የቆዩ ፁሁፎቼ ናቸው። ብሎጌ ላይ ተሰባስበው ይቀመጡ ብዬ ነው።
የቆዩ ፁሁፎቼ ናቸው። ብሎጌ ላይ ተሰባስበው ይቀመጡ ብዬ ነው። ሌሎች ብሎጎች ፖስት አድርገዋቸው ዬነበሩት። ትክክል ! ( ሥርጉተ ሥላሴ ) August 17, 2014, 7:43 am Next የውጭ ምንዛሪ ንዋየ - ኩብለላ ከሃገረ ኢትዩጵያ ወደ ባህር ማዶ ሃገራት ( ሚሊዬን ዘአማኑኤል ) Previous ኧረ ተው ኢህአዴግ ተረጋጋ !! “ ዴዣ ቩ ” – በአምስት አመቱ የተደገመ ታሪክ የጋዜጠኞችን ማሰርና ማሳደድ፤ ንግድ ቤቶችን ማሸግና ማዋከብ ከሥርጉተ ሥላሴ 17.08.2014 ( ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ ) ዛሬ ዕለተ ሰንበት እ . ኤ . አ 17.08.2014 ጀግና አበራ ሃይለመድህን ሲዊዘርላንድ ጄኔባ የገባበት 7 ኛ ወሩ ነው። ቤቴ ውስጥም ሰባት ሻማዎች እዬበሩ ነው። ይገባል አይደል ?! ፎቶው ደግሞ ፊት ለፊቴ አለ - አይቼም አልጠግበውም ! ወገኖቼ የኔዎቹ ልክ የስድስተኛ ወሩ ስናከበር እኛ ማለትም በ 17.07.2014 ከሰዓት በኋላ ዘንድሮ ወፉ ያላወጣቸው የማልዥያ አዬር መንገድ ዩክሬን ላይ ዳግም ሃዘን አደጋ የገጠማቸው ዜና ተደመጠ። አንድም የሰው ዘር ቁራጭ ምልክት ሳይገኝ አመድ ዶቄት ሆኖ መላ ዓለም በሃዘን ሰቆቃ የተደመመበት የጨለ መው ዕለት ነበር። እንደ ሰው ለተፈጠረ፤ ብቁ ህሊና ላለው ፍጡር ይህ ድንገተኛ አደጋ ቀለምም፣ ወሰንም፣ ደንበርም ሳይኖረው የሰው ልጅ በሙሉ ሃዘኑን በተለያዬ መልኩ ተጋርቶታል። የዚህ መከራ ቀን ፊርማ ሳይደርቅ ነበር በዕንባ ተሰቅዛ አሳሯን በምታዬው እናት ሀገራችን ኢትዮጵያ የዘረኛው...