ለቅን ኢትዮጵውያን ነፍሴ ትራራለች።
እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ።
ለቅን ኢትዮጵውያን ነፍሴ ትራራለች።
„ኃጣን ግን ዝም ብለው በጨለማ
ይቀመጣሉ፤ ሰው በኃይሉ አይበረታም“
(መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕራፍ 2 ቁጥር 9)
በድንገት በሳቢያ አይደለም የአማራ ህዝብ እዬተፈጄ ያለው። ሊቆቹም እዬታሰሩ ያሉት። መነሻውም መድረሻውም የገደ ዴሞግራፊ ሥሪት ነው።፡
አሁን የሰሞኑን የከተሞች ውድመት፤ በኢትዮጵያዊነት የሚታወቁ የፖለቲካ ሊሂቃን አስሮ የመበቀል ድንገቴ አድርገው የሚዩ ቅኖችን አያለሁኝ። እናም ነፍሴ ትራራላቸዋለች። የ ኦሮሞ ፖለቲካ የበታችነት ደዌ ነው። በሽታ። ወረርሹኙ ያልነካቸው ትናንት የነበሩ ዛሬም ያሉ ይኖራሉ። በሂደት ግን ውስጣቸውን እዬገለጡ የሚመጡም ይኖራሉ። በሽታ ጥቃቱን የሚፈጽው ለፈቀደው ብቻ አይደለምና።
ከዚህ ወረርሽኝ ያመለጡ ጀግኖች አይኖሩም ብዬ መደምደም አልችልም። ይህን ካልኩ ተፈጥሮን መቃረን ይሆንብኛል እና። ችግሩ በዚህ ሂደት ያለ አቅም የሚፈሰው አቅም መባከኑ ነው። ለዚህ ነው እኔ ቅኑ አማራ አቅም ቁጠባው ዋና ስትራቴጄ እንዲሆን እምሻው።
ተስፋውም ከ50% በታች አድርጎ እንዲጠብቅ እምለምነው። ለምን ቢባል ድንገት የእኔ ያለው ሰው ሲያጠው እዬተጎዳ ስለማይ። ደስታንም በልክ አድርጉት እምለው ለዚህ ነው። ደስታ ሲበዛ ምርቃትም ይነሳል። የተጠበቀው ደስታ ሲከስም ደግሞ የሥነ - ልቦና ክሳት ያመጣል።
ማንም የለም፤ ምንም የለም ብሎ አጨልሞ ማዬትም ችግር ያስከስታል። ቋሚ ሊሆን እንደማይችል ማሰቡ ይበጃል። አሁን ባለፈው ዓመት የ አብይወለማ ጉዞ መንገድ ሲስት ብዙው በ አዲስ ተስፋ ውስጥ ነበር። በባልደራስ እና በአብን። ዘግዬት ብሎም በአብሮነት ላይ። አሁን ያሉበትን ደረጃ ስታዩ ደግሞ ከዬሉም የሚሻል ነገር ስሌለ ብቻ ካልሆነ ቀጣይ ተስፋው ከምርጫ በፊት ዳመና ለብሷል። ጭጋግ ውጦታል። በዚህ ጭጋግ ውስጥም ተስፋ አያልቅም እና አቅም ይመገባል። ስለምን ፈጣሪ አለ ብሎ የሚያስብ ሰብ ተስፋ ተፈጥሯዊ መኖሩ ነውና።
የሆነ ሆኖ አቅምን መጥኖ ለመስተዳደር አለመፍቀድ ምክንያታዊ ነው። ይህ ስለምን ብትሉ ዴሞግራፊ ፍልስፍናውና ላይ በቂ አቅም አልፈሰሰም። የፖለቲካ ሙግቱ ተረኝነት ፈረቃ በሚል ከዛ ላይ ተቀርቅሮ ነው የቀረው። ይህ ሥርዓት ከህውሃት በቀዳው ብቻ አይደለም እዬተመራ ያለው። በገዳ ትውፊት ነው።
እርግጥ ነው ትናንት ባዘናጉበት መልክ ዛሬም አዲስ አቅም እዬሰበሰቡ ነው። መጋረጃው ኢትዮጰያዊነት ነው። ስለሆነም ትናንት ሥር ሰዶ ትንፋሽ እስኪያገኝ ድረስ ሁለገብ ድጋፍ አግኝቷል። ያገኜው በቀጥታም በተዘዋዋሪ ምክንያት ነው።
ተስፋ የሆኑ ነገሮች ብቅ ሲሉ በዛ ላይ አትኩሮት ይሰጣል፤ ድንገቴው ትራጄዲ ታቅዶ ሲከውን በዛ ላይ አቅም ይፈሳል። ከዋናው አብይወለማ ዴሞግራፊ ላይ ሊሰራ የሚገባው በሳል ፖለቲካዊ ተግባር የተገባውን ያህል አቅም ሊመገብ ስላልቻለ ውድመቱ፤ ጥቃቱ ቀጠለ። የተገባውን ያህል ከምል ጭራሽም ተረስቷል ብል የሚሻል ይመስለኛል።
