውና ዘረኛው ህወሃት ከኢትዮጵያ ትከሻ ላይ ያለጥርጥር ተመንጭቆ ወርዷል። የወረደውና የተዋረደው ህወሃት መቀሌ ትግራይ መሽጎ ይንደፋደፋል። በወላለቀ ጥርሱ እየገለፈጠ፤ በተሸበሸበ እጁ እያጨበጨበ በስታዲየምና በአዳራሽ እየተሰበሰበ የቁም ተዝካሩን ያወጣል። ማጋነን የመሰለው በቅርቡ በ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ የተካሄደውን ስብሰባ ይመልከት። በዚያ አዳራሽ የክፉ ሰዎች ስብስብ የሆነው ህወሃት ጣዕረ ሞት ላይ ስለመሆኑ አቶ ስብሃት ነጋ በአስረጅነት የቀረበ « አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም » የሚለው ብሂል ማሳያ ነው። 27 ዓመት ዲሞክራሲን ቤተ መንግሥት ሆኖ ሲሰይፍ የኖረው ህወሃት መቀሌ ላይ መሰየፍ ባቃታቸው የጃጁ እጆቹ እያጨበጨበ የፀረ ዲሞክራሲነቱን ተዝካር አውጥቷል። አሸባሪው ህወሃትና በኢትዮጵያ ምድር በአምሳያው ፈጥሮ የዘራቸው ...