የቆዩ ፁሁፎቼ ናቸው። ብሎጌ ላይ ተሰባስበው ይቀመጡ ብዬ ነው።
የቆዩ ፁሁፎቼ ናቸው። ብሎጌ ላይ ተሰባስበው ይቀመጡ ብዬ ነው። ሌሎች ብሎጎች ፖስት አድርገዋቸው ዬነበሩት።
August 17, 2014, 7:43 am
Next የውጭ ምንዛሪ ንዋየ-ኩብለላ ከሃገረ ኢትዩጵያ ወደ ባህር ማዶ ሃገራት (ሚሊዬን ዘአማኑኤል)
Previous ኧረ ተው ኢህአዴግ ተረጋጋ!! “ዴዣ ቩ” –በአምስት አመቱ የተደገመ ታሪክ የጋዜጠኞችን ማሰርና ማሳደድ፤ ንግድ ቤቶችን ማሸግና ማዋከብ
ከሥርጉተ ሥላሴ 17.08.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)
ዛሬ ዕለተ ሰንበት እ.ኤ.አ 17.08.2014 ጀግና አበራ ሃይለመድህን ሲዊዘርላንድ ጄኔባ የገባበት 7ኛ ወሩ ነው። ቤቴ ውስጥም ሰባት ሻማዎች እዬበሩ ነው። ይገባል አይደል?! ፎቶው ደግሞ ፊት ለፊቴ አለ -አይቼም አልጠግበውም!
ወገኖቼ የኔዎቹ ልክ የስድስተኛ ወሩ ስናከበር እኛ ማለትም በ17.07.2014 ከሰዓት በኋላ ዘንድሮ ወፉ ያላወጣቸው የማልዥያ አዬር መንገድ ዩክሬን ላይ ዳግም ሃዘን አደጋ የገጠማቸው ዜና ተደመጠ። አንድም የሰው ዘር ቁራጭ ምልክት ሳይገኝ አመድ ዶቄት ሆኖ መላ ዓለም በሃዘን ሰቆቃ የተደመመበት የጨለመው ዕለት ነበር። እንደ ሰው ለተፈጠረ፤ ብቁ ህሊና ላለው ፍጡር ይህ ድንገተኛ አደጋ ቀለምም፣ ወሰንም፣ ደንበርም ሳይኖረው የሰው ልጅ በሙሉ ሃዘኑን በተለያዬ መልኩ ተጋርቶታል።
የዚህ መከራ ቀን ፊርማ ሳይደርቅ ነበር በዕንባ ተሰቅዛ አሳሯን በምታዬው እናት ሀገራችን ኢትዮጵያ የዘረኛው የወያኔ አስተዳደር የጀግና ካፒቴን አበራ ሃይለመድህን ክስ በአምሳሉ በፈጠረው ፍትህ አልቦሽ ተቋም ምስክር አዳመጥን ብሎ የባዶነት ሙጣጭ ሂደቱን የገለጠልን።
ህሊና ቢኖር 202 ፍጡራንና ነፍስ የታደገውን ወጣት ተግባር ዩክሬን ከደረሰው ሰቅጣጭ አደጋ፤ አስደንጋጭ ዜና ጋር አነጻጽሮ – በማስተዋልም ፈትሾ፤ ቆም ብሎ ማሰብ በቻለ ነበር። አቅልም ህሊናም መግዛት ወይንም መሸመት አይቻል ነገር ሆኖ ነው እንጂ፤ „ተፈጥሮን ተመክሮ አያድነውም“ ይላሉ ቀደምቶቹ … ባልተራራቀ ቀንም እንደ ማልዢያውም ባይሆን የአውሮፕላን አደጋ ተከስቷል። ሰው ማለት ታላቅ የፍጡርና የፍጥረታት አውራ ነው። ፍጥረቱም – ጽንሰቱም – ውልደቱም ሆነ ዕድገቱ ረቂቅ ነው። የሰው ልጅን የነገረ ፍጥረት ረቂቅነት በሰው ልጅ ህሊናዊ ቀመር ወይንም ፍለስፍና ሳይንስ ሊደፍረው ከቶውንም አይችልም። ለወያኔ ደግሞ ሰው ማለት ሸቀጥ ነው። እሚገዛ – እሚለወጥ – እሚሸቀጥ እንዳወጣ በጉልት ገብያ የሚቸበቸብ። ባለፈም እንደ አውዳመት ዶሮ ባገኘበት አርዶ ባሰኘው ቦታ የሚጥለው የበቀል ማስከኛው፣ የደም ጥማቱ እርካታ ማወራራጃ – መፈተኛ – መሞከሪያ ….
ስለሆነም አረሙ ወያኔ የበለጠበት ሰው ሰራሹ ቆርቆሮ በሰላም አርፎ እስከ ዓይን ጥርሱ ተረከቦ ግን በጥቃቅን ወጪዎች ስሌት እንዲህ ይዳክራል። ይህ ነው የወያኔ የስብዕዊነት፤ የዕንባ ተቆርቋሪ ድርጅት በሚር/ ማዕረግ አደራጀሁ እያለ የሚያላግጠው። ሰው ለወያኔ ከእንሰሳትም፤ ከማሽን መሳሪያም እጅግ ያነሰ ፍጡር …..
አይደለም ሰው ከነህይወቱ ተርፎ። አውሮፕላኑ ብቻውን አደጋ ቢድርስበት እንኳን ሰው ተረፈ ተመስገን ይባላል። በሌላ በኩልም ዬትልቁ የሰው ልጅ ተፈጥሮ ሞተሩ መንፈሱ ነው። በዚህም ዘርፍ እጅግ በጥንቃቄ ነበር ትክክል የከወነው። አደጋ ሲደርስ ለዛውም ሰማይ ላይ ያቺ የግቢ ውጪ ነፍስ ቆይታ እራሱ በምንም ምንዛሬ ሊሰላ ከቶውንም አይችለም። ግን ለአድናቆት ቀርቶ እንደ ሰው ለማሰብ ለተሳነው የዘረኛው አፓርታይድ የወያኔ ከፋፋይ ሥርዓት ለፍጡራን ደንታ ቢስ በመሆኑ ስሌቱን በጎጥና በሂሳብ እንዲሁም በጭካኔ መንፈስ እንዲህ ያወራርደዋል። እንጠብቃለን …. አዬር አልባው ፉኛ ችሎት የሚሰጠውን ብይን ….
ካፒቴን አበራ ሃይለመድህን ከመጠን የዘለለውን ረገጣና ግፍን መክቶ – ጥቃትን ለማውጣት ትክክል ሆኖ የተፈጠረ ብቁ ዜጋ ነው። „አሻምን“ የገለጠበት መንገዱ በስክነት ከእጁ በገባ ዕድል ለትክክለኛው ጊዜ ትክክለኛውን ሁኔታ፤ ለትክክለኛው አቅም ትክክለኛውን የኃላፊነት ደረጃ፤ ለትክለኛው ውሳኔ ትክክለኛውን ችሎታ መግቦ ትክክልን አቅም መግቦ፤ በትክክል ንጹህ አዬርን አስማምቶ ሰጥቶ ካለ ብክነት ንጥርነትን በስኬት አወራርዶ ዕውነት – ትክክል ሆነ ከደባባዩ ላይም ዋለ። ፍትህ – ርትህ – ፍርድ ይሏችኋል ይህ ነው። የተገፋ -የተገለለ መንፈስ በዚህ መልክ የጠላቱን ዕላቂ መንፈስ ያወላልቃል።
ሲፈጠር ተስተካክሎ ስለነበረ በዝምታ የከወነው ድንቅ ተግባር አቋሙን፤ ውሳኔውን፤ ድርጊቱን፤ ችሎታውን፤ ለትክክል ውስጥ ሸልሞ ለዘመኑ ትክክሉን የጀግንነት ጥሪት ባለቤት ለመሆን እንሆ ቻለ። አረሙ ወያኔ እንዲህ ተቆፍሮ ተቀብሮ እንደ ኖረ አውሬ ያዬውን ሁሉ በሽብር ሴራ ፈርጆ መቆሚያ መቀመጫ ላሳጣው ግዑፋን ትውልድ የደም መላሹ ወጣት አንዳዊነትን በአሃታዊ ፍላጎት ቀምሮ ድልን ያበለገ እራስ እግሩ ፍሬ ዘር እርምጃ ነበር የወሰደው።
ጀግናዬ አበራ ሃይለመድህን ይህን ዬታሪክ ዕለት እዚህ ሲዊዘርላንድ ካስመዘገበ ጀምሮ እኔ በግሌ አድርጌ የማላውቃቸውን ነገሮች እፈጽማለሁ። እንዴት ቢሉ …. ሁልጊዜ ጉግል ገብቼ ምን የአውሮፕላን ክስተት እንደተፈጠረ አያለሁ። በሰማይ ላይ አውሮፕላን ሲበርም ቀና ብዬ አይና በሰላም ያግባችሁ እላለሁ። ከአደጋዎች ሁሉ የከፋው ሰማይ ላይ አመድ – ዱቄት ሆኖ ለወሬ ነጋሪ እንኳን ሳይበቁ መቅረት ነውና ለህይወቴ በዚህ ዙሪያ አዲስ ምዕራፍ ነው ማለት እችላለሁ። ማለት ልክ ከቤተሰቤ አንድ ሰው በዚህ ሙያ እንደተሰማራ ያህል ነው ውስጤ እያዳመጠ ያለው።
ዓይን ያለው ህሊና፤ መንፈስ ያለው ፍላጎት፤ ተስፋ ያለው ችሎታ እንዲህ ካለምንም ግድፈት ሲከውን መምህርነቱ፤ አብነቱ ለእኛ ብቻ ሳይሆን ዓለምአቀፋዊ ነው። ያኮራል ወንድም ጋሼ – ተባረክልኝ!
አንድ ሰው ብዙ ነው። ሰው መኖርን አስቦ መኖር ሳያማክረው ወይንም መኖርን ሳይወስንበት በእንዲህ ዓይነት አጋጣሚ ማለፍ ዘላለማዊ ጸጸት ነው። ጀግና አበራ ሃይለመድህን በዞግ የከረፋ አስተዳደር መከራውን – መከፋቱን – ቅሬታውን – መሸከም አለመቻሉን የገለጸበት መንገዱ ሆነ ከማናቸውም ጉዳት ያዳነውን የሰው ልጅ ሆነ ንብረት ስሌቱን በሂሳብ መተመን ዕብንነት ይመስለኛል።
ጀግናዬ – ለተፈጠረበት መክሊቱ – የልጅነት ምኞቱ፤ የወጣትነቱ ተስፋው አፈጻጸሙና ሂደቱ እንከን የማይወጣለት ትክክሉ ልኩ ነው። የኔው ጀግና አበራ ሃይለመድህን እንኳንም ተፈጠረ። ደመ ከልብ ሆኖ ለቀረ ወገን ፊት ላይ ሆኖ እንዲህ መከተ።
ዛሬ እንዲህ በአንድ የመንደር አስተዳደር ሀገር ተከትፋ እየታመሰች ባለችበት ወቅት፤ ልጆቿ በዬሄዱበት እዬታደኑ በመርዝ ጋዝ መሞከሪያ በሆኑበት ወቅት፤ አልፎ ተርፎ ውጪ ያለነውን ብዕርና አንደበት ለመዝጋት፤ አብሶ የነገ ተረካቢ ወጣቶቻን ግንባር ቀደም፣ ትንታግ፣ ሀገር ወዳድ የነፃነት ትግሉን ቤተኞችን ከእንቅስቃሴያቸው ለመገደብ ከፍተኛ የሥነ – ልቦና ጦርነት በታወጀበት ዘመን እንዲህ ሞግድ ግጣሙን ሲያገኝ የሰማይ ታምር ነው። ጀግንነትና አደራ ተጋቡ። ቃላቶች ሁሉ ሰልፍ ቢወጡ መተርጎም የማይችሉት ብሄራዊ የሀገር ፍቅር እንዲህ ፈክቶ በተባ ድፍረት በትክክል ተከውኖ አዬን።
የኔዎቹ ታስታውሱ እንደሆን ቱቦው የዘር አስተዳደር ቀለብ ተሰፋሪዎች ልዑክ ሆነው እዚህ ሲዊዘርላንድ መጥተው በነበረቡት ጊዜ „ታሟል“ ይሰጠን ነበር ጥያቄያቸው። አሁን ደግሞ „ጤነኛ ነው“ በወንጀል ይጠዬቃል። አያችሁት የበቀል ብቅሉ ወያኔ ጥልቅ ሴራና የቋሳ ጉድጓድ። ፍርዱም ባለጉዳዩ በሌለበት ይታያል። የሥነ -ልቦናውም ጦርነት ይቀጥላል። ግን በማያውቁት ተፈጥሮ ላይ ስለሆነ ይሄን አጅሬ ሃይልዬ መንፈሱን ከቀለሙ ጋር አስተጋብቶ የሀገሬውን ቋንቋ ጥናቱን አስከንድቶት ይሆናል – ትክክል ነዋ! ጠፈፍ ብሎ የተፈጠረ የህሊና ዓይንና ጆሮ።
አይደለም እነሱ እነ – የዘር ብልቂያጦች፤ የዘር በሽተኞች ቀርቶ የወለዱት አጅግ በሚደንቅ እንክብካቤና ሥነ – ምግባር ኮትኩተው ያሳደጉት ክብርት እናቱ ወ/ሮ የህዝብአለም ሥዩምና የተከበሩ አባቱ አቶ አበራ ተገኜ አያውቁትም – በፍጹም። የማያውቁትን ልጅ ነው ወልደው ያሳደጉት። እርምጃውና ዕቅዱ፤ ዕቅዱና ውጤቱ፤ ብልህነቱና ላቂያነቱ በዚህ ዘመን ከቶ የማይተሰብ ነው። ደሙን ሲመልስ ኮሽ ሳያደርግ በእጥፍ ድርብ፤ እራሱንም ጠብቆ – ክብሩንም ጠብቆ – የሙያውን ክህሎት ጠብቆ – የሙያውን ሥነ ምግባር ሳያጓድል እንግዶቹን እንዳከበረ፤ የኢትዮጵያዊነትን ጠንቃቃነት በናሙናነት ጠብቆ ታሪክንም አልምቶ ነው። ቀበቶውንስ እሱ ይታጠቀው …. ትክክሉ ነውና። ወንድነቱን እሱ ይነገር ትክክሉ ነውና። ተግባርም ይናገር ትክክሉን አግኝቷልና። ተመስገን – ተስፋዬ!
ካፒቴን አበራ ሃይለመድህን መሰደድን ሲተረጉመው በጠላቱ ጦር ሰፈር ላይ የመንፈስ ትቅማጥ አውጆ፤ ጥቃቱን አስገድዶ ግቶ -፤ ለጎጠኛው ወያኔ – ቁርስ – ምሳ እራቱን ሽንፈትን – አስጎንጭቶ። የሴራ – የሸር – ዬኢጎ – የምቀኝነትን ትብትቦችን በተከደነ መንገድ አፈር አስግጦ። መገለልን – በተግባሩ አሸንፎ፤ እንደ ወያኔ ላለ ሙጃ አስተዳደር ትክክሉ እንዲህ ዓይነት የዝምታ ገድል ነው። ጠላት ባለሰበው – ባለወጠነው – ባላተኮረበት መንገድ ሆድ ዕቃውን እንዳልነበር አድርጎ ማስማጥ – ማስመጥ። ማጥቃት እኮ መልኩም ዘርፉም ረቂቅ ነው። ረቂቅነቱን እንዲህ በትክክል ኢትዮጵያዊነት መሸነፍ አለመሆኑ ይተረጎማል። ለመክሊቱ ያደረ ፍጥረት ትክክልነቱን በድርጊት እንዲህ ያበሥራል። የኔ ጌታ – የእኔ አባት – የእኔ ውድ – ዬእኔ ብርቅ እግዚአብሄር አምላክ የልቦናህን አሟልቶ ያሳዬኝ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ውድድድድ ….
ክብረቶቼ የምትችሉ በፌስ ቡካችሁ – በቲዩተር አካውንታችሁ ጀግናችሁን ከፍ አድርጋችሁ ሰንደቃችሁ አድርጋችሁ ብተውሉ ቤታችን አውዳችን ጠረኑ ጀግና – ጀግና ….. ይመቻችሁ። መሸቢያ – ጊዜ።
ጀግኖቻችን የመንገዳችን መብራቶች ናቸው!
ደሜን ሳዳምጠው ውስጤን አገኘዋለሁ!
ለእኔስ ሰው ሆኜ መፈጠሬ ብቻ ይበቃኛል!
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
የጎረና ጉርና –ነዳላ (ሥርጉተ ሥላሴ)
Next ኢትዮጵያዊነት ማለት
Previous ከውጭ የተላከ ያልተመዘገበ ገንዘብ /የሐዋላ ቅሸባ
ልብ አምላክ ዳዊት „ህግ ተላላፊዎችን ጠላሁ“ አለ።
ሱባኤውም ተጠናቀቀ – መልስ ይሰጥበት።
ከሥርጉተ ሥላሴ 25.08.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)
ሥርጉተ ሥላሴ
ይድርስ ለጸሐፊ ጌታቸው ረዳ ካሉበት። እንደምን አሉ? ደህናነዎት ወይ። ደስ ሊለዎት የሚገባ ሊያሰተላልፉት የሚፈልጉትን መልዕክት በማስተላለፈዎት ሳይሆን እራሰዎትን ፈልገው ከመሸ በማግኘተዎት ነው። እንኳን ለዚህ አበቃዎት! አሻቅቦ መናገር ከመንፈሴ ዕድገት ውጪ ቢሆንም ልክን ማወቅ ከልክ የሚያድርስ ስለመሆኑ ተምሬ ስላደኩ አቻውን ዬፍላጎተዎትን እንሆ – ይረከቡኝ!
„ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል“ ወይ ዘመን ምኑን ጉድ ነው እዬዘለዘለ ያለው? እግዚአብሄር ይይልህ አይዋ ዘመን ምን አለበት ጉግልን ባትጋፋው?
የኔዎቹ እንዴት አላችሁልኝ። ጥያቄ ተጠዬቁ እስቲ። ደግሞ ብለው ብለው ላልጠፋው እህል እውሃ በነጭ ሀገር ብዕርና ብራና ስንቃቸው አብሾ ሆነ እንዴ?
