ልጥፎች

ለቅን ኢትዮጵውያን ነፍሴ ትራራለች።

ምስል
  እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ። ለቅን ኢትዮጵውያን ነፍሴ ትራራለች። „ ኃጣን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይቀመጣሉ፤ ሰው በኃይሉ አይበረታም “ ( መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕራፍ 2 ቁጥር 9)   በድንገት በሳቢያ አይደለም የአማራ ህዝብ እዬተፈጄ ያለው። ሊቆቹም እዬታሰሩ ያሉት። መነሻውም መድረሻውም የገደ ዴሞግራፊ ሥሪት ነው።፡ አሁን የሰሞኑን የከተሞች ውድመት፤ በኢትዮጵያዊነት የሚታወቁ የፖለቲካ ሊሂቃን አስሮ የመበቀል ድንገቴ አድርገው የሚዩ ቅኖችን አያለሁኝ። እናም ነፍሴ ትራራላቸዋለች። የ ኦሮሞ ፖለቲካ የበታችነት ደዌ ነው። በሽታ። ወረርሹኙ ያልነካቸው ትናንት የነበሩ ዛሬም ያሉ ይኖራሉ። በሂደት ግን ውስጣቸውን እዬገለጡ የሚመጡም ይኖራሉ። በሽታ ጥቃቱን የሚፈጽው ለፈቀደው ብቻ አይደለምና። ከዚህ ወረርሽኝ ያመለጡ ጀግኖች አይኖሩም ብዬ መደምደም አልችልም። ይህን ካልኩ ተፈጥሮን መቃረን ይሆንብኛል እና። ችግሩ በዚህ ሂደት ያለ አቅም የሚፈሰው አቅም መባከኑ ነው። ለዚህ ነው እኔ ቅኑ አማራ አቅም ቁጠባው ዋና ስትራቴጄ እንዲሆን እምሻው። ተስፋውም ከ50% በታች አድርጎ እንዲጠብቅ እምለምነው። ለምን ቢባል ድንገት የእኔ ያለው ሰው ሲያጠው እዬተጎዳ ስለማይ። ደስታንም በልክ አድርጉት እምለው ለዚህ ነው። ደስታ ሲበዛ ምርቃትም ይነሳል። የተጠበቀው ደስታ ሲከስም ደግሞ የሥነ - ልቦና ክሳት ያመጣል። ማንም የለም፤ ምንም የለም ብሎ አጨልሞ ማዬትም ችግር ያስከስታል። ቋሚ ሊሆን እንደማይችል ማሰቡ ይበጃል። አሁን ባለፈው ዓመት የ አብይወለማ ጉዞ መንገድ ሲስት ብዙው በ አዲስ ተስፋ ውስጥ ነበር። በባልደራስ እና በአብን። ዘግዬት ብሎም በአብሮነት ላይ። አሁን ያሉበትን ደረጃ ስታዩ ደግሞ ከዬሉም...

ኢትዮጵያ ተምች ነው የወረደባት።

ምስል
እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ። ·         ኢትዮጵያ ተምች ነው የወረደባት።   „ ኃጣን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይቀመጣሉ፤ ሰው በኃይሉ አይበረታም “ ( መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕራፍ 2 ቁጥር 9)   ዕለተ አርብ ማዕዶተ ኢትዮጵያ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ሕይወት አዝመራ ለራህብ የሚራር።   ኢትዮጵያዊነትን ያከበረ፤ ያጸደቀ፤ ያሰበለ ለካቴና ሲሰጥ ኢትዮጵያ የት ነሽ ብሎ መጠዬቅ ይገባል። አወን ኢትዮጵያ ካቴና ላይ ናት። ለምን „ በገዳ መደመር “ ስላልተካተተች። ይህን አሻም ያሉ ካቴና ላይ ናቸው። ወይንም በረጅም ገመድ በቁም እስር። እሺ ያሉ ደግሞ በከራባት እና በገበርዲን ሰርግ እና መልስ ላይ። ኬክም አለበት። ኢትዮጵያም ሙሉ ወርዱ ቀርቶባት ማቅ ለብሳ ትንፋሽ ባገኜች ምንኛ ዕድለኛ በሆነች ነበር። ህወሃት መራሹ ኢህዴግ የከታተፋት ኢትዮጵያ እንኳን አሁን የለችም። ድፍን ነገር። አቶ እስክንድር ነጋ ሲታሰር እኮ ነገሩ አብቅቷል። እ። ከዛ በፊት ኢንጂነር ስመኜው በቀለም ሲገደሉ የኢትዮጵያ ሉዕላዊነት ተረሽኗል። ነገረ አባይ እኮ ረግረግ ውስጥ የገባው ለዛ አሉታዊ ዴሞግራፊ የኮፒ ራይት ሽሚያ ላይ ሲዳካ ነበር። ግን ልብ መሸመቻ ይኖር ይሆን ? እህ። ማፈላለጉ ይገባል ብዬ ነው። ገዳ አባይ የእኔ ነው አለ። ሊቃውንታቱ የፈለሰሙት፤ የመሩት፤ ያስተዳደሩት በእ...