ጃዋር ቀነ ገደብ ያስቀመጠውን የምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ፈርሞ ተቀበለ (ጎልጉል እንደዘገበው)
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። „በውን እግዚአብሄር እንዴት እንደሚያዝዛቸው የደማናውን ብርሃን እንዴት እንደሚያበራ አውቀሃልን?“ (መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ 37 ቁጥር 15) የጉጉሱን መጨረሻውን ያዬው ሰው። ሥርጉተ©ሥላሴ Seregute©Selassie 21.01.2020 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ · መቅድም ። እንዴት ናችሁ የኔዎቹ። እኔ ለብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ጠንከር ያለ አቤቱታ ላቀርብ ጹሑፍ ጨርሼ እርማት ላይ ነበርኩኝ። ነገር ግን የተለወጠ መርጃ ካለ ብዬ ድህረ ገፆችን ስዳስስ ይህን አዲስ መረጃ ከጎልጉል አገኜሁኝ። የእኔ ከዚህም ከፍ ያለ ስለሆነ ሙግቴ ይቀጥላል። የሆነ ሆኖ ይህም ጎሽ የሚያሰኝ ስለሆነ እነሆ ሙሉውን ትታደምቡት ዘንድ አጋራሁኝ። ይህ የእርምጃ አወሳስድ ጉዳይ የሃይል አሰላላፉን እንደገና የሚበውዘው ይመስለኛል። ኢትዮጵያ የትኛው መንግሥት እንደሚገዛትም ይለይለታል። ግርዶሽ የተሠራላቸውም ነገሮች ገለጥለጥ ይላሉ። በዚህ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ድፍረት ውስጥ የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ፈቃድ እንዳለበት አስተውያለሁኝ። ድፍሩቱ የሚቀዳው ከዛ ነውና። ዘገባው የጎልጉል ነው። ለዚህም ነው ትምህርተ ጥቅስ ውስጥ ያስገባሁት። ፎቶውም ከጎልጉል የተወሰደ ነው። · መነሻ። http://www.goolgule.com/jawar-signed-and-received-the-election-board-letter/ ጃዋር ቀነ ገደብ ያስቀመጠውን የምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ፈርሞ ተቀበለ ለቀረበለት ሕጋዊ ደብዳቤ ዛቻን አስቀድሟል...