እንደ ፖለቲካ መሪ በጣም ያዘንኩት ፕ/ ብርሃኑ ነጋ የሱማሌ ክልል የኦሮሞ ማፈናቀል ተወዶ ተፈቅዶ በሁለት ምክንያት እንደተካሄደ ሊገባቸው አለመቻሉን ከጦማሪ ወ/ሮ መስከረም አበራ ጋር በነበራቸው የቤተሰባዊ የወግ ቆይታ ተረዳሁኝ።
በሱማሌ ክልል በነበረው መፈናቀል ኦህዴድ ሙሉ አቅሙን አፍሶበታል። በሁለት ምክንያት። አንደኛው ምክንያት ጫና በህወሃት ላይ ለማሳደር ነበር። ሁለተኛው ምክንያት ግን ለከተማ ዴሞግራፊ አዲስ አበበ እና ዙሪያውን ከሱማሌ ክልል አፈናቅሎ በማስፈር የፖለቲካ ሸቀጥ ለመሸቀጥ ታቅዶ በኦህዴድ መከወኑን እንደ አንድ የኮኖሚ ሊቀ ሊቃውንት ወይንም ሳይንቲስት፤ እንደ አንድ አገር ይመራል ተብሎ እንደታሰበ የፖለቲካ ሊቅ ይህን ማገናዘብ አለመቻል ሥምዬለሽ ነው የሆነብኝ ክህሎቱ።
በባልደራስ ላይም የሰጡት አስተያዬት የሳቸውን ማህበራዊ መሰረት ለማናጋት ስለመሆኑ ልብ አለመለታቸው እና ከዴሞግራፊው ፖለቲካ ጋር አጣምረው በቁጥብነት መራመድ አለመቻላቸው አሁንም የመክሊትም የቅባም ችግር እንዳለ አይቻለሁ። እንኳንስ ሌላው በቅንነት፤ በተቆርቋሪነት የሚሳተፈው ፖለቲከኛው ቀርቶ። እነዶር አንባቸው መኮነን በህይወት እያሉ እንኳን ከዚህ መነሳት አልቻሉም ነበር። ለምን ብለው አልጠዬቁም። አሁን ያለውን መንግሥት አቅጣጫ መንገዱን ያሳያል ዴሞግራፊው። በይፋ እኮ ነው የሰሩት።
ሌላው የኦሮሞ ማህበረስብ በታሪክ እንደተረዳነው ከተሞች ላይ አይደለም መኖሩ የሚመሰረተው። መኖሩ ገጠር ላይ ነው። ስለዚህ በፖለቲካ ምስረታ ላይ ያለው ሚና ድርሻው ስስ ነው። የለማወአብይ የፖለቲካ መሰረት ደግሞ ይህ ነው። ይህን መገልበጥ።ይህን በተለያዬ መንገድ ከሁለት ዓመት በዘለለ ይህ ማለት ሲቻል ባለው ላይ መበወዝ እንደ የንጉሦች ንጉሥ አጤ ሚኒሊክ ቤተ መንግሥት ሳይቻል ደግሞ አፍርሶ መስራት። ከመቀሌ በስተቀር ሁሉንም ከተሞች የ እኛ ነው የሚሉት አሁን ባለው ሁኔታ። የሚገርመው ቅባውም፤ ትውፊቱም ስለሌላ የተረከቧቸው ከተሞች ደቀው ነው የቀሩት። አሁን ከፋ ከትልልቆቹ የሚመደብ ነበር። ዛሬ ደግሞ የወረዳ ያህል እንኳን አይደለም ነው ዪባለው። ለዚህ ነው አሁን በቁጭት ደቡብን አፍርሶ አዋሳን ለሲዳማ መስጠት የተተገበረው። ማፍረስ፤ መበወዝ ወዘተ … የዚህ መሰረቱ የህሊና ደዌነት ነው። የበታችነት ስሜት።
ሌላው ያልተነካው፤ ያልተደፈረው ጉዳይ በ አቶ በረከት ስሞን እና በ አቶ አባ ዱላ ገመዳ መሃል የነበረው ስውር ስምምነት የአማራ የህልውና እና የማንነት ተጋድሎ እና የ ኦሮሞ ንቅናቄን ለመወርስ የነበረው ፍርርም እንደ ተቀበረ ያለ ጥልቅ ዕምቅ ፖለቲካዊ ዕድምታ ነው። በዚህ ውስጥ ከምንም ያልተቆጠረው፤ ልቦናም የተነፈገው የአቶ አባ ዱላ የፖለቲካ አመራር ጥብብ እና ግብ አንደምን ገዢ መሬቱን መቆጣጠር እንደቻለ ሌላ የታሪክ ቻፕተር ነው።