አልኳችሁ ወዳጆቼ አጣደፉኝ። ስሄድ ካላሆነ ቦታ ገባሁ። ከዛንላችሁ ቀጥ ብዬ እርእሱን ይዤ ኤዲተር ካላው ወዳጄና ረጃጅም ትንተናዊ ጹሑፍ በማወጣት ወደ ዬሚታወቀው ኢትዮ ሚዲያ ጎራ ስል ተዛም ዝክንትሉ ብራና የለም። ያው እንደፈረደብኝ ተመልሼ እንደ ነገሩ ከብትክትኩ ጋር በባዕቱ መተያዬት አይቀር – ተያዬን። እርእሱና ፎቶው በቂ ነበር „የናዚ ኔት ወርክ“ ዘመናይ ነዎት — ዖዬ!
ከዛ ደግሞ አነበብሽው? ምንስ ተሰማሽ መጣ? ስለ ወጣቶች „ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ“ በመሆኑ ሰቀጠጠኝ። እኔ ለወጣት የነፃነት ትግሉ ቤተሰቦች ስስታም ነኝ። እንዲሁም ቀጥ ያለ አቋም ብቻ ላላቸው የመወያያ መድረኮችና ሙሁራንም እጅግ ቀናተኛ ነኝ።
በተረፈ እኔን በሚመለከት አደራ አበደች እንዳትሉኝ። ደስ አለኝ። እዬሳቅኩኝ ነበር የተያዬነው። በቃ የጠላት ጎራ መንፈስ እንዲህ በአንድ ጹሑፍ ትቅማጥ ሲይዘው ማዬት የምር ምኞቴ ነበር። ሆድ ዕቃው ወስፋቱ የተንጫጫ ሲገኝ አጋጠመ ነው። ለዚህ ነበር እኮ እኔ የጻፍኩት። በቃ! ሁልጊዜ ፋሲካ የለምና እንደ ወትሮው መንፈስን ከአንድነት ኃይሉ ማፈናቀል ያልቸል ደካማ መሆኑ ደግሞ ተከታታይ መረጃ ወገኖቼ ሲሰጠኙ የበለጠ ሐሴት አገኘሁበት። አዎና! እኔ እኮ ስጽፍ በውስጤ ሁኜ ነው። የፓርቲ አባል ዬማልሆነውም ለዚህ ነው። በዲስፕሊን መታሰር አልሻም። ፓርቲዬንም ማስነቀስ አልፈልግም። እንዲህ በልቅ ዓለም መኖር፤ በምንም ነገር ያላታሰረ ነፃነት እሻለሁ። ባሩዱ ተነጣጠረ ዓላማውን ሳይስት ጦሮዎ በጠላት ሰፈር ልኮ እንዲህ ቆርቆሮውን ቢና ጢናውን አወጣው። ዓይነተኛ የውስጥ ተቆርቋሪ ይሄው እንዲህ ከእንቅልፍ ጋር ተጣልቶ ጎልቶ አውሎ ያሳድራል ጌታውን ሲያስጨር። ተመስገን – አነቃነቀ – ናጠም።
በግራ ቀኝ ስውርና ረቂቅ ሴራ በጠላት እጅ ለወደቀ – ስለ ራሱ ቆሞ ሊናገር ለማይችል፤ በጠላት እጅ በመንፈስ ማደንዘዣ የበቀል መርዝ ሙከራ የሚሠራበት ታላቅ ወገኔ በሌለበት ቦታ ስለ እሱ ተናግሬ ወንጀለኛ መሆን ክብር ነው – ለሥርጉትዬ። ይልቅ ያልተገባኝን ክብር ባልተገባኝ ወቅት ሰጡኝና ከነፃነት አባት ጋር አንጠለጠሉኝ። ከአንድ የነፃነት ሙሴ – ሰማዕት ጋር ደረጃዬ አይፈቅድም። ይህ ባይሆን ጥሩ ነበር። ይሄ ወቅትን ጊዜን ያልጠበቀ ከፍ ማለት አልወደወም። አጉል መንጠራራትን ፈጥሮ እሸት ቅመሱ ሳይባል ዘጭ ያደርጋልና። ለዚህም ነው በብዕር ሥሜ እምጽፈው። እንጂ እኔ እህታችሁ በተፈጥሮዬ ደስታ ላይ አልገኝም። ከተሸነፈ ወይንም ከተጠቃ ጋር ግን ማን ይዞኝ። ባለፈው ዓመት የተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እዚህ መጥተው አባላቱን ካነጋገሩ በኋላ እንዲሁም በተለዬ ሁኔታ ለሚያግዙ የነፃነት ትግሉን ግንባር ቀደም „አክቲቢስቶች“ ነው የሚባለው ከእነሱ ጋር እንደተወያዩም አዳምጬ ነበር። አሁን ደግሞ ፎቶም አይቻለሁ። ለእኔ ይህ ጉዳዬ አይደለም። ድንበር አለው ኑሮዬም – ተፈጥሮዬም።
አንድ ነገር – እንዲህ ሆነላችሁ ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ ታስራ በነበረች ወቅት በዬሳምነቱ እደውል ነበር ለቤተሰብ። እምችለውን የመንፈስ ደጋፍ አድርጌያለሁ ብዬ አስባለሁ። ስትፈታ ግን አልደወልኩም። ኢሜሏም አድራሻውም አላስፈለገኝም። አላገኘኋትም።
ለእኔ ቁም ነገሩ ጠላት እንዲህ ጥቃት ሲፈጽም፤ ሰብዕዊነትን ሲዳፈር፤ የዜግነት መንፈስ ሲጨፈለቅ፤ ህግ በጠራራ ፀሐይ በጉልበተኛው ወያኔ ሲረሸን የእኔ ብዬ መቀበል – በግንባር በባለቤትን በዕውነታዊ ውስጥ መገኘት ነው። እንዲያውም ጀግናዬ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የግል ህይወታቸውን ከተከበሩ ወንድማቸው ከሰማሁ በኋላ የበለጠ ነው እኔን ዬመረመረኝ። እንዲህ በአደገ ሀገር በአንዲት ክፍል ቤት ሁሉንም ዓይነት አማራጭ ደፍሮ ለመሞከር እራስን ረስቶ ታጥቆ መጠበቅ ልዩ ጸጋ ነው። መታደል – የእውነት። እና መከራን ለፈቀደ ወገን መሰከራችሁ ነው „ናዚነቱ ሆነ ጉዲትነቱ“። ወቅትንና ጊዜን ማድመጥ በሚመለከት ለሽበት መንገር ወንዝን አሻቅበህ ተጓዝ እንደማለት ከቶ ይሆንብኝን? ግድፈቱ ዘመን ይቅር አይለውም – ጌታው። ግራጫ አለቀሰ – እዬተቀነሰ – እዬተበጠሰ …. ከቶ ይህቺ ስንኝ ተመቼዎትን?!
ሌላው ከትክት ብዬ በፈንጠርጣራ ጥርሶቼ የሳቅኩት ደግሞ በነፃነት ሀገር ፈቃድ ጥዬቃ መዝመት ነበረብን ወደ ዘመን ሰጡ ጌታው። ወይ አቅምን አለማወቅ?! „ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል“ ይላል ጎንደሬ ሲተርት። ሃሳብን በሃሳብ መታገል የአባት። ድንበር ዘለል የጎጥ አገዛዝ ለዛውም ነጭ ሀገር ግን እማይቻል ልግጫ ነው። ዝለት – በፍዘት ይሉታል ዕብኑን ህልም። ለነገሩ የጎጥ በሽታ ከዚህ በላይ መሄድ አይችልም … በጣም ረጅም ጊዜ እኮ ነው፤ 23 ዓመት መስሎ – ተመሳስሎ መኖር መርግ ነው አቅልን የሚፈትል።
መኖር ማለት መኖር የለገሰውን ተፈጥሯዊ ጸጋና ክህሎት በጊዜ አውቆ ተጠቃሚ መሆን መቻል ነው። መቻል ደግሞ እራስን ሆኖ እንደ ራስ ሆኖ በመጤ እንደራሴ ሳይጠቀለሉ እንዲህ አደባባይ ላይ ወጥቶ ውስጥን ማስጎብኘት ነው። ይህ መሸቢያ መንገድ ነው። ስለምን? ድርጀቶችን ተጠልሎ ጥቃት መፈጸም ሆነ ወቅትን አስታኮ ማመስ ከምድር በታች ይቀበራሉና። ብዙ ድርጅቶች ታሪካዊ ስህተት የሚፈጽሙት በእንዲህ ዓይነት ዝበትና ግብዝነት በጎበኛቸው መንፈሶች የዋህ ወገኖች በቅንነትና በአዎንታዊ ተመልክተው ይጥቅማል በማለት ሃሳብን ስለሚያስተናግዱ ነው። ስንሰበሰብ ሲበተን፤ አፍሰን ስንለቅም ወይንም ለቅመን ስናፈስ የኖርነው … በዚህ ጆሮ አልቦሽ መንገድ ነበር።
ከእንግዲህ ያ ይናፈቅ የነበረ ዬናሙናዊነት መለዮ ልዑቅ ክብር፤ ተወዶና ተፈቅዶ የተለገሰው ንጡር ፍቅር፤ በብዙኃኑ የተጫነለወት ልዩ ዘውድ ተምልሶ ዳግም አይገኝም። ቁርጠዎትን ይወቁ – ጌታው። ዬትኛው ጌታቸው ረዳ? የኛው ወይንስ የወያኔው? ….. መለያወት ላቂያ ፍቅር ነበረው። ጌጥማ አቅርቦትና ልዩ ዜማዊ አክብሮት – ቅርበትም በነኑ – ስለፈቀዱላቸው። የአብነት ት/ቤት – ነትወትንም ለዘለዓለም ከረቸሙት – ምነው እንዲህ – የጤና?! ከብዙኃኑ ቤተኝነት መውጣትስ ይመች ይሆን? ይህ ግንፍል ግንፍል ማለቱስ — ?
ማንም ሰው እንደ ሰው በምድር ላይ ብዙ ነገር ሊኖረው ይችላል። ከሁሉ የሚልቀው ግን የህዝብ ፍቅር ሃብት ነው። ፍቅር የተጠረገ ልብና ብቁ አስተዳዳሪን ይሻል። ፍቅር አድማጭና ተናጋሪም ነው። ስለፍቅር መሸነፍም ውስጥን እንደ ተፈጥሮው እንዲኖር መፍቀድ ነው። ይህን ሁሉ ዘመን በነፃነት የኖረ አባወራ በመዳፉ ላይ ያለውን የህዝብን ፍቅርን በአግባቡ ለማስተዳደር አቅቶት ወይንም ግራጫዊ ዘመን ዘለቅ ተመከሮው መተርጎም ተስኖት እንዲህ እናት ሀገር ማቅ ለብሳ በማህጸኗ የደም ዕንባ በምታለቅስበት እጅግ በጠቆረ ዘመኗ፤ በከፋት ዘመኗ፤ ሾልኮ መቅረት ….. ብልሃት የሌለው ቅላት ነው ለእኔ።
እኔ ሰው ነኝ። ከዚህ በላይ ስለ እኔ የሚተረጉም ምንም አልፈልግም። እርስዎ ግን አስፈለገዎት። በአደገው ሀገር ተቀመጠው ዘመን የሰጠውን፤ የፈቀደውን ፍትህና ነፃነት አግኝተው እዬኖሩ በጣም ታች ወረዱ። ጎሳ ላይ -
ዘመነዎትና ተመክሮዎት ውስጥዎትን ለማሸነፍ አቅልም - አቅም አነሰው። ምነው ቸኮሉ?! ኩታረነቱን* ለልጅ መስጠት ይገባ ነበር። ምን ቆጠቆጠዎት? ምን እንዲህ አንተከተከዎት? ምን አበሳጨዎት? ምን አቅለዎትን ነስቶ በነፈሰበት መረጃ አካልዎትን የገዛ ቤተሰቦወትን ለመወንጀል ምን አስነሳዎት? የምን ጥድፊያ ነው ትቅማጥ እንደያዘው ሰው?
እኔ ልመልሰው። እስከ ዛሬ ድርስ እራስዎትን አሸንፈው አልኖሩም ነበር። ፍላጎቶዎትና እርስዎ አብራችሁ አልነበራችሁም። ወይንም ውስጥወትን አያውቁትም ነበር። ከዚህ የከፋ ነገርም እኮ ሊመጣ ይችላል። በደለኛ እስካለ ድረስ። ሰው እራሱን ሳያውቅ ወይንም እራሱን ሳያዳምጥ ሲኖር አንድ ቀን እንዲህ እራሱን ፈልጎ ያገኛዋል። እሱን ያገኘው ዕለት እንዲህ ይቧርቃል። ሜዳውም ሸንተረሩም አይበቁትም። ይጠበዋል። ታፍኖ እንደ ኖረ ስለሚቆጥረውም ይተነፍሰውና እንዲህ ይወጣለታል። እንኳን ለዚህ አበቃዎት – ጌታው። እንጡሩብ አዘለለዎት …. ነዘረዎት – ሰረሰረዎት።
መመካት ቢኖር አብነት ላለው – ትንሽ ብጣቂ የመንፈስ ማረፊያ ዬብትን አፈር ተቆርቋሪነት ቢኖር ነበር። አንድ የመንደር ወመኔ ስብስብ የፈጸመው ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚል ጣዕም ቢኖረው፤ ወይንም ሰውኛ ያለው ጠረኑ ቋት የሚሞላ ተግባር ላይ የሚታይ ተጨባጭ ነገር ቢኖር በነበር። ዕድሉን ቢጠቀምበት በነበረ። ጭብጦ አኮ የለም። የፈለሰ = የመከነ – የተፋቀ፤ የፈሰሰበት ዘመን ጥልማሞተ ነው የወያኔ ያረገዘው ዘመኑ። ምን ተነስቶ ምንስ ተጥሎ? …. በወያኔ ያልተበከለ ወይንም ያልተጠቃ – ያልተቃጠለ ተቋም ምን አለና? መርዝ!
ጸሐፊ ጌታቸው እረዳ እንደ እርስዎ ያለ ታላቅ የዕድሜም ባለጸጋ፤ በፖለቲካ ልምድ የበለጸገ አባወራ፤ በቀለም ትምህርትም ሙሑርነቱ ታክሎበት „ከትግራይ የወጣ፤ ከትግራይ የተፈለፈለ እጭ’፤ ትግራይን ነፃ እናወጣለን ብለው የተነሱ ጎጠኞች፤ ሀገርና ትውልድን የገደሉ፤ ትውፊትና ማንነትን የቀበሩ፤ የሀገራችን አካል የጎረዱ፤ ዜግነታችን የጠቀጠቁ፤ በዘር እዬነጠሉ ያጠቁ፤ እረቂቅ ዛሬ የማናያቸው ነገ ግን እዬፈነዱ ሀገር አልባ የሚያደርጉን ደባ የፈጸሙ፤ ሰንድቅዓላማን የተዳፈሩ – የተጸዬፉም፤ ባህልን ካለርህራሄ የጠቀጠቁ፤ ግብረ ሰዶምን ያበረታቱ፤ የዕምነት ምኩራቦችን በትዕቢት የረገጡ፤ በወገኖቻችን ላይ አራዊታዊ ተግባር የሚፈጽሙ፤ ሀገራቸውን በጠላትነት ፈርጀው ተቋማቷን ሁሉ ያከሰሉ፤ ጥርጣሬን ያነገሡ፤ ምቀኝነትን ያፋፉ፤ አብሮነትን በተባይ ያስወረሩ….“ ምኑ ያልቃል እንዲህ አውሎ ጎልቶ በሚያሳደር የብዕር እልልታ ጎሽ ያሰኝ ነበርን? ህሊና ቢኖርስ አንገት ያስደፋል። ያሳፍራል?
ብዕረኛው ቢያውቁትና ቢገነዘቡት ዛሬ ወያኔ በሚፈጽመው በደል የተፈጠረበት መሬት ያለው ንክኪ ሁሉ ቁስል ነው። መግልን ፈቅዶ ያዘለ። አጋጣሚው ቢሾልክ እንዴት እልቂትን በቀለን ታግሶ ምህረት ማውረድ እንደሚቻል በዚህ መስመር ነበር ምርምር ሊያደርጉበት የሚገባ። እኛ አንቅልፍ የነሳን ይህ ነው። …. ጀግና አንዳርጋቸው ጽጌን የማድንቅበት ትልቁ መስፈርቴ ይህን የተፈራ አምክንዮ ሁሉን ችለው – ዘለፋውን ሁሉ ተሸክመው፤ ወጨፈውን ሁሉ ተቋቁመው ደፈረው መግባታቸው ነው። ጤናማ የመተንፈሻ ቧንቧ ለመዘርጋት አብነቱ ነበሩ – ቀንዲል።
እንደ እርስዎ ያለ በልምድና በተመክሮ ከለማ ወገን እምንጠብቀው የነበረ የበቀል ተጠቂ ተቋማትና ወገን ለማዳን የትግራይን ዬኢትዮጵያዊነት ጉልተኝነት ለማስከበር ፊተኛው ረድፍ ላይ ቆመው እሳቱን ቋያውን እንዲቀበሉ ነበር። ተዉ! በቃ! በዛ! እንዲሉ ነበር። እንጂ እንዲህ አይጥ የበላው ጨርቅ የመሰለ ብትክትክ ያለ፤ በዬቦታው የተቦጫጨቀ፤ ዘሎ ፈርጦ ዪሚወራጭ የነገር ጅምናስቲክ አስተሳሰብ ይዘው ብዕርና ብራናን ሲያገናኙ አንገትን ቀና አድርጎ ለመሄድ ከእንግዲህ ጋዳ ነው የሚሆነው። ፍሰኃና ሰናይ ከሆነወት —— ስ
እውነቱን ብነግረዎት ለትግራይና ለትግራይ ህዝብም የእርስዎ መስመር መዳህኒቱ አይሆንም። በፍጹም። …. ደግሞስ ወጪውንስ ጉዞውንስ እንዴት ቻሉት? – የቀረዎት ሀገር፤ የቀረዎት ሰው፤ የቀረዎት የነፃነት መንፈስ የለም። አዳረሱት። ግን ብዕሮዎት እንዲህ ዟሪ ናት? … ኧረ እንዲህ ስድ አደግማ አያድረጓት!…. የጠብ ተጠማኝም አያድርጓት። እ! መንጠራራቷም ልክ ቢኖረው መልካም ነው። ምን አልባት እርስዎን እረስታ በራሷ ኢጎ መጪ ብላ ይሆን? ኧረ በፈጠረዎ ልጓም ቢጤ ይፈልጉላት …. እዘጭ ያደረገችው እኮ ትልቁን ዳቦ …. እም! አቤት ያንት ያለህ! ከስንቱ ረገጠች? ደግሞ ጠላት ማብዛት ግጥሟ ሆኖ አረፈ — አፈርም ላይ ፈርፈር አለች …. ተጋግጣ – ህም!
