አብን እና የሥርጉተ ዕይታ ትናንትና ዛሬ።

 

እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ።

እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ።

 


አብን እና የሥርጉተ ዕይታ ትናንትና ዛሬ

 

 

እኔ በተፈጥሮዬ አዲስ የፖለቲካ ድርጅት ሲፈጠር እንደ ገናም ፖለቲካ ድርጅቶች ተጣመርን፤ ተዋህድን ሲሉ አይደንቀኝም። ብዙም አልደክምበትም። ሲመሰረት በብዛት የጸፍኩበት አብን እና ባልደራስን ብቻ ነው። ምክንያቱም የህልውና ተጋድሎ የፈጠራቸው ስለሆኑ ብቻ።

ስለሆነም አብን ሲፈጠር የጻፍኩት፤ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም እና ጋዜጠኛ ካሳሁን ይልማን የሞገትኩበት ሊንኩ ተቀምጧል። በውጭም አብን ወጀቡ ሲበዛ ዕውቅና እንዲያገኝ ተደክሞበታል። አብን በተነሳበት መክሊቱ መዛነፍ ሲያሳይ ደግሞ ሊነገረው ይገባል። በቂ አጀንዳ አለው። በራሱ አጀንዳ ውስጥ ሰክኖ ለተልዕኮው መትጋት ይኖርበታል።

ኦህዴድን ልተካ ብሎ መገልገል አይገባውም። ኦህዴድ የስሜን ፖቲካ እንዲደቅለት ይፈለጋል። የሰሜን ጥንታዊ ከተሞች እና ቅርሶቹ ከተሞች በጦርነት እንዲወድሙ ይሻል። በጦርነት የአማራ ህዝብ እንዲጎሳቆል ይሻል።

በጦርነት የትግራይ እና የአማራ ህዝብ በቅራኔ እንዲወጠሩ ትውልድ እንደሚመክን ይሻል። የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ትቢያ እንዲሆን ይሻል። ከተሞችን እኮ ፕሮቴስታንቶች እንዲመሩት እዬተደረገ ነው።

ዕድሉን ባገኝ አገር ልመራ እችላለሁ ያለ ፓርቲ በዚህ መሰል የአብይዝም ትሪኪ ገብቶ መማገድ አይገባውም። አቅሙን አውቆም መንቀሳቀስ ይኖርበታል። የኃይል አሰላልፉን መረዳት ይገባዋል።

አብን ኦነጋዊው ኦህዴድ ለፈጠረው ፈንቅል መግለጫ ማውጣት፤ ህወሃት በሽብርተኛ እንዲፈረጅ መጠዬቅ፤ በአማራ ክልል የሌሉ አቤቱታ የቀረበባቸው የአማራ ርስቶችን ምርጫ አያካሂድ ብሎ ማገድ የማይሆን አካሄድ ነው። ፌድራል መንግሥቱ ያልቻለውን አብን እችለዋለሁ ብሎ መቀርቀሩ የልምድም የተመክሮም ስስነት ነው። የቅራኔ አያያዝ ጥበብብ ፍገትም ነው። 

ህወሃትን ከቤተመንግሥት ነቅሎ መቀሌ ያስገባው የአማራ ተጋድሎ ነው። ህወሃትም በይፋ ገልፆታል። በጣም የረቀቁ የሎቢ ተግባራት ተከውኖበታል። ከአገር ውስጡ ተጋድሎ ባለነሰ። ለዛ የአማራ ህዝብ አይደለም ትርፍ መሰቃው በቀረለት፤ መገደሉ ባባራለት፤ እረኛ ማጣቱ በቀረ፤ ድንፋታው በታገሰለት፤ ጦሮው በሰከነለት።

አሁን ኦነጋዊ ኦህዴድ ይድላው ተብሎ ሌላ ቅራኔ፤ ሌላ ሞት ለህዝባችን ሊደገስለት ፈጽሞ አይገባም። መጀመሪያ ህዝባችን የሞት ጥላው ይነሳለት። ስጋቱ ይቅርለት። በይፋ የታወጀው የዴሞግራፊ አዋጅ ይነሳ።

