ልጥፎች

የኔታዋ የደወል ምህላን፤ ብትደፍረው፤ የአርሲ ነገሌ መስቀል ጉዞ ወደ ቀራንዮ

ምስል
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። የኔታዋ የደወል ምህላን ፤ የደወል አቤቱታን ብትደፍረው ታተርፍበታለች። የአርሲ ነገሌ መስቀል ጉዞ ወደ ቀራንዮ። „አንተ ታካች እስከ መቼ ትተኛለህ? ከእንቅልፍህስ መቼ ትነሳለህ?“ {መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ 6 ቁጥር 9} ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ 13.01.2020 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ። አሜን። ይድረስ ለብፁዓን ወቅዱሳን አባቶቼ በሙሉ። በያሉበት ።                                                 ሰማዕት ሱራፌል ሰለሞን።                         ·        እፍታ። ጤና ይስጥልኝ የአገሬ ቅኔዎች እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? እኔ በረጋ ጸጥታ - በአርምሞ ዝምታ - ዘመንን በቀስታ ከምታስናግደው ከእመቤት ሲዊዝሻ ጋር ደህና ነኝ። እህቴ ከወደ አሜሪካ ጎራ ባለችበት ወቅት የገዳም ከተማ ስትል የምኖርበትን ቀዬ መሰጠረችው። ለእኔም ግጥሜ የሆነው በዚህ ስሌት ይመስለኛል አብረን ገደምን። ስከነት የሰፈነበት። ዛሬ ሁለት ዕርዕሰ ጉዳዮችን በአንድ አጣምሬ ነው እማቀርበው። „ የኔታዋ የደወል ምህላን፤ የደወል አቤቱታን  ብትደፍረው ታተርፍ...