አሁን ባለው ሁኔታ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ጎሽ እንኳንም የኛ ሆናችሁ የሚያስብልበት ጊዜ አይደለም። የትግራይን ክብርና ዝና የፈገፈገ የጎጥ ስብስብ ከረፋህን ብሎ ትግራይን ማዳን ማለት ለእኔ ኢትዮጵያን ማዳን ስለሆነ፤ በዚህ በጣም የተጋ ተግባር በተከታታይነት በተከወነበት ነበር። መሬት ያያዘ፤ ጭብጥን የተንተራሰ፤ ሥልጡን – እርጋታ የከበከበው የምርምር ድርጊት ያስፈልግ ነበር። የማዳን ዘመቻ እራስን አቅልጦ …..
የብዕረዎት ጠብታ ግን ጦርነት ነው ያወጀች ….. ይገባልን? በመገዳደል፤ በመጨፋጨፍ፤ በጥላቻ በተከዘነ ጎጣዊ ጉዞ ሀገርና ህዝብ ይድናሉን? ለመሆኑ ሽበተዎት በውስጥ ወይንስ ውጪ ላይ ነው ያለው ይሆን? ለሰው አይደለም ለታሪክ – ለትውፊት – ለሀገር – ለሰንድቅአላማ – ለአደራ -ሽምግልና በሚያስፈልጉበት ጊዜ እንዲህ ያለ መላቅጡ የጠፋ የጎረና ጉርና ነዳላ አስተሳሰብ ይዞ መቅረብ ከቶ ወደ ዬትኛው ዕድሜዎት ላይ ተመልሰው ይሆን?
አሁንም አልጠገቡም ይጽፋሉ። ስህተቶችን አነባብረው እዬካቡ ነው። ቃላቶቹ አምጸው – ተንደው ቢደርምሰዎትስ? ሞትንም እርሰዎም ብዕረዎት እረሱ መሰል። ሰው ያዘነበትም ሰው ….. የበቀል አምላክ አለና ይበቀላል። „ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ“ አድርገው ጭንግፍ ያደረጓችን የነገ ወጣቶች እኛ ህይወቱ ባይኖረን ወላጆቻቸው ያነባሉ — ሀገርም ….. ታነባላች። ጊዜያቸውን – ጉልበታቸውን – ገንዘባቸውን – እያፈሰሱ፤ ደፍረው ቅራኔ ውስጥ እዬገቡ፤ ሌትና ቀን በሚተጉ የነፃነት አርበኞች፤ ወጣትነታቸው ሳያውቁት አልፎ ሲሄድ እያዬዩት ኑሮን ንቀው ነገን በተግባር በሚያደምቁት ላይ …. እነዚህ ፎቷቸውን በማናለብኝነት የለጠፏቸው ወጣቶች አንድ ነገር በህይወታቸው ቢደርስ – ተጠያቂ መሆነዎትን ግን ልብ ብለውታልን? …. ከልበዎት ሆነው ይስቡት። ጹሑፎዎትንም ደግሞው ያንብቡት። ተኝተውም ይሰቡ። ግን ግን እርሰዎ ነው የጻፉት ወይንስ ኮበሌው ጌታቸው ይሆን የጻፈለዎት …..? ኦ አምላኬ! ተሳህለነ!
„ኢትዮጵያዊነትን ሃይማኖታቸው“ ስላደረጉ ብቻ ፎቷቸውን የለጠፉት ወጣቶች ወያኔ አፍኖ ወስዶ ምን እንዲያደርጋቸው ይሆን የፈለጉት? ወይንም ሽፍታው ወያኔ የሞት ቅጣት ወይንም ዕድሜ ልክ እስራት ፈርዶባቸው በዛ ተደናግጠው ምን እንዲሆኑ ይሆን ምኞተዎትና ዓላማዎት? ወይንም አንዱ እንዲህ እራሱ የሾለከበት የዘር በሽተኛ ባገኘው አጋጣሚ አነጣጥሮ እንዲገድላቸው ይሆን? ለምንስ መሳሪያውን ገዝተው አይሰጡትም ለአንዱ የዘር ብኩን?! ….. ገድለዋቸዋል እኮ እርስዎ። ሞት እኮ ነው የፈረዱባቸው።
እኔ እኮ እበቃዎት ነበር – ጌታው። የጻፍኩት እኔ። ስለምንድነው ሳቢያ ዬሚፈልጉት። „አንዳርጋቸው ስለምን ጀግና ተባለ?“ ነው አይደል። ጸሐፊዋ እኮ እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ነኝ። ፎቶዬ ከናፈቀዎት ከፈለጉት ላይ ይለብዱት። በፈሉጉት ዘይቤ ይሰልቁኝ። እንዳሻዎ ይቀጥቅጡኝ። እኔ እመመኘው ነፃነት የማይመቸኘን ሃሳብ ለማስመቸት ነው። ሃሳብን በሃሳብና በፋክት አፋጭቶ በነጠረው ሃሳብ በብዙሃን ድምጽ የሚመራ ነፃነት ነው ናፍቆቴ። ስለሆነም በፈለጉት ዓይነት አቀራረብ ዱላዎት ይደላው ነበር። እችለዋለሁ። ምንም እንኳን ጹሑፎ ብናኝ ጭብጥ ባይኖረውም – እንኩቶ ቢሆንም።
ከእነዚህ ወጣቶች እራስ ግን መውረድ አለበዎት። ፎቷቸውንም ማንሳት። ትእዛዝ አይደለም – አስተያዬት እንጂ። እኔና እርስዎ አንደራረስም እርስዎ ከፍ ያሉ እኔ ደግሞ ትቢያ። በሁሉም ነገር እንደሚበልጡኝ አሳምሬ አውቃለሁ። ለዚህም ነበር በጭምትነት ዝም ብዬ የሰነበትኩት። እርስዎ ግን የከተቡት ሁሉ የተሰባባረ – አቅጣጫው የጠፋበት – የወለላለቀ – ወለምታው የሰቀዘው የቃላት ድርደር ሁሉ ቁጭተዎትን፤ ለወያኔ ያለዎትን መጠነ ሰፊ ተቆርቋሪነተዎትን ሁሉ ሊመክትለውት አልቻለም። መደረት – መደረት በላይ በላይ – ከሽበተዎት ጋር ይምከሩ።
እኔ ልንገርዎት ዓላማው የሥነ – ልቦና ጦርነት በውጪ የነፃነት ታጋይ ቤተሰብ ለመሰንዘር ነው። ችግሩ አንተዋወቅም። ከብረት ቁርጥራጭ ዬተሰራው መንፈሳችን ግን ከቶውንም ለአፍታ አያንቀላፋም። ጠላታችን ወያኔ ፋሽስታዊ ማኒፌስቶው እስኪነቀል ድረስ የነፃነት ትግሉ በበቃን መሪነት ይቀጥላል። ለሰማዕትነት የቆረጠ ጀግና በጠላት እጅ ነው። ውስጡን ጎርጉራችሁ ምን እንዳደረጋችሁት አይተናል። ይህ ደግሞ ሃይልና አቅም እንደ አዲስ እዬፋፋ እንዲሄድ ያደርገዋል። አንፈራም! አንገታታችንም አንደፋም – በፍጹም።
በስሜት ጋልበንም ከህዝብ ፍቅር ማሳ አንወጣም። ይህ ይመረወታል – ይወረወታልም። ይህ ተቆስቁሶ „ትግራይን“ እንደናብጠለጥል ነበር የፈለጉት። ጓደኛ ፍለጋም እዬባዘኑ ነው። በዓይናችን በተከበሩ አቶ ገ/ድህን አርያማ አይምጡ። አዩ ቅናት! እኔ ስነግረዎት – የተጠለሉበት ጥግ ቀን ዋቢ የለውም። ቀን ወዳጅ የለውም – አውላላ ሜዳ ላይ ጥሎዎት እንዲህ እብስ -
የፈሩት – እንዲህ ያባከነዎት የተከበሩ የአቶ አንዳርጋቸው ዝክረ ጀግንነት በቋሚነት ጽላታችን ይሆናል – ለአብዛኞቻችን። ተከፍሎን ወይንም ባውንድ ተሸልመን አይደለም። እንዲያውም እንዲህ አቅም ሆነን ማገር እንዳንሆን የራሳችን ቅንቅኖችን እዬተጋፋን – እዬገፈተርን ነው ዕውነትና ሃቅን ለማድመጥ የፈቀድነው። በገንዘብ ተገዝቶ ዕንባና ጥቁር ልብስ ሄሮድስ መለስን ቀበረ። እኛ ግን ለአርበኞቻችን – ለሰማዕቶቻችን ፈቅደንና ወደን ደስ ብሎን የምናደርገው ድርጊት ነው …. ለህሊና መኖር ማለት ተፈጥሮን የመተርጎም አቅምና ብቃት ማለት ነው።
መላሾ አሞሌ እኔ ሳውቀው ለከብት እንጂ ለሰው ልጅ አይታሰብም። የወያኔ ሥር ለማረግረግ ጥሎሹ ወይንም እጅ መንሻው እንደልቡሻ ማይጨውና መተማን እንዲሁም ሌሎች ሀገር ወዳድ ወገኖቼን ታሪካቸውን አቃጥለው፤ ሞት ፈርደው ሲባትሉ ሰነበቱ። መጥኔ ለእርስዎና ለአውቆ አበድ ብዕርዎ። እኔ ልንገረዎ እንደ እግር እሳት ያንገበገበዎት ለወያኔ ሽፋን ለመስጠት በሰላማዊ ትግሉ ስም ጠንከር ብለው የሚወጡትን የነፃነት ድርጅቶችን በውስጥ ለውስጥ መንገድ ስትንዱ፤ ስታናክሱ፤ አንጃ ስታስፈጥሩ በዚህ ለሰው በማይታይ ደባ እሳካሁን አረሙ ወያኔ ትንፋሹን እዬሰበሰባ የተፈጠረበትን የጥፋትና የባንዳነት ተልዕኮውን ሲከውን ኖረ።
ከዛም በፊት አልተሳካም እንጂ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን በሚያመክኑ ሥውር ሴራ ረቂቅ በሆነ – ሰልጠን ባለ መንገድ ፍርሻ -ህውክት – ሲፈጠር ማገዶዎች ሌሎች ነበሩ። አሁን ጥግ ጠፋ …. በጠራራ ጸሐይ መሸፈኛ አልባ ገመና መውጣቱ ግድ ሆነ። የወገን የበዛ ሰቃይ የምትፈሩትን አቅም በመንፈስ ጽዑም ለዛ አጋባና ፋሽስቱን ወያኔ ፊት ለፊት ወጥቶ አወገዘ። ይህ ሲቀጠል ደግሞ ተከታዩ ምን ሊሆን እንደሚችል ታውቁታላችሁ …. አጃቢ ጠፋ … አቆላማጭ ጠፋ …. ሸፋኝ ጠፋ …. ቅኖች ዛሬን አነበቡ ….. ሚስጥር ተግልጦ እንዲህ በጉባኤ ሥጋና ደምን አዋህደ፤ የሀገራችን ውርዴት ውርዴታችን ነው አሉ ዬእትብት የቁርጥ ቀን አላማና ራዕይ ያላቸው ልጆቿ እንሆ ፊት ላይ ተገኙ። የወገናችን ስቃዩ ስቃያችን ነው አሉ የትውፊት አንበሶች። የወገናችን መከራው መከራችን ብለው ሆ! ብለው እንደ ትሩፋታቸው ተነሱ። ሌሎችም በዚህ በመከራ ቀን መታቀብ አለብን ብለው ሰብሰብ ብለው ተቀመጡ። ወቀሳ የለ ነቀሳ የለ። መነገድ በቃ ….. እዬተጣቡ መጣባት ማብቃት አለበት አሉ። ወሰኑ - ቆረጡ – ተንቀሳቀሱ። ይህ ደግሞ መሽጎ ብቅ እያለ ቤንዚን ለሚያርከፈክፈው አልማጭ አልተመቸም።
ጭድ ከማቀበሉ በፊት ሃሳቡና እልሙ ጭድ ሆኖ አረፈ። ራሱን ገልብጦ አቃጠለው። እኔ እንደማስበው ወቅቱን በአግባቡ አድምጦ ማስተዳደር ከተቻለ አሁን የነፃነት ትግሉ ከጠራ መስመር ላይ ይገኛል። በእጣት የምትቆጠሩ ወገኖች በሰላማዊ ትግል ሥም፤ ወይንም በሉዕላዊነት ተቆርቋሪነት ሥም፤ ወይንም ሊዋህዱ ባልቻሉ የአንድነቱ ቤተሰቦች ሥም ወይንም በሃይማኖት ሥም፤ ወይንም በብሄርና ብሄረሰቦች ሥም ስሱን ቦታ እያዩ ካቫውን ደረብ አድርጎ ጠቅ እያደረጉ አጋግሞ ዞር፤ ወይንም እኔም አለሁ እያሉ እዬገቡ ማመስና ማተራመስ አይቻልም። ቀኑ እንደ ክብረዎት ሾለከ …. አዬ ቀን! …. እርግጥ ሲያስቡት ጎሽ መሸቢያ የሚባሉ መስሎዎት ነበር። በጣም ብዙ ሰው ነው ያዘነቦዎት።
እጅግ የምትናፍቁኝ የሀገሬ ልጆች በዚህ ዓመት ብቻ ሁለት ነገር ተከሰተ። ጀግና ካፒቴን አበራ ሃይለመድህን በሚመለከት በተፈጠሩ ክስተቶች በዬቦታው እጅግ በጣም ብዙ ነገር ነው የተዝረከረከው፤ የነፃነት ትግሉ አካል ተብለው ባለወርቅ ተክሊል ባለቤት የነበሩትን ሁሉ ነው የዛ ጀግና ድል ያንዘረዘረው – ካልጎሽ አይጣራ፤
ከዚህ ቀጥሎ ጀግናዬ አንዳርጋቸው ጽጌን በማፍያ ትብብር ከወያኔ እጅ መግባት በሚመለከት ደማችን የተቆጣ ሃይሎች የሀገራችን ክብር መደፈር ያነገበገበን ወገኖች፤ በገፍ ሰላማዊ ቀንበጥ አርበኞቻችን ወደ እስር እዬተጣሉ በሚወሰድባቸው ፋሽስታዊ ህገ ወጥ እርምጃ ይግርመዎታል ብዕረኛው አቶ ጌታቸው እረዳ ጉዳያችን ነው ብለን አካላችን እንዳይመስለዎት መንፈሳችን በፈቃድ አጋባን። በቃ! ተሰደንም ሰላም እንዴት እናጣለን ብለን ለይ አልን። ….. ለስላሳዊ ተፈጥሯዊ ባህሪያችን ጎርበጥባጣ ሆነ … ልንመች አልቻልነም። እኔ እንዲያውም ቆርጫለሁ የፈለገ ህዝባዊ ስበሰባ ይሁን አቋሙ ባለዬ፤ በተወዛወዘ ቦታ አልገኝም። ብዕሬም ብራናዬም መደከም የለባትም። በሃይማኖት፤ በማህበራዊ ግንኙነት ሁሉ ጥርት ባለ መስመር መድከም – ለትርፍ፤ በስተቀር ለኪሳራ ቆራጣ ነገር አይባክንም ከእንግዲህ።
ኢትዮጵያዊነት ሃይማኖታችን፤ ኢትዮጵያዊነት ቀለበታችን፤ ኢትዮጵያዊነት ድምጻችን፤ ኢትዮጵያዊነት ቀለማችን፤ ኢትዮጵያዊነት ህገ – መንግሥታችን፤ ኢትዮጵያዊነት ቅኔያችን፤ ኢትዮጵያዊነት ውስጣችን ብለን እነሆ ተነሳን። የሃይላችን ምንጩ – የሃይላችን ጭንቅላቱ – የሃይላችን ጉልበቱ – ብንዘገይም እግዚአብሄር ምክንያት ሰጥቶ ከቀስት እናመልጥበት ዘንድ አጥቢያ ኮከብ አበራልን።
ይህ ነው ፋታ ነስቶ – እረፍት ነስቶ አምክንዮው የፈለሰበት፤ ጠረኑ የተበተነ፤ መግቢያና መውጫው የተተበተበ፤ ፍላጎቱ እንጡሩብ የሚዘል፣ አንድም መረጃ ሊቀርብበት ያልቻለ ብትክ – ብትክትክ ያለ የቃላት ድርድር ያሰነበቡን። …. ድጋሚ እንኳን ደስ አለዎት እራስዎትን ስላገኙ። ከመሼ ቢሆንም። ከቻሉ በመጪው ምርጫ ለጠ/ሚር ውድር ወይንም ለከዘራ ደጋፊነት ይወዳደሩ …. ምን ሻታ ያዞረዎታል? … ከዘራ ስል እርጅና ማለቴ አይደለም። አልወጣኝም እንዲያውም ብዕረዎት በሬ ወለደ ናት እንኳንስ እኔ ብዬ። ለማለት የፈለግኩት ስንት ናቸው የሽፍታው ዬወያኔ ም/ጠ ሚር …. ለነገሩ በመጪው ምርጫ ያው ዘሬን ዘሬን እያለ የሚዳጭረው አቶ ወንበር ከቦታው ወርቃማውን ካገኘ ከዘራ ላያስፈልገው ይችል ይሆናል …. ከዛ በፊት ግን ነፍሳችን በመቋጠሪያ አልያዝናትም ሁላችንም …. ማን ያውቃል የሁለት ቢላዋ ባላቤቶች …. ሽኝት ቢጤ ይኖር ይሆን? ወፏን ጥያቄ መሄድ ….. አሰኘኝ …. እንደ ማለት —-
ሌላው እንዲያውቁት ዬምፈልገው ነገር ኢትዮጵዊ ተቋማቱ የመወያያ መድረኮች ስለምን እንዲህ „የናዚ ኔት ወርክ“ እስከማለት አደረስዎት ቢባል። ለዘር – ለመንደር በሽተኞች „ኢትዮጵያ“ የምትል ሥም ሁሉ ዛር ታስወርዳላች …. የወያኔ ተልዕኮ ይህቺን ምድር በተፈለገው መልክ ማጥፋት ነው። ይመኟት የነበሩት ባእድ ሀገሮችም እነሱ ስላልቻሉ ከማህጸኗ በፈሉ ተውሳኮች ፍላጎታቸውን በማስፈጸም ላይ ይገኛሉ።….ሽፍታው ወ ያኔ መሰረተ ጥንስሱ በአንድ ዘር የበላይነት ኢትዮጵያዊነትን ለማጠፋት፤ ለመደምሰስ በተከታታይነተትና በትጋት መሥራቱ ፍጥረተ ነገሩ ነው። ሲከስም ግን ከሥሩ ዘር አልባ ሆኖ ይሆናል። እኔ እምሻው እንደዚህ ነው … መርዝ መነቀል አለበት።!
