ልጥፎች

ልብ እግር ላይ ባይሆን?

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ልብ እግር ላይ ባይሆን? „ኃጢያት የሚሠሩ በውን አያውቁምን? እግዚአብሔርን አይጠሩትም“ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲፫ ቁጥር ፯ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 10.04.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። ጤና ይስጥል የኔዎቹ። ደህና ናችሁ ወይ ዛሬ ደመንመን ብሏል። ከፍቶታል እንደማለት። አላዛሯ ኢትዮጵያስ? ደመና ዛሬ በፆም በጸሎት የማይገኝ እዬሆነ ይሆን እላለሁኝ እኔ? ዛሬ ለመነሻ የሚሆን ተያያዥ ነገሮችን በክፍል አንድ ዓይተን ክፍል ሁለትን አስከትላላሁኝ። መነሻዬ ባለ መዲያሊያው አስተኛኝ የ ኦዴፓ መግለጫ ይሆናል። https://www.zehabesha.com/amharic/archives/94663 የህዝቦች ወንድማማችነትና የአብሮነት መልካም እሴቶች በአፍራሽ ሃይሎች ተልዕኮ አይደናቀፍም ! ኦዴፓ ከዓመት በኋዋላ ይመስለኛል ብራና የነካ መግለጫ አውጥቷል። ያው ማይክ ላይ ነው መግለጫው ጥዋት እና ማታ የሚንቆረቆረው … ለማመሳከር፤ ለማያያዝ፤ ለመሞገትም በማይመች መልኩ። አሁን አዲስ አባባን የኦሮምያ የባለቤትነት የማድረግ ዓዋጁ አልወጣም። ያን በነጋሪት ጋዜጣ እስኪወጣ ተብሎ ይመስለኛል … የሆነ ሆኖ ያን ጊዜ ሲያምልሉን በነበረው ጊዜ አንድ ልባም መግለጫ አውጥተው ነበር። „የብሄር ጭቆና አልነበረም“ ብለው። ያ ነበር ፍልስፍናው አገር የማዳኑ ሥር - ነቀል ለወጥ አደረገ ብለን በሆታ ተስፋችን መሬት ያዘ ያልነው። በስውርም ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን ወደ ቀብር የላከ ነበር። አሁን ዳግሚያ ትንሳኤ ላይ ነው ያለው። ለነገሩ አሁን ብቻ ሳይሆን ለለጥ ይበሉ ብአዴን ሥሙን ሲቀብል በዛ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት አልነበረም አይባልም፤ የፌድ...