ልጥፎች

ውሃም የሜንጫ ቤተኛ ….

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ  ውሃም የሜንጫ ቤተኛ …. „ጥበብ በቀደሙ ሰዎች ሁሉ ዘንድ ተመረመረች“ መጽሐፍ ሲራክ ምዕራፍ ፴፱ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 24.03.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። እንዴት ናችሁ ውዶቼ ጥቂት ነገር አንድ ማሰተዋል ባለብን ጉዳይ የበለጠ ብልህነት መሰነቅ እንዳለብን ትንሽ ማለትን ፈልግሁ … ·        ቁጥር አንድ አሮማራ እና ጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመ … ኦሮማራ ውስጥ በንቃት ከተሳተፉት ጦማርያን ውስጥ አቶ ስዩም ተሾመ አንዱ ናቸው። በኦሮማራ ጥምረት ምን ትርፍ ምን ኪሳራ ተገኜ የዛሬ አጀንዳዬ አይደለም። ብቻ የዛ ቀዳሚ አቀንቃኝ የነበሩት አሁንም የሆኑት ጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመ ማን ናቸው? የሚለውን የቤት ሥራ ልሰጣችሁ ነው … ለቅኖቹ ለውድ አንባቢዎቼ …   https://www.youtube.com/watch?v=4O6kMzSSwPE&t=21s Ethiopia: [ ነፃ ውይይት ] የአዲስ አበባ ባለቤትነት እና የኦሮማራ ጥምረት Andafta Published on Feb 27, 2019 ከዚህ ውይይት በሆዋላ ጠ/ሚር አብይ አህመድ የዶር ገዱ አንዳርጋቸውን ሽኘታ ተገኝተው ጠቅላይ  አዲሱ ርዕሰ መስተዳደር ዶር አንባቸው መኮነን ወደ አንቦ ጎራ ብለው ያ የተጀመረውን የአስተኛኝ ኦሮማራን መንፈስ እንዲያድሱ ጥሪ አቅርበዋል።  ቀኑን ተመልከቱት ጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመ በየካቲት 27 ቀን 2019 ያደረጉትን ቃለ ምልልስ እሳቸው በመጋቢት 8 ቀን 2019 አጸደቁት ማለት ነው። አሁን ትናንት ሳደማጥ ደግሞ ከትህትናም ወርዶ ይቅርታ እንዲጠዬቅ የሚል ዕድምታ አ...