ሌላው ቀርቶ ወያኔን የተገባውን ያህል „ለትግራይ“ አላደረገም ወይንም በደሉ መረን ለቀቀ እቃወመዋለሁ ብሎ የሚነሳ አንድም ድርጅት ወይንም አንድም የመወያያ ክፍል „ኢትዮጵያ“ የምትለውን አስቀድሞ አያውቅም። አይደፍሯትም። ቀዳሚው …. ለምን ይህ አልጎረበጠወትም? ይመቸወት ይሆን - የሸረፋ ሸጎሬ?
አቶ ጌታቸው ረዳ ጹሑፎዎት በጣም ቁንጥንጥ ያበዛ ቁንጣን ያያዘው ነበር። እጅግ አብዝቶ የዕድሜዎትን ተፈጥሯዊ ጸጋ ሁሉ ድጦታል ልበልን? ጥንቃቄ ፈጽሞ አልጎበኘውም። ማገናዘቢያው ሆነ ማመሳካሪያው የእንቧይ ካብ ነበር። እንዲህ የሚጋልብ ስሜታዊነት ኢትዮጵያንም ሆነ ኢትዮጵያዊነትን አያድንም። የሳሙና አረፋ ያውቃሉ? ወይንም ፈረሰኛ ውሃ ሙላት የሚባል እንደዛ ነው ልበልን? ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን የሚያድነው ከበቀል የጸዳ ከቂም የነፃ እራስን በፍጹም ሁኔታ ያሸነፈ፤ ውስጥን በሚገባ መቆጣጠር የቻለ፤ ዬባህላዊ ትውፊታችን ህግጋት በስክነት ያወያዬ መንገድ ብቻ ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ኢትዮጵያዊነት እንደማንነት መግለጫ ያድነዋል። በዚህ ሃዲድ ብቻ ትውልዱ ከአፍር ለማኝነት ይድናል። በስተቀር ግን ዛሬ ስንዴ ነገ ደግሞ ከበለጸጉ ሀገሮች አፈር ለማኝ መሆናችን አይቀሬ ነው። የአንድነቱ ዋቢ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ አቅም ብቻ አይደለም ለዚህ የበቁት። ዬኢትዮጵያ ዬአፍሪካ ቀንድነት፤ የመካከለኛው አፍሪካ እራስነት መናድ በጥረታቸው የማይቻል መሆኑን ሲያውቁ ከውስጧ ባንዳ አመረቱላት። ይህ ዕውን እንዳይሆን ነው የሴራው ድርና ማግ። ለማንኛውም በዚህ ሳይሞቅ እንደ ጉድ በሚፈላ ኮበሌ ብዕርና ብራና የተበዳይን – የመከራን – የግፉዕንን ሰዉ ትእግስቱን ያሸፍታል። አይገባም። እልህና ቁጭት ሌላም እሳት ያቀጣላል። የከረፋ በደል አለ። የሚያንገሸግሽ አድሎ አለ። የሚያንገፈግፍ መገፋት አለ።
በከረፋው በደል ውስጥ ወያኔ እንዲሸፈን ሽፋን ፈልጎ የትግራይን ህዝብ ምሽጉ አድርጓል። ይህን ሚስጥር ተፈልፍሎ እንዲገኝ ማስተዋል ተንበርክኮ ይጠይቃል። ማስተዋል ሱባኤ ላይ ነው። ዕንባም ህማማት ላይ። ስለሆነም መርዛማ እጩን ለይቶ ነቅሎ ዬማውጣት ሥራ ነው መሠራት ያለበት። እርስዎ እያሉን ያሉት ደግሞ ሌላ በበቀል የጨቀዬ – ጨቀጨቅ ከሃሞት ጋር አንድንጎርስ ነው። ቢያዳምጡኝ ምልዕትን አግልሎ ኢትዮጵያን ማዳን ከቶ አይቻልም። ስለዚህ ወቅቱ አብዝቶ ከእያንዳንዳችን እላፊ አለመሄድን ይጠይቃል። በተጨማሪም እራስን አሸንፎ ሆኖ መገኘት ያስፈልጋል። እርስው እኮ እራስዎት አመለጠወት። ሰው መሆን በቂ ነው – ለዛሬም – ለነገም – ለነገ ተወዲያም። በበቀል ብቅል እዬታረሰ ያለውን የምልዕት መንፈስ መፈወስ የሚቻለው እርስው በመረጡት መንገድ አይደደለም። የድህንቱ መንፈስ እንዲህ ሲል ይቃኙታል http://www.zehabesha.com/amharic/archives/33615
ህዝባችን ጎጥ አስተዳደር እጅ እጅ ብሎታል። እጅ እጅ ያለውን አስተዳደር የበቀል ብቅል ሚዛን ላይ አስቀምጦ ፍትሃትንት ማወጅ …. ቢደለዝ – ቢቀባባ – ቢሸፋፈን አይሆንም። ኢትዮጵያ ከትግራይ በወጡ ፈለፈሎች እዬተደበደበች ነው ያለችው። ልጆቿ መጠጊያ አልባ በቀን ብርሃን ጨለማ ተውጠው ነው ያሉት። በዜግነታቸው ለመኖር አልተፈቀደላቸውም። አልሰሙም ማለት ነው። የተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ታላቅ እህት እኮ በ24 ሰዓት ሀገር ለቀው እንዲወጡ ነው የተበዬነባቸው … ምን ማለት ነው ይሄ …. የቀለም ጥልቅ ዕውቀተዎት ይህንን አምክንዮ እንዴት ይተረጉመዋል? እውነትና ሃቅን አይሸሹት! … ይድፈሩት! ….. ማነው የዜግነት ፈቃድ ሰጪው?! …. ሀገሬ ሰንድቅዓለማዬ ብሎ የማያውቅ የጎጥ አስተዳደር ….? ብዕረዎት ማጅራቷ ላይ ይሆን ዓይኗ ያለው? የጥበብ ሰው እኮ መከራን አብዝቶ መጋራት አለበት። መረመጥ አለበት። አልቻለችም ብዕረዎት …. ወንዝ መሻገር አቃታት …. ቃተተችም። የጥበብ ቋንቋ እኮ ሰውነት ብቻ ነው። የፍቅር መግለጫው ደግሞ ህግን አለመዳፍር ነበረ። ወደቀች አንዘላልጦትም። ወያኔ ማለት በግልጽ ቋንቋ ከባህር የወጣ አሳ ማለት ነው።
የኔዎቹ ወገኖቼ። እንደዚህ ዓይነት ክብሪት ብዕሮችና አንደበቶች አብረው የኖሩ ናቸው። በሰላሙ ጊዜ የተረጋጋ ተግባር ሲከውን ከቀፏቸው ውስጥ ተሰብስበው አድብተው ይቆያሉ። ወያኔ በወሰደው ጨካኝ እርምጃ ቁጣ ሲነሳ ግን አዲስ ተለጣፊ ነገር ፈብርከው ብቅ ይላሉ። መጠለያ አላቸው ድርጅት። ይህንንም መፈተሽ ያስፈልጋል። ማንዘርዘሪያ ማዘጋጀት በእጅጉ ያስፈልጋል።
እርግጥ ነው አንድ የፖለቲካ ድርጅት አባላቱ የሚተዳደሩበት ደንብ ለአባላቱ የህይወታቸው መተዳደሪያቸው ነው። ከዚህ ማዕቀፍ ከወጡ በድርጅቱ ሥርዓት ቅጣት ይፈጸምባቸዋል። እንደዚህ ዓይነት ሀገር የሚንድ ውጪ ያለነውን ሳይቀር ህግን ጥሶ ነፃነት የሚቀማ፤ ክብርን የሚዳፍር ተግባር አባላት ሲፈጽሙ ድርጅቶች ሃግ ማለት አለባቸው። በስተቀር ግን ተስማምተውበታል ማለት ነው።
በሌላ በኩል ድርጅቱን አትንኩ፤ የግል አስተያዬት ነው ለማለት የሚቻል አይመስለኝም። የፓርቲ አባል ትንፋሹ ከፓርቲው ማልያ ጋር የተሳሰረ ነው። በፓርቲ ህይወት ውስጥ ዬግል ዕይታ የሚባል ነገር የለም። በቀኝም – በግራም – በፊትም ሆነ በኋላም ቢመዘን – ቢፈተሽ በስተጀርባ ካላው የፓርቲውን አቋም ጋር እንደዚህ መሰል የአባላት ግድፈቶች ነፃ ሊሆኑ ከቶውንም አይችሉም። ነፃ ሊሆን የሚችሉት ፓርቲው በአባሉ ላይ ፈጣን እርምጃ ሲወስድ ወይንም ግልጽ የሆነ አቋሙን በአደባባይ ሲገልጽ ብቻ ነው። በስተቀር ድርጅቱ አብሮ መድቀቁ የግድ ነው። አኔ ከፓርቲዬ – ፓርቲም ከእኔ ፈጽሞ መለዬት አይችልም። ምክንያቱም አንድ የፓርቲ አባልን ከፓርቲው ነጥሎ ለማዬት ፈጽሞ አይቻልም። ሰርገኛ ጤፍ ላይ ነጭ ጤፍን ለቅሞ የማውጣት ያህል ከባድ ነው። ስለዚህ የእስካሁኑ ጉዞ በዚህ በተደባለቀ ዝንቅ ጉዙ ጊዜው መቃጠሉ አይደለም በጣም ብዙ ሀገራዊ ጉዳዮች ተጎድተዋል። ተመስገን! ሱማሌን መመከት በይቻል ዛሬ እንደ ህዝብና እንደ ሀገር ለመጠራት ባልቻልንም ርፍራፊ ነገር አለችን።
ከዚህ ባለፈ በዚህ መሰል የሀገር ጠላትንት ነቀዝነት ማጋዶዎቹ – ቅኖች – ደጎች – የእውነት አርበኞች – የግንባር ሥጋዎቹ አለፉ፤ ቤት ንብረት ፈረሰ፤ ልጆች ወላጅ አልባ ሆኑ፤ የሰው ልጅ እንደ እንሰሳ በመርዝ መሞከሪያ ሆነ …. በቤንዝንም ተቃጠለ … በጠራራ ጸሀይም በመዲናዋ የባሩድ እራት ሆኑ … በርካቶች ታፈኑ …. ከእንግዲህ ግን ዬሚከፈለው መስዋዕትና የትግሉ የጥራት ጉዙ መመጣጠን አለበት። ይህ የማግለል ዘመቻና ፖሊሲ የወያኔ ብቻ አይደለም አዲስ ነገር በቅሎ ለማዬት አይናቸው የማይችሉትም አቅም ቢሶች መገለጫ ነው። የሆነ ሆኖ የሾለከው ነጥሎ ሌላው ሾላኪውን እዬቀደሙ በጥንቃቄና በማስተዋል መጓዝን ይጠይቃል። ወቅቱ የመቆላማጫ የመላላሻ የጥሎሽ ጊዜ አይደለም።
…. ግን እንዲያው ለነገሩ ለእርሰዎ የተከበሩ ዬአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በመያዛቸው እንደዛ ሆነው በጎጥ አራዊቶች ማዬታችን፤ ወጣት ጀግኖቻችን የሃብታሙን፣ የዳንኤልን፤ የሽዋስን፤ የአብርሽን የጣር ድምጽ መሰማት እንዲህ ያስጨፍራል? ለእኔ አቶ አንዳርጋቸውን ጀግናዬም ሽልማቴም ብዬ መጻፌ ይህን ያህል ዛር ያስነሳል? ጎሽ ወያኔ ደግ አደረክ መልካም ሰራህ – የምትፈራውን ሰማዕት በእጅህ ስለገባልህ ሻማ ይብራልህ ልንል ነበር የተፈለገው …. ደግሞስ እኔ እኮ ነፃ ሴት ነኝ። የፈለግኩትን ድርጅት የመቀላቀል፤ የፈለኩትን ድርጅት ዬማድነቅና ዬማክበር፤ ውስጤ የሚያምንበትን አውጥቼ መጻፍ እንድችል እኮ ነው የተሰደድኩት። የእሶዎ አጋዚ ብዕር ተፈርቶ ጭጭ ረጭ እንዲባል ነበር የሚፈልጉት። እንዴት ተቀለደ?!
…. እጅግ የማከብራቸው ሙሴን ነው ወያኔ ያፈነው – የማድመጥ ሊቅም ነበሩ። ይውጣለዎት። ወያኔ ባንዳው ጠላቴ ነው። አሁንም ይደገም እስከ ማንፌስቶው መነቀል አለበት። www.tsegaye.ethio.info በዚህ ገባ ብለው „ተስፋ“ ላይ የድህረ ገጹን ዓላማ ያንብቡት ካስፈለገዎም በድምጽም ያገኙታል። በተጨማሪም እኔ ስላለኝ አቋም በዬ15 ቀኑ በዚህ በድምጽ ያገኙኛል እርግጥ አሁን የበጋ እረፍት ላይ ነን ግን አርኬቡ ላይ ያለውንም Radio Tsegaye Aktuell Sendung ገባ እያሉ ይኮምኩሙ።
ትናንት የተፈጠረች አይደለችም ሥርጉተ። እንዲህ ገባ ተብሎ የሚዘለልባትም አይደለችም። ነዳያንን ስንት ፍሪዳ አርደው ድንኳን ጥለው የልደት ፆምን አደግድግዎ ጉንብስ ቀና ብለው ከሚያስተናግዱ ሊቀ ሊቃውንታት የተፈጠረች ናት። መንገድና መርህ ራይና ተስፋዋ ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው። በምንም ንቅዘትና ጸያፍ ተግባራትም ፈጽሞ የማትታሰብ ክውን ናት። እንዴት የምትደነግጣውን ሴት አግኝተዋል? እሷን አፍ ለማዘጋት – አይችሉም! – ህልም ነው! — ለመሆኑ ይህ ግራ በሚባለወስ ታላቁ መርህ „የሴቶች የእኩልነት የአርነት ትግል አልነበረንም? ምነው ግፊያ አሰኘዎት? አንዲት ሴት እንኳን ለማስተናገድ ታዬ አቅመዎት …. ትንሽ እራፊ ቦታ የለዎትም ለሴቶች ተሳትፎ …. እግዚኦ! አዬ አቅል – አዬ አቅል — አይገዛ ነገር ———–
በተረፈ የሀገሬ ጫካ ሆነ እስር ቤቱንም የማውቀው ነው። ለእኔ አዲስ ዬሆነ ነገር የለም። ምነው ወጣት በሆንኩ በነበረ እንዲህ የዘር ዛርን በብዕር ሳይሆን በባሩድ ነበር የማሰተነፍሰው በለመድኩት ጫካ።
የኢትዮጵያ ወቅታዊ የመወያያ ክፍል መድረክን በሚመለከት በእኔ ሥም አይወርፉት። እኔ አድሚንም ቦርድም አባል አይደለሁም። በህግ ዕውቅና ያለው የተደራጀ ስለሆነ ዕውቅና የሰጠው አካል ቢጠይቀዎት መልስዎት ምን ይሆን? በቃ ቱግ – ቱጉ ብቻ … ማህከነ!
ከረንትን ያህል ኢትዮጵያዊ ተቋም በቦርድ አባልነት ለመምራት አቅሙ የለኝም። ቢሆን ግን ደስታውን አልችለውም። እርግጥ ነው ከዬካቲት 2009 አስከ የከቲት 8 . 2010 ቋሚ አባል ነበርኩኝ። አሁን አባል ባልሆንም እናት ቤቴነቱ ግን እንደተጠበቀ ሆኖ የድህረ ገጹ ደግሞ ዘበኛው ነኝ። የማይመቸኝ ላይ ሚዛን ለመጠበቅ ብዙ ጊዜ ከሥር እጽፋለሁ። አላምነውም በቀን እስከ ስድስት ጊዜ አዬዋለሁ። ይገርመወታል ሌሊት ሁሉ ክፈት አድርጌ አዬዋለሁ። እንደ ጦር የምትፈሩት የተግባር ቤት ስለሆነ ነው። ከረንት አቅሙን የሚገልጸው በሥራ ነው። አቋሙ ደግሞ ከጊዜ ጋር እንደ ወጀብ እንደነካው ዛፍ አይዘፍንም። ቀጥ ያለ የአደራ ማውጫ ቤት ነው። ኢትዮጵያዊነትን ሰንደቁ ስላደረገ ትቢያ ለበሳችሁ አፈር ቆረጠማችሁ ብትረግሙትም ከተግባሩ አንድ ጋት ፈቅ እንደማይል አስባለሁ። ግልጽና ጽኑ አቋም ነው ያለው። አቋሙ ወያኔ ከነጉቱ ከነ ዘረኛ ማኒፌስቶው መነቀል አለበት ባይ ነው። ይህ ደግሞ የእኔም የህይወቴ መርህ ነው ተግባባን ጌታው?!።
ማይጨውን ሳዬው ደግሞ … ዬሽበት ትርጉሙ ሽሽጉኝ ብሎ ጆንያ ውስጥ ሲቀረቀር አዬሁት። ታዬኝ እኮ ማይጮ የግንቦት 7 አባል ሲሆን? በመንፈሱ የጉልማ መሬት ታህል ለትጥቅ ትግል ቦታ እንዳልነበረው ነበር እኔ ሳውቀው። ሰላማዊ ትግል ደጋፊ ሆኖ ነው እኔ የማውቀው። ኢሳትን ሊደግፍ ይችላል – የነፃነት ትግሉ መተንፈሻ ንጹህ ቧንቧ ስለሆነ። ይህ ደግሞ ለወያኔ ስርዎ ስውርም ደጋፊዎች ረመጥ ነው። ቅጥል – ድብን - ፍርክርክ አድርጎ ብርክ ያስይዛችኋል። እኔ እንደማስበው ያው እርስዎም ተደብቀው ያጣጥሙታል ብዬ አስባለሁ። ያው ቅናት ናት እንዲህ ፈርፈር የምታደረግዎ እንጂ። በልበዎ ያደንቁታል አይደል ኢሳትን? ማንም የአፍሪካ ሀገር ያልደረሰበት የእድገት ደረጃ ላይ ስደት ላይ ሆኖ ተግባሩ አንቱ ነው።
ሳረሳው ደግሞ አንድ ነገር – አልኮዎት ጌታው አሁን እኔ ሌላ የወመኔውን ድራማ እዬጠበኩ ነው። … ኢሳትን የሚረዱት ጥንታዊ ጠላቶችችን ናቸው የሚል …. ይህ አይቀሬ ነው። ለነገሩ እርሰዎም እኔም ተሰደን የምንኖርባቸው ሐገሮች አንድም ቀን ለአፍሪካ የነፃነት ትግል ቀን ያወጣቸው ዬሀገረ – ኢትዮጵያ ወዳጆች አይደሉም። ማንስ ወዳጅ ኖሯት ሲያውቅ ነውና? ስለዚህ እርስዎም እኔም ጓዛችን ጠቅለላ ነዋ ከእነሱ ዘንድ አይደለን ያለነው? በፈለገው ቅርጽና ይዘት ብቅ ይበል ዬእንኮሸሽሊቱን* የበቀል ብቅሉ ድራማ እንኩቶ እናዳርገዋለን። አይገርመንም – አይደንቀንም። አሁንስ ተግባባን?! … ያው ያችን አንጠልጥሎ ማቀጣጠያ የባህር ዛፍ ቅጠል ለቀማ ቢወጣ ባዶ እጁን ተመላሽ ይሆናል – ግፋፎው – ወያኔ። ሌላው እርስዎም አንደሚያውቁት ዘረኛው ወያኔ የሚተነፍስው በልምና ስንዴ ነው እንኳንስ የስደቱ ሚዲያ …. ስለዚህ ገና ወያኔ አፉን ሲከፍት ቆረቆንዳ በልኩ ተሰርቶለት ይደፈናል – እሺ!