ሌላው ኦሮሞማን እንደ ሊኳንዳ ስጋ የሚሸነሽኑ ወይንም ቅርጫ ሥጋ አድርገው የሚያርቡ ወገኖች ጉዳይም የተሳሳት መንገድ ነው። ያለው ኦሮሞማ መሰረቱ አንድ ነው የገዳ ሥርዓት። „የለማ - የአብይ - የጃዋር - የዳውድ - የመራራ - የበቀለ - አባ ዱላ ኦሮሞማ“ የሚለው መንፈስን በፋስ የሚተረትር ሚስሊዲንግ አብን እንደግፈው ከሚል ሽምቅ የፖለቲካ ሸፍጥ ወይንም የግንዛቤ እጥረት ሊሆን ይችላል። በዘመናዊቱ ኢትዮጵያ የ16ኛውን ክፍለ ዘመን አስምሌሽን ዕውን የማድረግ ሂደት በ ኢትዮጵያ ማዋለ ንዋይ፤ በኢትዮጵያ መንፈሳዊ አቅም በይፋ እና በአደባባይ እዬተከወነ ነው።
አቅምን እንደ ሥጋ እዬበለቱ አቅም እንዲያገኝ የሚያደርጉ የፖለቲካ ተንታኞች ኢትዮጵያዊነትን ፈተና ውስጥ እዬከተቱት ስለመሆኑ አበክሬ እገልጻለሁኝ። በሌላ በኩል ተስፋዎቻችንም ለበላህሰብ እያስከቡ ስለመሆኑም ጨምሬ እገልጻለሁኝ።
ልብለልብ ስለምንተዋወቅ ይገባቸዋል ብዬ አስባለሁኝ። በቁጥብንት እምጽፈው ሁሉንም ካጨልምነው ትውልዱ ቅስሙ እንዳይሰበር ኃላፊነት ስለሚሰማኝ ነው።
ተስፋ ያደረግንባቸው አብን ባልደራስ እና አብሮነት ዕጣ ፈንታቸው ምን ሊሆን እንደሚችል ለታገሰ በቅርብ ቀን ያዬዋል። በዚህ ማህል አዳኝ ነን ብለው የሚመጡ ነፍሶችም ይኖራሉ።
ሁሉም አቅም የሚሹት ከአማራ መሆኑን ግን ቸል ሊባል አይገባም። ለአማራ ጆኖሳይድ ግን አንድም ሰው ደፍሮ ዓለምን የሞገተ የለም ልጆቹ አልፎ አልፎ ከሚታትሩት በስተቀር። ይልቁንም ለጨካኙ የገዳ ሥርዓት አቅም አዋጡ የሚል አጋሰስ ጥሪ ነው የሚደመጠው። እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ግን አላደርገውም። ደፍሮ የሚመጣ የለም እንጂ የሚመጣ ካለ ይምጣ እና ይሞግተኝ። ለገዳ ሎሌ ከምሆን ብሞት ይሻለኛል። የማህበረ ሌንጮ ሎሌ ከምሆን እዬሰማሁ መቃብር ብወርድ ይሻለኛል። ባልደራስ አለን? በማን ሥር ነው ያለው? አብን አለን? በማን ሥር ነው ያለው? ቅን ሆናችሁ ፈትሹት። አመሰግናለሁኝ።
https://www.youtube.com/watch?v=myaY01aP4pg&t=278s
የኦሮሙማ ጠቀራዊ የዲሞግራፊ ፋሽስታዊ ጉዞ ከአቶ ለማ መገርሳ አንደበት።
https://www.youtube.com/watch?v=JSlvGahMtwg&t=527s
አሉታዊ የዴሞግራፊ ምህንድስና የበታችነት ስሜት ደዌ ነው። {የወግ ገበታ}
https://www.youtube.com/watch?v=xFrQuu3qjyg&t=469s
የአሉታዊው የዴሞግራፊ ዕሳቤ ለአላዛሯ ኢትዮጵያ የታዘዘ የጢስ አይዎሎጂ ነው። {የወግ ገበታ 17.06.2019}
https://www.youtube.com/watch?v=ipRpgkxgioU
አሉታዊው የዴሞግራፊ ፍልስፍና የበቀል ፍልስፍና ነው። {የወግ ገበታ 08.06.2019}
https://www.youtube.com/watch?v=-yWKYUC_9iA&t=165s
2: የዴሞክራሲ ውድቀት እንጂ የዴሞክራሲ ተስፋ የልቅና ምህንድስና አይደለም።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