አዲስ አበባ የመላ ኢትዮጵያውያን ዋና ከተማ መሆኗ በይፋ ይታወጅ። ለተረሸኑት ወገኖቻችን የሃዘን ቀን ይታወጅ። ለተጎዱት ካሳ ይከፈል። የታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ ይነገር። የታሰሩ አማራዎች ይፈቱ። የአማራ ሊሂቃን የታሰሩት ካለምንም ቅደም ሁኔታ ይፈቱ። ይህን ሁሉ መከራ ወዝፎ ኦነግ ለጠራው ጦርነት ህዝብ እንዲሰለፍ ሁኔታውን ማመቻቸቸት እልህ እንዲገባ፤ ህዝብ በስሜት እንዲነጉድ ማነሳሳት ለህልውና የሚቆም ድርጅት ተልዕኮ አይደለም። የህልዋና ተጋድሎ ሰው ማዳን ነው ተልዕኮውም ጥሪውም። ሰውም ብቻ አይደለም የመንፈስ ውጥረትን፤ የመንፈስ መረበሽን ሁሉ እንዲሰክን ማድረግ ግዴታው ነው።

 እኔ ሥርጉተ ሥላሴ የህወሃት የበላይነት ካከተመበት ቅጽበት ጀምሮ አንድም ቀን በህወሃት ጉዳይ አቅም አባክኜ አላውቅም። ህወሃትን በተጋበው መልክ መርቶ ልክ ማስያዝ አገር እመራለሁ ብሎ ሃላፊነት የተረከበው መንግሥት ግዴታ ነው። ሊወቀስም፤ በሃላፊነት ሊጠዬቅም የሚገባው ኦናገዊው ኦህዴድ ነው። እምከሰውም ይህን አካል ነው።

 ህገ - መንግሥቱን ቢሆን መሻር ይችላል። ፓርላማውን መበተን ይችላል። ግን ይፈልገዋል የአማራን ጉስቁልና። ስለምን? እሱ ጸረ አማራ ስለሆነ፤ ጸረ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስለሆነ። ከህወሃት የባሰ ጨካኝ ነው በተፈጥሮው ኦነጋዊው ኦህዴድ። ጸረ የስሜን ፖለቲካም ነው ፖሊሲው።

በሌላ በኩል አብን አሁን ይጥፋ፤ አይወክለንም፤ አይመራንም የሚሉ መንፈሶችም ተገቢዎች አይደሉም። ያለ ነገር ነው መልካም። የሌለ ነገር የለም። ባለ ነገር ላይ ቆሞ ተጨማሪ ነገርን ማሰብ፤ አማራጭ መንገዶችን ማዬት፤ የጎደለውን መሙላት፤ የጎበጠውን ማቃናት ይገባል። አደብ፤ ስክነት የሚጠይቁ ጉዳዮች አሉ።

እርግጥ ነው ተስፋን 100% ማደረግም አይገባም። እንኳንስ ድርጅት ዛሬ እራስንም በዛ ልክ መመዘን አይቻልምና። አብን ከአንጃ፤ ከመከፋፋል ከዳነም መልካም ነው። በዬትኛውም ሁኔታ ለማንኛውም ነገር ሲሆን 49% በስተቀር ግን 50% በቂ ነው ተስፋን ለመጠበቅ።  

 

https://sergute.blogspot.com/2018/06/blog-post_77.html

አዲሱን የአማራ ፓርቲ ማን ወለደው?

https://sergute.blogspot.com/2018/06/blog-post_41.html

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን)

https://sergute.blogspot.com/2018/06/blog-post_44.html

የአብን መሥራች ጉባኤ ልዩ የምሥራች ነው - ለእኔ።

https://sergute.blogspot.com/2018/06/blog-post_10.html

እልል በል አማራ!

https://sergute.blogspot.com/2018/06/blog-post_36.html

ደስ ይበልህ ጐጃም።

https://sergute.blogspot.com/2018/06/blog-post_87.html

አብን አመራሩን መርጦ በተሳካ ሁኔታ ጉባኤውን አጠናቀቀ።

https://sergute.blogspot.com/2018/07/blog-post_90.html

ወይ ፍርጃ? ጋዜጠኛ ካሳሁን ይልማ ደግሞ ይወርድብናል? አማራን በሙሉ "ኦነጋውያን" ብሎናል፤

https://sergute.blogspot.com/2019/01/blog-post_28.html

ለጨለማው ሳጅን በረከት ስምዖን የጋዜጠኛ ፋሲል ልዩ ስጦታ¡ እንዲህ ይሰለቅ!

 

አመሰግናለሁኝ።

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።