ሲገርሙ! ምነው ይህቺ ሚዛኗ ላይ አስኳላዋን ገፋ አላደረጉ ይሆን? ሰው በነፃነት በሚኖርበት ሀገር ካላፈቃድ ፎቶ በወንጀለኛ ሥንኝ … መለጠፍ፤ እንደ ተቋም ሶስቱም ሩሞች ህግ በመተላለፍ ክስ ቢመሰርቱ ዋጋወን ያገኙ ነበር። ታዳሚውን ሁሉ እኮ ነው አብረው ያረሱት። ኦኦ! በግለሰብ ደረጃም ቢሆን ፎቶና ከሥሩ የጨነቆሩት ሐረግ በራሱ ገመድ ነበር አዙሮ የሚያንቅዎት። በጣም ተዳፈሩ፤ በጣም እራስዎትን ውድና ዬትግራይ ህዝብ ተቆርቋሪ አደረጉ፤ ቆርጠውና ቀደው የሚያሳድሩን ያህል ነው የተጋፉት፤ ግን ህግ እዬተላለፉ – እዬዘለፉ – እያዋራዱ …. እንዴት እንቅልፍ ወሰዶዎት?
ለመሆኑ „ናዚ“ ማለት ምን ማለት ነው? እንዴትስ በምንስ ሁኔታ ሊከሰት ይችላል? አስፈጻሚ ተቋማቱ ምንድን ናቸው? ዬዶክተሪኑ ሥነ ህይወት ገጽታ ሆነ ፍለስፍናው በምን ይገለጻል? በዚህ እድሜ - በዚህ የዘመናት ተመክሮ በስሜት የተከዘነ ጆንያ ሙሉ የጭድ ትንፋሽ የኢትዮጵያን የነፃነት ራህብ አይታደግም። ዙሪያ ገባው ነዳላ – መወተፊያ ወይንም መጥቀሚያ መርፌ ወይንም ለማያያዝ ሙጫ ነገር የማይደፈረው የተቆራረጠ ሙጣጭ – ግብና መቋጠሪያ አልቦሽ ኩረት ነው ሲደረደሩ እንቅልፍ አልባ ሆነው የሰነበቱት ….
ጌታው አንሰነባበት – ስንብቱ ለዳርቻ ነው። ከዚህ በኋላ የገደሉትን ገድለው – የወቁትን ወቅተው – ቀረኝ የሚሉት ማሳ ካለዎት ያስኬዱት። የፈራን እንዳይመስለዎት። ከትጋታችን አንዲት ጋት ፈቅ የማንል እንደሆነ እንዲያውቁት ነው የተጣፈለዎት። ቀጣዩ ህይወትዎትን – ዘርዎትን ፍለጋ መማሰን ሽበትዎትን – ዝልቅ ተመክሮዎት አንገቱን ደፍቶ እዬጠበቀዎት ነውና ይታረቁት። የሽንፍላ ጹሑፎወትን የመረጃ ማያያዣ ሊንከዎትን አለጠፍኩትም ተጸዬፍኩት – ገዳይ ገዳይ ወይንም አስገዳይ አስገዳይ ይሸታል – ይከረፋል። እኔ አብቅቻለሁ። መልካም የምንም ጊዜ …..
ውዶቼ የእኔዎቹ አሻቅቦ በሁሉ ነገር የሚበልጥን ወገን መናገር እንዴት ይከብድ ይመስላችኋል። ያልኖርኩበትና ያላደኩበት ሆኖ ውስጤን አብዝቶ አስጨነኩት። ግን መሆን ነበረበት። የኔዎቹ ደህና ሰንብቱልኝ። መሸቢያ ጊዜ! ውድድድ.
- ጉርና – የቅል ዕድገት ማብቂያ – ቅርጽ የለሽ ዕድገቱ አንገቱን ውጦ ሽንጡን ያሰፋዋል። በባለሙያ ውስጡ በሚገባ ይዘጋጅና ማንገቻ ይሠራለታል። ከባላ መንታ እንጨት ላይ ሆኖ እርጎ ይገፋበታል ወይንም እርጎው ተንጦ ቅቤ እንዲወጣ የሚረዳ ባህላዊ ዕቃ ነው። ትንሽ የምትሉት ብዙ ስለሚይዝ ጉርና ይመስል ሆድ አታብዛ ይባላል። ከተሰጠው ጸጋ ወጥቶ እሳት ላይ ቢጣድ ግን ከማረርም አልፎ ከእርጎ ጋር ጎርንቶ ተነዳድሎ እራሱ ህልፈቱን ያውጃል።
- ኩታራ - የልጅነት ጊዜ። ምራቁን ለዋጠ የእድገት ደረጃ ገና ጮርቃ የሆነ እንደ ማለት።
- እንኮሸሸሊት - ቅጠሉም ግንዱም ፍሬውም እሾህ የሆነ በወይና ደጋ የሚበቅል የዕጽዋት ዓይነት
ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል!
ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጥር ነው!
ደሜን ሳደምጠው ውስጤን አገኘዋለሁ!
https://zehabesha3.rssing.com/chan-19551786/all_p45.html
“ሀገርን እግዚአብሄር ካልጠበቀ ሰራዊቱ በከንቱ ይደክማል”
September 27, 2014, 9:47 am
Previous ኢትዮጵያዊያንና ትግላችን፤ (ትግሉ ወደፊት እንዲሄድ ምን ማድረግ አለብን? )
ሥርጉተ ሥላሴ 27.09.2014 / ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/
ይህ ቃል አካል የሌለው ዬህዝብ አገለጋይ የሆነው ቃለ ወንጌል ነው። እንዴት ናችሁ የእኔዎቹ? እንኳን ለአዲሱ ዘመን እንዲሁም ለተዋህዶ አማንያን እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ – አደረሰን። ጠፍቼ ከረምኩ ባለመቻል። ንፍቅ አላችሁኝ።
ብዙ ሰው በጣም የሚጨነቅበት – የሚጠበብት መሰረታዊ ጉዳይ የሠራዊት መኖርና አለመኖር። የመሳሪያ – መጠንና ጥራት እንዲሁም የሎጅስቲክ ብቃት ታክሎ ስሌት ውስጥ ይገባል። ስለሆነም የነፃነት ትግሉ ውጤታማነትም ሆነ የድርጅቶች የብቃት ተልዕኮ በዚህው ይመትሩታል። ለእኔ ደግሞ ይህ ምንም ነው። ስለምን?
ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)
መሣሪያ ከአለመንፈስ ደጋፊነት ባዶ ነው። ሎጅስቲክም ቢሆን የፈቀደ መንፈስ ከሌለው ባዶ ነው። ባዶ + ባዶ ውጤቱ ባዶ ነው። ሰው ብቻውን ሆነ መሳሪያ ብቻውን፤ በተጨማሪም ሎጅክስቲክስ ብቻውን ባዶ ነው። የመጀመሪያው ነገር ፈቃደ እግዚአብሄር ወሳኝ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ውስጡ ዬነፃነት ራህብ የፈጀው የምልዕት ህዝብ የለማ መንፈስ አስፈላጊ ነው። አብሶ ለነፃነት ትግል ፍሪያማነት ነፃነቱን የፈለገ፣ የለውጥ አስፈላጊነት ከውስጡ ያመነ፣ ለለውጡ ሂደት መንፈሱን በገፍ ለመቀለብ የተሰናዳ፣ ለውጡን ለማዬት የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመቀበል የቆረጠ – የወሰነ፤ ግን ያልነፈሰበት መንፈስ ያስፈልጋል።
“የለማ መንፈስ” ይህ ማለት የጠላትን ፍሬ ነገር፣ ፍላጎተ – ግብ፣ መርምሮ ህዝብ ከነፃነት ትግሉ ጎን እንዲሰለፍ መንፈሱን ሊያነሳሱ፤ ሊያዳብሩ፤ ሊያንቀሳቅሱ የሚችሉ የህሊና ሥራዎች በስፋትና በተከታታይነት የመከወን አስፈላጊነትን ያጠይቃል። ሁሉ ሰው የሚያስበው ሁሉን ያወቀ ሆኖ እንደተገኘ አድርጎ ይገምታል። ይህ ስህተት ይመስለኛል። ለምሳሌ “ድርጅት ማለት” በፅንሰ ሃሳብ ደረጀ ሆነ በተግባር ሂደት፤ በፈተናዎቹ ዙሪያ፤ በተግባር ስንቅና ትጥቁ ዙሪያ፤ በመብትና በግዴታዎቹ አካባቢ ምን ያህሉ በቂ ግንዛቤ ወይንም ዕውቀት አለው? በጥናት ቢሰራ መረጃዊ ዳታው ከገመትነው በታች ቁልቁል ይወርዳል። ይህ ለናሙና ያነሳሁት ጉዳይ ነው እንጂ መንፈስን በጥንቁቅ አጥቂነት፤ ደጀንነት ወይንም አብሪነት ለማሰለፍ መጠነ ሰፊ ያልሰራንባቸው ጉዳዮች አሉን እንጂ ከብረቱ ቆጠራ ይልቅ ለድሉ ቅርብ የሆነው ጠላትን በለማ ህሊናና መንፈስ መርታት መስዋዕትነቱም ሆነ ጊዜው በጣም ቅርብ ያደርገዋል። እርግጥ ኃይል በጎጥ ያለተደራጀ ወጥ ኢትዮጵያዊ ሠራዊት ደጀን አያስፈልግም ማለቴ ግን አይደለም። የሆነ ሆኖ ላነሳሁት ነጥብ መነሻወችን ትንሽ ልበል።
ይቻላል። አዎን ይቻላል። ትልቁ መሳሪያ የህዝብን መንፈስን ልማት ለማስበል … “ራዲዮ” ፕሮግራም ሰፊውን ድርሻ ሊወጣ ይችላል። ሚሊዮወን የመሳሪያ ጋጋታ፤ የትጥቅና ስንቅ ሆነ ዬሎጅስቲክስ ድርጅት የሚሠራውን ፋይዳ ያህል የመከወን አቅሙ ራዲዮን አለው። እኔ እንደማስበው ዘለግ ባለ ብልጫ ራዲዮ ፕሮግራሞች ሊሠሩት ይችላሉ። ራዲዮ ፕሮግራሞችን በሁለት አቅጣጫ ከፍለን ማዬት እንችላለን።
- የኮምኒቲ ራዲዮ ፕሮግራሞች /በደጀንነት/ ለነፃነት ትግሉ የቀረቡና ጠላታቸውን ጠንቅቀው ያወቁትን ማለቴ ነው። እነዚህን ራዲዮ ፕሮግራሞች ውጪ ያለውን የነፃነት ደጋፊ፣ ማህል ሠፋሪ፤ ዝመተኛ ወገን፤ አልፍ ሲልም በጎጥ አስተዳደር ደጋፊነት የተሰለፈውንም አክሎ በአንድ ማዕድ ዙሪያ ሊያመጡ የሚችሉ መሰመሮችን እንዲከተሉ ማድረግ ይቻላሉ። ነገር ግን አብዛኞቹ በዚህ ዙሪያ ከሚሠሩት ይልቅ ለተደጋገመ መረጃ የሚሰጡት የአዬር ጊዜ ሰፊ ነው። ብዙዎቹ በጣም የተደጋጋመ ጉዳዮችን በተወራራሽነት ነው የሚነሱት። አንድ ሰው ቃለ ምልልስ ከተደረገለት ያው ደግሞ በሌላው ይደገማል ይሰለሳል። ይህ ለእኔ ጊዜን የሚበላ ዕዳ ይመሰለኛል። በዚህ ዙሪያ ሌላ ማንሳት የምሻው ጉዳይ ሁሉ ሰው የተስተካከለ ግንዘቤ እንዳለው – እንዳወቀ አደርጎ ይገምታል። እእ! በጣም በብዙ እርቀት ላይ እንደምንገኝ ሃቁን ብንቀበል መልካም ነው። መንፈሳችን አለመደራጀቱ የሚረጋገጠው ለተመሳሳይ ጉዳይ ምን ያህል አቅምን እያሾለኩ – አቅምን የሚሰልቡ አቅለ ቢስ ጉዳዮችን እንደምንከበክብ ሁላችንም እናውቀዋለን። ስለዚህ ሁላችንም ገና ነን። ስለዚህ መንፈሳችን በመስኖ መልማት አለበት …. ቢቻል ቢቻል የኮሚኒቲ ራዲዮ ፕሮግራሞችን በአህጉር ደረጃ እንኳን አቅጣጫቸውን ማዕከላዊ ለማድረግ ቢሞከር አንድ መንገድ ነው። ካልተቻለ ግን የኮሚኒቲ ራዲዮ ፕሮግራሞች “በመንፈስ ልማት” ላይ ሰፊውን የአዬር ጊዜ ቢሰጡ መልካም ይስለኛል። በተደራጀ ሁኔታ የመንፈስ ፈሎች ተከታታይ በሆኖ እንደ አልሚ ምግቦች መስጠት፤ በታቀደና በተሰናዳ ሁኔታ የማስተማር፣ የማሰናደት ተግባር መከወን ያለበት ይመስለኛል። ጊዜም ሆነ አቅም መባከኑ ካልቀረ ዒላማው ወደ ጎሎ ማነጣጠር አለበት። ይህ መስክ የተዘለለ ነው ማለት እችላለሁ።
- ሀገር ቤት የሚደርሱ የራዲዮ ፕሮግራሞች /በአጥቂነት/ እኔ እንደማዬው ሀገር ቤት በሚደርሱ ራዲዮ ፕሮግራሞች ላይ የጥራት – የብቃት የዝግጅት አቅም ሙሉ ነው። አብሶ የድምጽ ጉዳይ ለራዲዮ ፕሮግራም ወሳኙ ክፍል ነው። በዚህ በኩል ብዙም ችግር አላዬሁም። የመረጃው ዕውነትነትም እንዲሁ። እንደ ሥርጉተ መንፈስ የነፃነት ትግል ራዲዮ ፕሮግራሞች ከቤት መከራና ችግር የሚነሱ ተከታታይ መስኖችን በመንፈስ ሥር በመቀዬስ መስኩን ማልማት በሚመለከት ሰፊ ጊዜ ሊሰጠው ይገባል ባይ ነኝ። ለእኔ እራህብ ላይ ለሆነ ወገን መዝናኛ ፕሮግራም ወይንም ትረካ ምኑ ነው? የወያኔ ዜና የተንተራሰ መረጃ ከሆነ ሃቁን ሳይሸፋፍን የገለጠና የደፈረ የመሆንም አለበት ባይ ነኝ። የወያኔን የሚዲያ ቅጥፈት በሚገባ ማገለጥ በእጅጉ ያስፈልጋል።
ከዚህም ሌላ ዜናዎች ይሰማሉ ዜናዎችን መነሻ ያደረጉ የጠላትን የጎን አጥንት እንኩት ዬሚያደርጉ የህሊና ሥራዎች ግን እንብዛም ነው። ለምሳሌ አቶ ኤርምያስ ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በሰጡት መልስ ላይ “ማስፈራራት የሥርአቱ ባህሪ ስለሆነ እኔም ከዚህ ልወጣ አልችልም ነበር በማለት የእምነት ቃላቸውን ሰጥተውናል” ወሸኔ ነው። ይህ አገላለጽ የወያኔን ሆድ ዕቃ ቁልጭ አድርጎ ያሳዬ፤ ተረት ተረት ያልሆነ ተጨባጭ አምክንዮ ነው። በዚህ ዙሪያ ማገናዘቢያ ስለተገኘ ለዓለም ዓቀፍ የሰባዕዊ መብት አስከባሪ ድርጅቶች በሚጻፉ ደብዳቤዎች ላይ መረጃውን በትክክል ማቀበል። ሀገር ውስጥ ለሚቀጠቀጠው ወገንም አጫጭር ጹሑፎችን በማዘጋጀት በዚህ ዙሪያ ተከታታይ፤ ጠንካራና ጫሪ አቀጣጣይ ስሜቶችን አባብሎ ወደ ግንባሩ ማምጣት ይቻላል። ሰራዊት እምለው እኔ ይሄን ነው። ፈንጅም በሉት አዬር መቃወሚያም ሆነ ተዋጊ ጀትም እምለው ይሄን ነው። ለዛውም ቋፍ ላይ ላለ ምልዕትማ ከሚሊዮን ሠራዊት ወይንም የብረት ኳኳቴ በላይ በአጭር ጊዜ ምልዕትን መንፈሱን አሸፍቶ ለድሉ ማብቃት ይቻላል። አንጋጦ ሰማይ ከማዬት መሬት ላይ ያለውን ዕድል በቅጡ አደራጅቶ የመምራት አቅምን ይጠይቃል። ብዕርና ብራና እንዲሁም ሸበላ ድምጽ ብዙ ያተርፋሉ። በጎጥ የተጠቀሙ /የተሰፉ/ ዲሪቶዎችን ሁሉ አመድ የማደረግ አቅማቸውም አንቱ ነው። ከሁሉ በላይ ሰፊው ህዝብ በፋፋ መንፈስ የሚያገኘው ድል የራሱ ነው። የማንም – የምንም ጥገኛ አይሆንም። ተስፋው መዳፉ ላይ አሱን ብቻ ይጠበቃል።
