ልጥፎች
ግንቦት 20 ለእኔ፤ ያኔም ሆነ ዘንድሮ። ከጸሐፊና ተርጓሚ አቶ መስፍን ማሞ ተሰማ።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። ግንቦት 20 ለእኔ፤ ያኔም ሆነ ዘንድሮ። “ሁሉ ተፈቅዶልኛል ሁሉ ግን አይጠቅምም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳን አይሰለጥንብኝም። የ ሐ ዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ቆሮንቶስ ምዕራፍ ፮ ቁጥር ፲፪” ከጸሐፊ እና ተርጓሚ ከአቶ መስፍን ማሞ ተሰማ። ሠላም ለናንተ ይሁን! ይላሉ ጸሐፊ እና ተርጓሚ አቶ መስፍን ተሰማ ከ አውስትራልያ ሲዲኒ … እኔም ሥርጉተ ሥላሴ ከእመ ዝማታ ሲወዘርላንድ ዘንጠፍ ያለ ትሁታዊ ሰላምታዬ ለታዳሚዎቻችን ይድረስ እላለሁኝ። ውዶቼ ... አሁን ወደ ጸሐፊው አቶ መስፍን ማሞ ጭብጥ አብረን ብያለሁ ጀርገድ ባለ ልስሉስ አክብሮት … እንሆ … በድምጽ ... https://www.youtube.com/watch?v=gQ-HCCzZ_T0&feature=youtu.be "ግንቦት 20 ለእኔ፤ ያኔም ሆነ ዘንድሮ።" ከጸሐፊና ተርጓሚ አቶ መስፍን ማሞ ተሰማ። በአምባ ገነኑ የደርግ ዘመነ መንግሥት እስከ ግንቦት 20/1983 ዓ / ም ኢትዮጵያውያን ( ከዘር ሐረጋቸው በፊትና በላይ በኢትዮጵያዊነታቸው የሚያምኑና የማይደራደሩ፣ ታሪካቸውን በታሪክነት ተቀበለው የታሪክ ቂም በቀል ያልወረሱና ለዚህም ያልዘመቱ ሁሉ ) ሀገር ነበራቸው፤ መቀመጫ። ሰሜን ብንወጣ ጎጆ ብንቀልስ፤ ደቡብ ብንወርድ ስራ ብንፈልግ፤ ምሥራቅ ብንቀመጥ ሱቅ ብንከፍት፤ ምዕራብ ብንኖር ብንነግድ/ ብናስተም ር ማንም መጤ፥ ማንም ሠፋሪ እያለ አያፈናቅለንም፥ በገጀራና በቀስት አይፈጀንም ነበር። እንደ መንግሥት ...