እኔ እላለሁ – ከጠላት የሚመጡ ማናቸውም መረጃዎች ሁሉ ከዜናቸው ቀጥሎ መረጃውን ተንተርሶ የጠላትን አቅም የሚቀጠቅጥ፤ አከርካሪውን እንኩትኩት አድርጎ የሚሳባብር በጉልበታም ድምጽ አጫጭር ጹሑፎች የአዬር ላይ የትምህርት ዜግነት ት/ ቤቶች ናቸውና የዘመኑ ቅኝት በዚህ ላይ ቢያተኩር መልካም ነው።
ጹሑፎቹ ግልጽ፣ አጭር፤ በቀላል አማርኛ የተቀነባበሩ፤ ራህብን ጠረጴዛ ላይ ቁጭ አድርገው የሚያወያዩ መሆን ይኖርባቸዋል። ደቂቃው ቢበዛ አምስት ቢያንስ 3 ደቂቃ መሆን አለበት። ለነገሩ በራዲዮ ፕሮግራም እኮ ከአምስት ደቂቃ በላይ ህጉም አይፈቀድም። አጃቢ ሙዚቃው በሚመለከት ውስጥን የሚያቆላምጥ ግን የሚያስቆርጥ መሆን ይገበዋል ባይም ነኝ። ብሄራዊነት ወንጀል በሆነበት ሁኔታ ላይ ህዝብን ሆ! ብሎ እንዲነሳ ለማደረግ ከሻንበል፤ ከሻለቃ፤ ከብርጌድ፤ ወይ ከክፍለጦር በላይ አዛዥም ኮከብም ሳይኖር አቶ ራዲዮ መከውን ይችላል። ዜግነታችን ተጠቅጥቋል – ለነገም እንዲጠፋ ተዶልቶበታል፤ ማንነታችን ተረግጧል – ለነገም ስደት ታውጆበታል፤ ክብራችን ተፍቋል ለነገም መቃብር ተቆፍሮለታል። ከዚህ በላይ ሊመጣ የሚችል ነገር የለም – በፍጹም።
መሳሪያ ለሚቆጥሩ፤ የሠራዊትን አቅም ለሚያገኑ ወይንም ለሚያንኳስሱ ወገኖች እኔ የምላቸው መሣሪያ ዬሰው ልጅ ያለው በእጁ ነው። እሱም አንጎሉ ነው። አንጎሉን በሚገባ መምራት ከተቻለ ድሉ በእጅ ነው። የወያኔ ሽንፈቱም አይቀሬ ነው። አለኝ ለሚለው ሠራዊት እሱ ከሚነዛው የጎጥ ፕሮፖጋንዳ ይልቅ ተጨባጩን እንዲተረጉም መንፈሱን ማልማት ከተቻለ አረሙ ወያኔ ባደራጀው ዬእኔ ባለው ሠራዊት ይቀባራል። ነገር ግን ይህ ከግብታዊነት ሆነ ከበቀል የጸዳን የመምራት አቅምን ሆነ ብቃትን ይጠይቃል። አብዝቶ ማሰብን – ማብሰልንም።
ከዚህ ላይ እንደ ህልም – እንደ ታምር የማዬው አንድ ሀቅ አለ። “የድምጻችን ይሰማ” የአመራር – የክህሎት ተመክሮ – የእውቀት መብለጥ – ብቃት ለእኔ የዘመኑ ፊኖሚናል ነው። እንደ ማንኛውም እንቅስቃሴ በውስጣቸው ፈታኝ ሁኔታወች ገጥሟቸዋል። የወጣት ጆዋር ጉዳይ ብቻም ሳይሆን እሱን ተከትለው የተመዘዙ ህፃፆች። ለንቅናቄው እጅግ ፈታኝ ነበር። መሪዎቻቸው ደጋፊዎቻቸው ተሰቃይተዋል፤ ታስረዋል፤ ተገድለዋል። ግን ተዘናጉ? ተረቱ? ወይንስ ፈረሱ? በፍጹም። በአዲስ መንፈስና ሃይል፤ በብቁ ስልትና በስልጡን አመራር ደምቀው አሉ። የለማ የመንፈስ ሀብታት ባለቤቶች ስለሆኑም በአኃታዊነት ፍላጎታቸውን ለማስፈጸም ትጉሃን ናቸው። አቅም አይባክንም ወይንም ሲሾልክ አይታይም። የሚገርመው ነገ ሰላማዊ ሰልፍ ከኖራቸው እንዲቀር ሰልፉ ሌሊት ቢወሰን በተቆረጠው ሰዓት አንድም ሰው በሰልፉ ቦታ ዝር አይልም። በምን ታምር ይህን እንደሚከውኑት ጥበቡ ልቅናው ዘሊቅ ነው። መሪና ተመሪ በትክክል በእትብት የተገናኙበት ከድንቅ በላይ አመክንዮ ነው – ለእኔ። ለእኔ ይህ ንቅናቄ ተስፋዬን የሚያለምልም ንጹህ አዬሬ ነው። ልንማርበት የሚገባ የተግባር ተቋም። ዘመኑ መማሰን ያለበት ተመክሮውን እንደ አንድ የልምድ ማዕከል ማደረግን ነው።
እኔ በግሌ እምመኘው እንዲህ ዓይነቱ፣ ፍጹም የላቀ አዎንታው የአዛዥና የታዛዥ የፍላጎት አዎንታዊ ጋብቻን ነው። ወይንም የመሪና የተመሪ አዎንታዊ የራዕይ ጋብቻን ነው። ይህን ለማምጣት ደግሜ – ደጋሜ እምገልጸው ነገር እራሰን አሸንፎ ለማደር መቁረጥና መወሰንን ነው። ስልቶቻችን – ሂደቶቻችን በመመርምር ወቅቱን ያዳመጠ፣ ከዘመኑ ጋር ሊሄዱ የሚችሉ ፈጠራዎችን አክሎ አዲስ መስመርን መከተል የነፃነት ትግሉ ያለበት ይመስለኛል።
የሠራዊት ሆነ የመሳሪያ ብቃት መለኪያው ለእኔ መንፈስን የማልማትና ለማብቀል ዝግጁ የማደረግ በእንግሊዘኛው /ፈርታይል/ መሆኑን ነው። ይቅርታ ፎንቱን ቀይሬ በእንግሊዘኛ አልፋቤት ለመፃፍ ለጊዜው አልችልም። /ፈርታይል/ መደረስ … ሴት ልጅ ልትጸንስ የምትችልበት ጊዜ አላት። የነፃነት ትግሉም ጊዜና ወቅት እንዲሁም ፈቃደ እግዚአብሄርና ቀን ያስፈልጋቸዋል። ቅድመ ሁኔታውን ማሟላት ደግሞ የሁላችንም ግዴታ ነው። ወቃሽም ሆነ ተወቃሽ ሊኖር አይገባም። የጎደለውን መሞላት የሁላችንም ነው። እንደ እኔ ፊት ለፊት ወጥተው ከጠላት ጋር በማናቸውም ዘርፍ ለመታገል የቆረጡ ሁሉ ሊደገፉ፤ ሊበረታቱ ሊመሰገኑ ይገባቸዋል። ተከፍሎት የሚሰራ የለም። አብዛኛው ነፃ አገልግሎት ነው የሚሠጠው። ካላ ቋሚ የፖለቲካ ሠራተኛ ወይንም ፋንክሽነሪ የነፃነት ትግል ጉዙ ረጅም መሆኑንም መቀበል ያለብን ይመስለኛል። ይህም ቢሟላ እንኳን በጎጥ የተደራጀን መንፈስ አሸንፎ ህዝባዊነትን ለማምጣት የሰከነ ትዕግስት – በማስተዋል የተቀመመ ተግባር ይጠይቃል።
በተረፈ የኔዎቹ አብርሽ በዘሃበሻ የተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በኢሳት ምርጥ ሰውነታቸው ድምጽ ስላገኘ ደስ ብሎኛል። ጀግና አልጋነሽ ገብሩ ደግሞ ልጆች ት/ቤት ከመጀመራቸው በፊት መፈታቷ ሰላም ሰጥቶኛል። በተረፈ ሳይታክቱ ሌትና ቀን የአራዊትን ግፊያና ግልማጫ ችለው የሚሰቃዩትን የእስረኛ ቤተሰቦች፤ የትዳር አጋሮች፤ ልጆች፤ ደጋፊዎች፤ ጠያቂዎች ሁሉ ላደረጋችሁት መልካም ነገር ሁሉ ምስጋናዬን ሆነ አክብሮቴን ሸልሜ የልቤን የሚያደርስልኝን ዘሃበሻ ዝቅ ብዬ አመስግኜ ልሰናበት። መሸቢያ – ሰንበት።
ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል!
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
https://zehabesha3.rssing.com/chan-19551786/all_p49.html
አፍንጫህን ላስ –አቶ ሂደት።
Next “ሰው በላ” በሆኑት የኢህአዴግ ሙሰኞች ላይ ኮሚሽኑ ለምን ይሽኮረመማል?
Previous ለአልሙዲ “ማፅናኛ”
ከሥርጉተ ሥላሴ ሲዊዘርላንድ ዙሪክ
እኔ ነኝ አቶ ሂደትን አፍንጫውን እንዲልስ የፈለኩት። ሃሳቤን የሚጋራ ትብብር ካለም ደስታውን አልችለውም። በ16.03.2014 ጀንበር ዘቅዘቅ ከመለቷ በፊት ዘሀበሻ ስገባ አንድ አዲስ መረጃ አገኘሁ። የአንድነትና የመኢአድ ቅድም ውህደት መሰናዶ።
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/13623 ዘግዬት ብሎ ደግሞ ማምሻ ላይ ለሁለተኛው ቀን በደብተራ ክፍል አዲሱን ዜና አበሰሩ ለታዳሚው የአንድነቱ አቶ ሃብታሙ አያሌው። እንደ ድሮው ቢሆን እንዴት? ወዴት? ለምን? እያልኩ መንፈሴን አመሰው፤ አውከው ነበር። አሁን ግን አዳማጠኩ አቶ ሂደትን ማዬት ነው ፍሬውን። በቃ! ጅልነት ቀረ ወላለቀም። ነገም የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና ከባዶ ሳጥን ቆጠራ በኋላ አቶ ሂደት ሌላ ትዕይነት ይዞ ከች ቢል አፍንጫህን ላስ በመጣህበት መንገድ ብዬ ቅንጡን አብርሬ ማሳፈር። ሞኙን ይፈልግ …. ይበቃል የተዳቀቅነው —-
ይልቅ አቶ ሀብታሙ በ16.03.2014 በነገሩን ሰበር ዜና ላይ የተፈለፈለ ቁምነገር አብሬ አዳመጥኩኝ። ኮረቻ ላይ ቁጢጥ ያለ „ኢጎ“ አላሰራም ካላ በመጣበት መንገድ ለመሸኘት መወሰኑን። ይህ ማለፊያ ነገር ነው። ግን ላይ ብቻ ነው „ኢጎ“ ያለውን አቶ ሀብታሙ? ታችም አለና ታቹም ላዩም በተገባው ይቃኝ ባይም ነኝ። እንዲውም መጋኛው ያለው ከታች ይመስለኛል። ለማንኛውም እኔ ጅልነትን ስለቀበርኩት አቶ ሂደት በፈለገው ቅርጽና ይዘት ሊያወናብድ ቢያነፈንፍ ቅስሙን እንኩት። የጀመረውን የማተራመስ ማሳ ለቀቅም አድርጌለት ከቻልኩ ማገዝ በሰተቀር ግን መፈሳፈስ፤ መፈራረጅን፤ አጋ ለይቶ በገጀሞ መከታከትን እሱ እንደሚጠብቀው ስለማውቅ አፍንጫህን ላስ ብዬዋለሁ። አሁን ተዋውቀናል። በዛች ቆልማማ አፍንጫው እሱ ከመሳቁ – ከመሳለቁ በፊት እኔ ቅድም …. ማን ሞኝ አለ።
ሌላው አቶ ሂደትን የምጠብቀው ቁም ነገር እንዳለ እስቲ ላስታውስህ። በዚህ ገጥመህ በሰፋኽው ማሳህ ብቃት ያላቸው ሴቶች ከገንዘብ ያዥነት ወይንም አቻዎቻቸውን ከሚመሩበት „የሴቶች ጉዳይ ክፍል“ ሸገር ያለ ወንዝ የሚያሻግር ላቅ ያለ ድርሻ እንዲያው ታምነው ይስጣቸው ይሆን?! ያው በአጭሩ ቢቀረጠፍም አንድነት የመጀመሪያው ፓርቲ ነው ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳን የሊቀመንበርነቱን ቦታ ሲሰጥ። ለዚህም ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ከአንድ ብሄራዊ ፓርቲ መሪዎች ዝርዝር ታሪክ ውስጥ አይኔ በክብር አለችና።
ከዛም በኋላ ምን ነበረ? ርዕዮትዬን ስጠብቅ ጭራሽ ተፈናቃይ አደረጋት አቶ ሂደት። አሁንስ ከቶ ምን እዬተመከረ ይሆን? …. እርግጥ እነ ወይንዬም ጠንከር ብለው ጎልተው እዬወጡ ነው። …. „በሴትነታችን ሳይሆን በብቃታችን“ በማለት …. ለማንኛውም ዘመነኛው ሂደት ይጠበቃል። መፍትሄውን እዬዘለለ ይህ ሂደት የሚባል ጉድ እኛንም አሞ ከሞ ያጫውተናል እንጂ የድሉ መናገሻ ፍሬ ነገር እኮ ይታወቃል። እነ ሚሚ እነ ቱቱ እነ እሙዬ እነ ሜላት ተናገሩ እኮ! ውይ! አንድ ነገር ረስቼ „ነገረ ሴቶችን“ የሚያዳምጥ ጆሮ የሚገዛበት ቦታ የምታውቁ አላችሁን? ከሰማችሁ እባካችሁ ….?! ለሚነግረኝ ትንሽ ሽልንግ ቢጤ በመቀነቴ ቆጣጥሬ እዬጠበኩ ነው ….
ሌላ ምን ነበር? ብቃትና አቅም አዬሁኝ ከ15.03.2014 ከአቶ ሃብታሙ አያሌው የደብተራ ሩም ቆይታ። ወያኔ አዘጋጅቶ በነበረው የሚዲያ ፓናል ዲስክሽንም ክርክም ያለች፤ ክሽን ያለች አንጀት አርስ ቦንብ ነበር ያጎረሱት ሽፋታውን ወያኔ፤ ወያኔ ከጫካ ወደ ከተማ ኑሮውን ሲያደላድል የ2ኛ ክፍል ተማሪ የነበሩት አቶ ሃብታሙ አያሌው። ለነገሩ አዲስ አበባም እኮ ለወያኔ ጫካው፤ መንፈሱ ጫካ፤ ህሊናው ጫካ …. ለአራዊትነት የተፈቀደ ግዛት ….. በጫካ ቲወሪ መደናበር —-
የአንድነት አዲስ መዋቅር፤ የመድረክ ምስረታ ሰሞናትም የአደራ ጠባቂው አቶ አንዶአለም አራጌ እንዲህ ከዓይን ያውጣህ የተባለ መንፈሰ ሊጋባ ነበር። የእኔ ስጋቴ እንዲህ ጎልብቶ የወጣ አቅምን ማዬት የሚፈልጉ፤ ማድመጥ የሚሹ፣ እንደ ብርቅ የሚያዩ፣ ይህን ሃብት ጥቅም ላይ ለማዬት የሚጓጉ የመኖራቸውን ያህል ተመሳስለው ያሉ የግል ኢጎ ቁስለኞች ደግሞ ከአረሙ ጋር በማበር ሌላ የጨለመ ትዕይነት እንዳይመጣ እንቅልፍ አለባው ሥርጉተ ትሰጋለች። ይፈቀዳል አይደል መስጋት …. ? ? ?
እኔ እነዚህ የትውልድ አዲስ ተረካቢ ወጣቶቹ ጥንካሬ ፈጽሞ የማይጠበቅ እዬሆነበኝ ነው። ግንዛቤያቸው፣ ዕያታቸው ከምኑ ነው የዛቁት? ይገርማል – ይገራል። ከመራራው የዕንባ ጅረት ሳይሆን አንደማይቀር ሰማይ ቤት ላይ ያለው የክሮስፖንዳንስ ሠረተኛ ጠቁሞኝ ነበር አንድ ቀን እንደ ዋዛ። …. ታዲያ እኛ ይህን የሚያሰተናግድ ንጡህ መንፈስ አለን ነው ጥያቄው … ከዚህው ከአቶ ሃብታሙ ማህደር ሳልወጣ ትንሽ ቆዬት ባለቸው የቃሌ ክፍል ቃለ ምልልሳቸው „መንገዱ ተጀመረ“ ልጃቸውን የትዳር ጥንዶቹ በጉራጌኛ የጠሩበት ስያሜ ነው። የኢትዮጵያን ቀለማም ማንነት እንዲህ ፈቅደው ያስጌጡ ናቸውና ተዚህ ላይ አቶ ሂደትን ቸር ወሬ ስላሰማኝ ለጥ ብዬ አመሰገንኩት። ውሳኔው ያስተምራል – ይመራል። የአዲሱን ትውልድ መንፈስም አሳምሮ ያሳያል …. ሌሎቻችንም ይልመድብን። እኔ ትርጉም የሚሰጡኝን ነገሮች በአግባቡ ነው አክብሬ የምይዛቸው። ጠብ ብላ የምትፈስ ጠበል የለችም። ሥጋና ምን ተባለዬ ቤት አይደለሁም ….
ገጥሞ መስፋት ያልኩት በአሉታዊ እንዳይታይብኝ። አዎንታዊ ነው። አኔ እራሴ ተገጥሜ ተሰፍቼ ነው በህይወት ቁሜ እንደ ጥንቱ ከሞት ተርፌ ሰው ሆኜ ቆሜ ያለሁት። የእውነት እምተርፍበት ሁኔታ በጣም ስስ ነበር። ግን ፈጣሪ ይመስገን ተገጥሜ ከተሰፋሁ በኋላ ሶስት ዓመት ተጨመረልኝ። በኋላም ይመጣሉ ተብለው የተሰጉት ነገሮችም በሃኪሞቼ እንደተተነበዩት አይደለም በጣም በእጅጉ የቀነሰ ነው።
ሌላ አንድ ነገር የቀረ ደግሞ አለኝ። አቶ ሂደት አለህ? ሆሆ ትሰማኛለህ? ከልብህ እባክህ አዳምጠኝ – ቢተ? (bitte? እባክህ?)? ገጥመህ ስትሰፋ ደስ ብሎህ ፍንክንክ ፍልቅልቅ ብለህ ተቀበሉኝ እንደምትለን ሁሉ „ተገጥሜ ለመሰፋት ጊዜዬ ገና ነው“ ላላው ልጅህ ደግሞ ነፃነቱን ፈቃዱን ጠብቅለት። ከነፃነቱ ጋር እዬሄድክ አትላተም። „ጊዜ ገቢረ ለእግዚአብሄር“ ይላል ወንጌሉ። እሱን መለስ በልና ገልበጥ አድርገህ ከቃሉ ጋር ጥድፊያህን አሰማማው። „ሲሮጡ የላኩህም“ አትሁን። አደብ የትውልዱ መንፈስ ነው፤ ለነገሩ ይሄ ሚስጥር ጠጠር ብሎብሃል አይደል?። ከሌለህ ደግሞ ቅዱስ ወንጌል ያለውን ይሄው እኔው እህትህ አስታወስኩህ። ካለጊዜው የተፈጸመ ድርጊት ታምራዊ አንድ ነገር ብቻ ነበር። የቃና ዘገሊላ የድንግል ማርያምና የልጇ ፍቅራዊ ሂደት። „መጠበቀን“ የመሰለ ነገር የለም። መጠበቅ ለእኔ የዲያመንድ ጮራ ነው።
ለነገሩ አንተ መስማማትን አትወድም። በምን አቅልህ? እንደ ሽፍታው ወያኔ እኮ አቅልህ የተዘቀዘቀ ሸውሻዋ ነህ። ደግሞ ታስፈራራለህ ወዮ! እያልክ አትስማሙ እያልክ፤ በእንትን በቅብጥርስ እያልክ ስታምሰን ከረምክ። አሁን ተነቃብህ። አፍንጫህን ላስ ተበላክ …. ጉድህ ፈላ …..። እዬተወላገዱ ሙድ ማሳት ተመነጠረ። አዬህ አቶ ሂደት …. መንፈስ ሲሰበሰብ አቅም ወግ ይደርሰዋል።
ብቻ አደራ እንደዚህ ለግለግ እያሉ የሚወጡትን ቀንበጦቼን ወደ ቃሊቲ …. እንዳታስባቸው እንጂ፣ እኛም ልክ እንደ ጀግናው አበበ ቢቂላ ቀደመንህ ልብ ገዛን። ከአንተ ጋር አብረን ወገኖቻችን በሰባራ ሰንጣራው መውቃት፤ መድቃት፤ ማብጠልጠል ቅርት፤ ምን ይውጥህ? ትላንትን አሳዬህን፤ ዛሬንም ሻምላ ጋሬጣ አዘጋጅተህ በሉ ልያችሁ የማን ደም ፈሰሰ ቀረ። „አሞራው በረረ ቅሉ ተሰበረ“ ሆነልህ – ትልምህ። እኛ ምናችን ሞኝ?! እቴ! ሞኝህን ፈልግ ብለን … በተደሞ ማዬትን መረጥን። ስንችል ደግሞ የምንችለውን ማጉረስ። ምን ይውጥህ?! ….. አንተ ምንትሶ – ቅብጥርሶ፤ ደልቅ ከዘመንኛው ጥጋበኛ ወያኔ ጋር … አንድ ቀን አንተም እንዲህ እዩዩኝ ስትል እንክት ትልና …. እንደ ጦር የምትፈራው „ገናናው ኢትዮጵያዊነት“ በአኃቲ ማዕዶት … በሽንጣም ሞሰብ ቅብጥን ቅልጥ በማለት በናፍቆት ማር የምታዘንበው ሀገራችን ላይ … ተግባባን ጌታው አቶ ሂደት። ለነገሩ ሰንደቅአላማን ገንባሌ አድርጎ ቀን ሳይታደል ካለአለአቅሙ፣ ካለወርዱም የተኮፈሰው ውሽልሽል የጎጥ ቅራቅንቦ „ኢትዮጵያዊነት“ ከእኔ ወዲያ ላሳር እያለ ነው አሉ …. አያልቅበት ቀዳዳ ዲሪቶ መጣፍ። ሰው ይተዘበኛል አይል? አይኑን በጥሬጨው ያሸ ጉድ …. „መሳቂያው ፓርላማ“ አለ አቤ ቶኪቻው። በል ከመሰናበቴ በፊት ተጠይቅ አስሰኪ አንድ ጥያቄ ከቶ መቼ ነው ከዚህ ኪስ አውላቂ የድቡሽት ቤት ጎጠኛ ሽፍታ ጋር የምትፋታው? የናፈቀኝ አሱ ነው …. ህልም አይከለከል ነገር ..
የእኔዎቹ እንዴት ናችሁልኝ። አብረን በመቆዬታችን ደስ ሲለኝ ስንበቱን ሳስብ ደግሞ ክፍት አለኝ። ባር ባር እያለኝ ናፍቆቴን በፍቅር ጥበብ አሳምሬ ቸር እንድተሰነብቱልኝ ተመኝቼ ልሰናበት። መልካም ጊዜ። ማይክ ፍሪ ….
እልፍ ነንና እልፍነታችን በተግባር እልፍ እናድርገው።
እግዚአበሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ ሥላሴ።
Related Posts:
https://zehabesha7.rssing.com/chan-12472427/article1313.html
ኢትዮጵያ የዜግነት መብት ተከብሮ ሁሉም በእኩልነት የሚኖርባት ሀገር ትሁን!!!
Tuesday, October 31, 2017
ለመሆኑ በብርሃን ጸዳል የተሽቆጠቆጠችው፤ ከሀገረ ቻይና እና ከብራዚል ጋር ዓለምዐቀፍ ተሸላሚዋ ዘመነኛዋ ትግራይ ግራጫ ጸጉር አላትን?
By ሳተናው
ከሥርጉተ
– ሥላሴ
31.10.2017 /ሲዊዘርላንድ
– ዙሪክ።/
„ … እንሆም፣ ሁሉ እሾህ ሞልቶበታል፣ ፊቱንም ሳማ ሸፍኖታል፣ የድንጋዩም ቅጥር ፈርሷል።
/ መጽሐፈ ምሳሌ ተግሣጽ ምዕራፍ 24 ከቁጥር 30 እስከ 31/“
እንደ በር።
ሥርጉተ ሥላሴ
በመጀመሪያ
ጥናቱንና መቀነቱን 40 ዐመት ሙሉ በዕንባ ክርትት ለሚሉ ለኢትዮጵያ እናቶች እንዲሰጥልኝ አምላኬን እማጸነዋለሁ። በሥጋ የተለዩትንም ወገኖቼ ሰማዕትነታቸውን ፈጠሪዬ ይቀበልልኝ ዘንድም እማጸነዋለሁ።
በማስከትል … ወደ ዋናው ጉዳዬ ከመሄዴ በፊት ግን የአዋዜ አዘጋጅ ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ የሰሞናቱን የአማራን የተደራጀና የታቀደ ጭፍጨፋ አስመልክቶ የሠራው ዜና እጅግ ውስጥን የተረጎመ፤ ሩቅ አሳቢና መንገድ ጠራጊ ዕድምታ ስለነበረ እጅግ አድርጌ ላመሰግነው ፈቀድኩኝ። ደፋር፤ ጥልቅ ትንታኔ ነው። ቅርብ – ከሩቅ ጥቃትን ያዋደደ ነው። ዓለም – ዓቀፋዊ ሰቅጣጭ የጭካኔ ዕውነታዎችን፤ ሁኔታዎችን በምልሰት የቃኘበት መንገዱ ብጡል ነው። አማራ እኮ ሐገር አልባነቱ ተውጆበታል። የከፈለው ደም ከንቱም ሆኗል። ስለሆነም የአዋዜ የንጽጽሩ የአምክንዮ አቅሙ አንቱ ነው። ለህሊና ቅድመ መሰናዶ ልዩ ተቋምም ነው። ለአማራ ሥነ – ልቦናዊ አኃቲነትም በኲራት ነው። አጭር ግን ልቅም ያለ፤ ልቁን የአማራን ዬዘር ጥፋት ትልም በጥልቀት የመረመረ፤ በስፋት ያስተዋለ፤ በውስጥነት የተቀበለ፤ የጉዳቱ ልክ በአትኩሮት እንዲታይ ፈር ቀያሽ የሆነ – መጸሐፍ ነው። ተባረክ!
No comments:
Post a Comment
http://equalright4all.blogspot.com/2017/10/blog-post_70.html
ኢትዮጵያ የዜግነት መብት ተከብሮ ሁሉም በእኩልነት የሚኖርባት ሀገር ትሁን!!!
Tuesday, October 31, 2017
ለመሆኑ በብርሃን ጸዳል የተሽቆጠቆጠችው፤ ከሀገረ ቻይና እና ከብራዚል ጋር ዓለምዐቀፍ ተሸላሚዋ ዘመነኛዋ ትግራይ ግራጫ ጸጉር አላትን?
By ሳተናው
ከሥርጉተ
– ሥላሴ
31.10.2017 /ሲዊዘርላንድ
– ዙሪክ።/
„ … እንሆም፣ ሁሉ እሾህ ሞልቶበታል፣ ፊቱንም ሳማ ሸፍኖታል፣ የድንጋዩም ቅጥር ፈርሷል።
/ መጽሐፈ ምሳሌ ተግሣጽ ምዕራፍ 24 ከቁጥር 30 እስከ 31/“
እንደ በር።
ሥርጉተ ሥላሴ
በመጀመሪያ
ጥናቱንና መቀነቱን 40 ዐመት ሙሉ በዕንባ ክርትት ለሚሉ ለኢትዮጵያ እናቶች እንዲሰጥልኝ አምላኬን እማጸነዋለሁ። በሥጋ የተለዩትንም ወገኖቼ ሰማዕትነታቸውን ፈጠሪዬ ይቀበልልኝ ዘንድም እማጸነዋለሁ።
በማስከትል … ወደ ዋናው ጉዳዬ ከመሄዴ በፊት ግን የአዋዜ አዘጋጅ ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ የሰሞናቱን የአማራን የተደራጀና የታቀደ ጭፍጨፋ አስመልክቶ የሠራው ዜና እጅግ ውስጥን የተረጎመ፤ ሩቅ አሳቢና መንገድ ጠራጊ ዕድምታ ስለነበረ እጅግ አድርጌ ላመሰግነው ፈቀድኩኝ። ደፋር፤ ጥልቅ ትንታኔ ነው። ቅርብ – ከሩቅ ጥቃትን ያዋደደ ነው። ዓለም – ዓቀፋዊ ሰቅጣጭ የጭካኔ ዕውነታዎችን፤ ሁኔታዎችን በምልሰት የቃኘበት መንገዱ ብጡል ነው። አማራ እኮ ሐገር አልባነቱ ተውጆበታል። የከፈለው ደም ከንቱም ሆኗል። ስለሆነም የአዋዜ የንጽጽሩ የአምክንዮ አቅሙ አንቱ ነው። ለህሊና ቅድመ መሰናዶ ልዩ ተቋምም ነው። ለአማራ ሥነ – ልቦናዊ አኃቲነትም በኲራት ነው። አጭር ግን ልቅም ያለ፤ ልቁን የአማራን ዬዘር ጥፋት ትልም በጥልቀት የመረመረ፤ በስፋት ያስተዋለ፤ በውስጥነት የተቀበለ፤ የጉዳቱ ልክ በአትኩሮት እንዲታይ ፈር ቀያሽ የሆነ – መጸሐፍ ነው። ተባረክ!
“… ያለው የገዳ መስፋፋት፣ አስምሌሽን እና ወረራ እንጂ ተረኝነት አይደለም…!!!”
ሥርጉተ ሥላሴ
“ተረኝነት ስትል የባጀህ የእጭ ፖለቲካ አራማጅ ሁሉ ዕወቀው ጉድህን – “የብልፅግና መንግስት 11ኛ &12ኛ ክፍል አማርኛ ቋንቋ እንዳይሰጥ ከልክሏል። አማራና እና አማርኛ ቋንቋን ማዳከሙ እንደቀጠለ ነው። ተረኝነት እንጂ ለውጥ የለም””
… ያለው የገዳ መስፋፋት፣ አስምሌሽን እና ወረራ እንጂ ተረኝነት በፍፁም አይደለም። ከዬኔታ ጎዳና ያዕቆብ በስተቀር ይህን እውነት የደፈረው የለም።
እሳቸው ከተረኝነት በላይ ነው ሲሉ አዳምጫለሁ። እኔ በ2019 ፅፌያለሁ። ለአፍሪካም እንደሚያሰጋም።
• ደጉ ሳተናው ለጥፎት ከ400 እስከ 600 ሰው ሼር አድርጎታል። በ2019 ነው የተጻፈው። አንቱ የተባለው ሚዲያ ሆነ ተንታይ አሁንም „ተረኝነት“ እያለ ያሽሞነሙነዋል የገዳን ወረራ። እኔ ግን በ2019 ይህን ጽፌያለሁ። ልባም ሰው ግብቶ ብሎጌ ላይ ማንበብ ይችላል።
https://sergute.blogspot.com/2019/12/blog-post.html
2019 ዲሴምበር 16, ሰኞ
ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።
ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም። ከዚያ የከበደ መከራ ላይ ናቸው አላዛሯ ኢትዮጵያም ሆነ እማማ አፍሪካም።
ይህ ያን ጊዜ የተጻፈ ነው። ገናም ገና … ጦርነቱ ላዛ ግርዶሽ ነው። የሽብሩ ሱናሜ ለዛ ግርዶሽ ነው። ገና ምን ታይቶ …
“ተረኝነት” የሚለው እጭ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ነው። ተጋድሎውንም ያስተኛው ይኽው ነው። ለዚህ የባልደራሱ አቶ ገለታው ዘለቀ ሰፊውን ድርሻ ተወጥቷል። ያው ከውጭ የሄደው የገዳ ልዐልት እና መሳፍንት ተልዕኮው ይኸው ነው። በ ኢትዮጵያኒዝም ዝም ኦሮሙማን የበላይ እድርጎ ማስቀጠል።
ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ተንታኞች ሚዲያወች በፍፁም ከወሳኙ አስኳላዊ ዕውነት ሊነሱ አልቻሉም። ገናም ገናም። ይህ የእከሌ ተከሌም አይደለም። የሁሉም ችግር ነው። ድህነት።
ወይ አልገባቸውም። የገባቸው እንደ ገዳ ገለታው ዘለቀ ዓይነቶች በዕውነት ላይ አድፍጠዋል።
Filed in: Amharic
https://ethioreference.com/archives/29297
ያለው የገዳ መስፋፋት፣ አስምሌሽን እና ወረራ እንጂ ተረኝነት አይደለም...!!!" ሥርጉተ ሥላሴ
መልካምነት የተፈጥሮ ፍልስፍና ብቻ አይደለም ከዚህም ይልቃል። መልካምነት የመኖር ሥነ -ሳይንስ ብቻ አይደለም መልክዐ ሰውም ነውም። መልካምነት ሰው ሰራሽ አይደለም የፈጣሪ ፍጥረት እንጂ። መልካምነት ሩቅም አይደለም ቅርብ ነው – እናት። መልካምነት ባዕድም አይደለም ሥጋና ደም ነው – መንፈስም። መልካምነት ቅርብ በጣም ቅርብ በውስጥ ያለ ስሜትን በቅንነት የመግራት ጥበብ የማስተዋል የቅኔ ጉባኤ ነው። ራስን የመግዛት ብቃት። መልካምነት የፈጣሪ ጸጋ ነው ሳይበላለጥ ለሁሉ እኩል የተሰጠው። መፍቅዱ የባለቤቱ ይሆናል። መልካም በማሰብ ብቻ ነው ሐገር መገንባት የሚቻለው፤ መልካምነት ብቻ ነው ትውልድን ሊያስቀጥል የሚችለው። መልካምነት ብቻ ነው ተስፋ ፈጥሮ፤ ተስፋን ከብክቦ ተስፋን ማግኘት የሚያስችለው። በመልካምነት ተስፋ ሲከበከብ የመልካምነት የማበልጸግ አቅሙ ከፍ ይላል። የመልካምነት ሐዋርያ መልካም ላለሆኑ ምግባሮች ጊዜ አይኖረውም። ስለምን? መልካም አለመሆነን አሸንፎ የተፈጠረ ነፍስ ስላለችው። ለቀጨሬ መጨሬ፤ ለምንትሶ ቅብጥርሶ፤ ለእንቶ ፈንቶ ስርክራኪ ጊዜ የለውም። ዕድሜውም አይሾልክም። ቁምነገራም ዕድሎችን የመጠቀም አቅሙ አንቱ ነው – መልካም ሰው። ራስ እግሩ ዝቀሽ ነው በሰብል። ህሊናው የፋፋ እና የዳበረ ነው የለማ። ለዚህ የተፈጠረ ሰው የሚውልበት መስክ ሁሉ የህውከት አውሎን ጸጥ ረጭ የማድረግ ልዩ የአቅም ተስጥዖ አለው። ልስላሴው ሰው የእጅ ሥራ አይደለም። በልስላሴው ውስጥ
“ቤት በጥበብ ይሠራል በማስተዋል ይጸናል።” (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፬ ቁጥር ፫) “ክፋት ስታዩ ያን ለማድረግ የምትሞክሩ ከሆነ ተሸንፋችኋዋል ማለት ነው። የሰው ልጅ በጎን ለማወቅ ያለው ጥረቱ ተሽንፏል።” – ዶር አብይ አህመድ ጠ/ሚር ከመሆናቸው በፊት ከተናገሩት የተወሰደ።
ሞገደኛው ተክሌ ውስጡን አስነበበኝ - የስሞተኛው ብዕር
ሥርጉተ ሥላሴ
ይድረስ
ብለናል
ከወደ
ሲዊዘርላንድ
ዙሪክ
እኔና
ብዕሬ
ለሞገደኛው
ብዕረ
ተክሌ
...
ጭራሽ ተበዳይ ብዙኃኑ ተወቃሽ ሆነ? ይገርም! ጡር የሚባል ነገር አለ። በፈጠረህ ጡር ፍራ የስሞተኛው ብዕር ...
እንደምን አለህ ሞገደኛው ተክሌ? ደህና ነህ ወይ? ጠፍተህብኝ ጭንቅ ብዬ ሳለ ዬወጣት ጃዋር ዶክተሪን በመቃወም ከሰሞናቱ ፊርማ የማሰባሰብ ዘመቻን ተከትሎ ብዕርህን ብቅ አደረገችህና ደስ አለኝ። የእውነት ናፍቆትህ ግድል አድርጎኝ ነበር። እኔማ የኦሮሞና የአምራ ትዳር ፈርሶ የነገ ሀገር ተረካቢዎች እንዲበተኑ፤ እንዲሁም ከሁለት ብሄረሰብ የተወለዱ ወገኖች ጥግ አጥተው ሜዳ አደር እንዲሆኑ ሲታወጅባቸው፤ ያው በትንሹም በትልቁም የምታብጠለጥለው ብሄረሰብ ቁምጥና መላያው ተደርጎ ሲቀጠቀጥ፤ አንድ ታላቅ ማህበረሰብ ሞትና መፈናቀል ሲታወጅበት፤ መዲናች ተለቃ የንጹኃን አንድትሆን ሰባት አንቀፆች ያሉት ድንጋጌዎች ሲተረተረ፤ ኃያሉ ሚኒሊክ ሃውልታቸው ፈርሶ ፈረሱ ወደ ኦሮሚያ ሲጫን፤ ክብራቸው ትብያ ሲለብስ፤ የወሎይቱ ወርቂቱ አፄ ቴውድሮሰን አነጣጥራ የገደለች ስለመኋኗ ሲነገርላት፤ አፄ የኋንስም ጥላሸት ሲቀቡ፤ ተዋህዶ ተዘቅዝቆ ሲንጠለጠል፤ ብዕርህ ሃግ ትላለች ብዬ ሳሰብ እቴ እሷ አብራ ከበሮ ስትደልቅ ሰነባብታ ይሁን አይታወቅም፤ ብቻ ከመሼ ብቅ አለች። እኔማ እህትህ ሰርግና መልሱ፤ ቅልቅሉ አላዳርሳት ብሎ ይሁን ጣል ጣል ያደረገችን በጤና? ብዬ ነበር።
አሁን መልካም ሆነ ዕድሜ ለዘሃበሻ ከወደ ቶረንቶ ብቅ ማለታችሁ አስደሰተኝ። እጅም ነሳን ለጥ ብለን አደግድገን። ግን ደህና ናችሁ? ብርዱና በረዶው እናንተን አልደረሰባችሁም .... ሞቅ ብሏችኋል "የፍቅር ጉዞ መደናቀፍ በደሌ ማዕቀብ እያጣጠምን ነው ... ብሎን ነበር ወጣቱ .... ከፌስ ቡኩ ወደ ዘሀበሻ በተሻጋገረው ቅምሻ ...
እኔ እንኳን ካንተው ከወዳጄ ጋር እንጂ በዛ ዙሪያ ምን መስራት እንዳለብኝ ስለማውቅ ቅጭጭም አይለኝ .... ቡጢ መግጠም አያስፈልግም። ሙያ በልብ ... ይላል የጎሪጥ የምታዬው የጎንደር ሰው ...
ለነገሩ ጎንደር ላይ ሆነ ጎጃም ላይ ስለነበረው የኦሮሞ ወራራስ ምን ይሰማህ ይሆን? የወተር የበደኖ የአርባጉጉ የጉራፈረዳ ጎሽ! ነው ወይንስ ሰቅጠጥ .... መሆን የማንችለውን የፈለገ ጫና ቢፈጠረም ማንነታችን ገላጫችን ነው - ኢትዮጵያዊነት። መወረድ የአባት አይደለም። ተግባባን? .... ጎሳ ከቤተሰብ ቀጥሎ ያለ ያላደገ የማህበረሰብ እስቤ በመሆኑ በግሌ ለእድሌም አላሳዬው። ሁኜም አላወቅም። መሆንም አልችልም። ሌላ የሚያርመጠምጠኝ መጠነ ሰፊ ሀገራዊ ጉዳይ አለብኝ። የሆነ ሆኖ ብዕራችን ጉጉስ ትጋጠም ዘንድ ወደደኩ። ደስ ስለምትለኝ ....
ዘሃበሻ ላይ ከአንተ ጹሑፍ ሥር የተሰጡ አስተያዬቶችን ሳነብ ደግሞ ጎሽ! ሞገደኛው ተብለኃል። ሜጫው አንተን ዘለል አድርጎ ሽልማት ቢጤ ልታገኝ ስበሰባ ላይ መቀመጣቸውን አነበብኩ። ድምጽም ሰጡህ። ለነገሩ ወገኖቼ እውነት ብለዋል። እንዲህ ሁሉንም ፍላጎት በእኩልነት የሚስተናገድ ሚዲያን ነፃ ሊያሰኘው ስለመቻሉ በተግባር መገኘቱ ዘሃበሻ እኔም ምርቃቴ ይድረሳቸው እላለሁ። እኔንስ እኩል አድርገው ባለወግ አድርገውኝ የለ። ይባረኩ። በአንድ አቅጣጫ ብቻ የሚፈስ ወንዝ ውበቱ እንብዛም ነው ... ህግጋትን ካልተላለፈ .... ትውልድን ለመናድ ካልተንጠራራ፤ ለዬት ያሉ አወያይ ሃሳቦች ጉልበት ይሰጣሉ። ቀዳዳም ይሸፍናሉ፤ ያልታዬትን ያስጎበኛሉ። እራስን ያርቃሉ። እንዲህም ያነጋግራሉ ...
አንድ ትውስታ አለችኝ። ልጅ ተክሌ አንተ የኢሳት መደበኛ አዘጋጅ በነበርክበት ጊዜ አብዝቼ አደምጠው የነበረው "እፍታና የእሁድ ወግ" ዛሬ የለሁበትም። ስለምን? አንተ በነበርክ ጊዜ የራስህን ዕይታ ይዘህ ከች ትልና አንተና ሲሳይ ማህል ዳኛው ደረጃ ስትፋተጉ፤ ሃሳብን በሃሳብ ስታፈጩ ትቆዩና ከዛም በሌላ ፕሮግራም ላይ ደግሞ በጋራ ማዕደኛ ስትሆኑ ገነት ነበር ለእኔ ለመንፈሴ። ምክንያቱም የእኔ ሃሳብ የእኔ ነው። እኔ ዬእምፈልገው እንደ አንተ ያለውን ወጣ ያለ የእኔን የማይመስለውን ስለነበር ጓጉቼ እታደም ነበር። የእውነት ውበት ነበረው። አዎን ዛሬ ዛሬ ግን የእኔን ሃሳብ ወይንም ዕይታ ደግሜ ለመስማት መታደሙ አላስፈለገኝም ማለት ቀርተህብኛል። የዛሬው ጹሑፍ ደግሞ ዋው! እራሰህን ያነበበው ሸጋ ነው። ማለፊያ ነው። አጋድመህ ከመጻፍ ግን እኔም ብሆን ብለህ ደፈር ብትል ማጣቀሻ ምሳሌዎችን ተረተረት ነገር ከምትነገረን የጭብጡን ተዋናይ አንተን አድርገኸው ቢሆን ገላጭ፤ ተራኪና ትዕይንታዊ በሆነ ነበር። እንዴት ባመረ ነበር። ካልጎሼ አይጠራም። የጠራ ደግሞ ጤና ነውና .... ከራስ መነሳት ደግሞ ... አብነትነት ነው ....
ከቶ .... ወንድምዬ ብልህ ይሻልኃል ወይንስ ታናሼ .... በሞቴ በሥርጉት ሞት እንዲህ ካለ የአንድ ሀገር ምስረታ ታሪክን ከናደ ጠቀራ ሂደት ጋር ዶር. ኦባንግ ኢትዮጵያን ማነካካትህን አልወደድኩትም። እሙት ወንድምዬ የምር ክፍት ነው ያለኝ። "በኢትዮጵያዊነታችን ያጣነው ነገር ስላለ ብቻ ኢትዮጵያዊነታችን ይሰረዛል ማለት አይደለም"። "ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ" እንዲሉ እንዳይሆን ...። ምን ባደረገ .... ዶር. ኦባንግ እኮ ንጹህ ግን ብልህ ሰው ነው። ተቋማችንም ነው። ሞት ካወጀ ጋር ማዳበለህ ይቀፋል እሺ! ያው የፈረደበት ግንቦት ሰባት በትንሹም በትልቁም ጥርስ መፋቂያህ፤ ማጠቀሻህ፤ ማጣፈጫህ ስለሆነ አሁን ደግሞ አምጥትህ ማህል ላይ ድንቅር አደረከውም። ፍቅሩ ገደለህ አይደል የግንቦት ሰባት?!! .... ከትክት .... መስጠት ነበረበት ነው ማለም ነበረበት ... እሱም እኮ ስደተኛ ነው የማከበርህ። ሥልጣን ኑሮት የነሳው ሲኖር ያን ጊዜ ቢተች .... በቀጠሮ .... ካለ ግንቦት 7 ብዕርህ ውቃቤዋ አይነሳም አይደል?
ከእርእስህ መነሳት ግድ ነው። "የእኛ ነገር የተሸነፈ ርእዮትናሀገር ገፊ ፖለቲካ" የጹሑፍ ሆድ እቃ እንደ አመለከተኝ ከሆነ ኢትዮጵያዊነት ተሸንፎ አያውቅም ለወደፊቱም አይሸነፍም። ሀገረ ኢትዮጵያም በታሪኳ ስታሸንፍ እንጂ ስትሸነፍ ተሰምቶም ታይቶወም አይታወቅም። ጠላቶቿም አይመሰክሩባትም። እውነት እናትዬ ሞገደኛው ዬትኛው ፕላኔት ላይ ይሆን የከተምከው? ይህ የብሄር የምተለውም ፍትኃዊ ሥርዓት ስንገነባ ነው ተጠያቂነቱ .... "የተሸነፈ ርዕዮትናሀገር?!" ይህ ታሪክን የመግደል ዕይታ የጤና ወንድምአለም? እርእሱ አራሱ እኮ ገዳይ ነው። አተጋፋት ሀገርህን ....
"ገፊ" ለሚለውም ከሌላ ዕይታ አንጻር አቅርበኸው ቢሆን ሊያስማማን ይችል ነበር። አቅማችን በመሰብሰብ እረገድ ብትመጣ፤ ወይንም ይህ ሥልጣን በሚሉት ተወዳጅ አዚመኛ ብቅ ብትል ስምምነት በወረደ። ምን የመሰለ ድፎ ዳቦም በተቆረሰ። አንተ ላነሰኸው ነጥብ ግን የተገፋ ነገር አልበረም። በራሱ ጊዜ አጎጠጎጠ፤ በራሱ ጊዜ በቀለ፤ በራሱ ጊዜ ጥፋትን አወጀ፤ በቀለን ዘራ .... ለዛውም ብዙዎቻችን ዝም ብለን ነው እያየን ያለነው። የተማገዱት ጥቂቶች ናቸው ... ፊት ለፊት ወጥተው "ኢትዮጵያዊነት" ሲጠቃ ... ዋቢ የሆኑት። ለነገሩ እንቅልፍ ሊኖረን ባልተገባ ....
ምንድን ነው የምትለን? ምን ሁኑ ነው የምንባለው? ከዛ በላይ ወጣቱ የፖለቲካ ተንታኝ፤ አክቲቢስት፤ የሰብዕዊ መብት ተሟጋች ምን ያልተባለው ነገር አለና? እኔ ከእሱ ይልቅ ጋዜጠኛ ሳዲቅ ቀልቤን ሳብ ያደርገው ነበር። ብቻ ከቁንጮጯችሁ ላይ ተሸክማችሁት ሂዱ ተብለን ነበር የታዘዝነው። ይገርምኃል እኔ እህትህ ሳይሞቀኝ ሳይቀዘቅዘኝ ጠርዝ ላይ ሆኜ እመለክት ነበር። በኋለም በዛ አጣብቂኝ ጥያቄ ከመንበሩ ዝቅ ማለት ሲጀምርም ኖርማል ነበር ለእኔ። ሰው ይወጣል ይወርዳል። በቃ!
ትእግስት አጣን ለምትለው ግን ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ላላ ምን ቆራጣ ጊዜ ያስፈልገዋል ብለህ ነው። ይቅናው። መንገዱንም ጨርቅ ያድርግለት .... ከእኛ ተነጥሎ ህይወቱ አልባብ ባልባብ ሲሆን ይድላው ... አይተናል ኤርትራን ... ሚሊዮን ወጣቶች በርኃ ላይ ሲረግፉና ሲንጋፖር አፍሪካ ቀንድ ላይ ሲገነባ .... ከትከት!
ሌላው ግን ይህን አክቲቢስት የሚባል ሹመት አብዝቼ እታዘበው ነበር። መቼ እንደሚያቆምም እያነፈቀኝ ነው ...የተያዘ የተረዘዘው ሁሉ "አክቲቢስቲ" ሲባል የአውቶብስ ትኬት እንደ መግዛት ነው የቆጠርኩት። እንደ ወያኔ ሹሞች ዶክተሬትነት ..... ሳር ቅጠሉ ሁሉ ሆነ። ለነገሩ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ካለ ከፍተኛ ድግሪ ፍንክች አልልም ብሎ መልዕክት ልኳል አሉ?! ነጋሪትም ጎስሟል ይላሉ። ወይኔ! ሥርጉተ ብጣቂ ምንም የለ ከነፃነት በኋላ አስኮባ ማግኘትሽን እንጃ እያለ መንፈሴ ያጣድፈኛል። አንተ ድነሃል አሉ .... የእውነት ነውን? ቀለሜዋ ሳትሆን አትቀርም ... በፈርንጅኛው ቃለ ምልስህን አዳምጬ ነበር። እኔ ስሜን መጣፉ አልሆነልኝም ....
ለማንኛውም የእኔ እናት ዘረኝነት በሽታ ነው። ጎጠኝነት ዲዲቲ ነው። ተመስጥሮ የተያዘ በሽታ ሲያዳልጥ በራስ ጊዜ ያፈናቅላል። ከእቅፍ .... አፈንጣሪው ንዑድ መንፈስ የማታውቀው እንደሆን ልንገርህ ወንድምዬ ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረው ሚስጢር "ኢትዮጵያዊነት" ነው .... አሁን ደግሞ ከመቼውም በላይ በራሳቸው ቋንቋና የዕምነት ዶክተሪን ተሰልፈው የሚሟገቱለትን አፈራ። ልጆቹን እዬሰበሰበ ነው ... ጎራ በልና በተቃራኒው በኩል ያሉትን ሲቢሊቲና ደብተራ ሩሞችም ሰንበት ላይ ሆነ በአዘቦት ታደምና ልኩን እወቅ። ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል - አሁንም ጎንደሬ ይላል።
የከፋን፤ የኢሊባቡርን፤ የጋሙን፤ የሲዳሞን፤ የባሌን የሀረርን ወጣቶች በተለያዬ ኮርስ ምክንያት በቤተሰብ ደረጃ አውቃቸዋለሁ። ንጹህ ናቸው። በነገራችን ላይ አርሲን አወቀዋለሁ። ሮቤን በሙሉ። የጢቾ የአምኛ የሴሩ የዲክሲስ ቁርጡ ወተቱ ገንፎው ጭኮው ፍቅሩ ስስቱ ናፍቆቱ ከቶም ልክ የማይወጣለት ኢትዮጵያዊነቱ፤ እንግዳ ተቀባይነቱና አክባሪነቱ፤ ወደር የለሽ ናፍቆቴ ነው። አሁን አንተና ብዕርህ ጥብቅና የቆምክለት ዬሜጫም ፖለቲካ ያን ደግ ህዝብ ሊወክል የማይችል፤ በአብሮነትና በጨዋነት የሚኖር ስለሆነ .... ብጣቂ ስጋት የለኝም። ማን ወልቆ እንደሚቀር ፈጣሪ ያወቀዋል። እኔ ስዛውር ለአንድ ሳምንት ሥራ የገባ አንድም ሰው አልነበረም። ፍቅር ነው። ነፍሶቼ ናቸው እሺ!
የፈረደበትን ዲያሰፖራ ለማተራመስ ወያኔ በሙሉ ኃይሉ የሰራበት ዘመቻም እሳት የላሱ የእስልምና የተዋህዶ ኦሮሞዎች ሆኑ የሌላ ብሄረስብ አባላት ሁሉ እጅ እጅ ያላቸውን የጃዋር ዶክተሪን ፊት ለፊት እዬተዋጉት ነው። የምሥራቹ ደግሞ እንደምታወቀው በተዋህዶ ትንሳኤን ያበሰራቸው ቅድስት መግዳላዊት ናት። አሁን ደግሞ ሞገዱ የሴቶች ኃይል በመሆኑ ወዬ! ነው ... እዬገፋህ ከማልፈልገው ነጥብ ጋር አለካለከኝ እግዚሩ ይይልህ። የእኔ አቅጣጫ ፈጽሞ ሌላ ነበር። የሚገርምህ ጆኖሳይድ ሩም ሲከፈት በተረጋጋ ስሜት ነበር የተቀበልኩት። "ኢትዮጵያዊነትን" በሚመለከት ባላቤት የሌለው ስለሆነ በዚህ ዙሪያ ብዙ መስራት እንዳለብን ብቻ መንፈሴን አዘጋጀሁት። አሁን እንዲያውም በራሳቸው ጊዜ ጎርቦ የነበረው እብጠት ፈናዳ፤ የዋሆቹ ደግሞ ወደ ጡታቸው እናታቸው ተመለሱ ደስ አይልም? የምስራቹ ይህ ነው።
ትንሽ ከተረተረት የወጣውን የሰሞናቱን የሃቅ አናት መስማት ያሰኝኃልን? በምስክርነት ትንሽ ልበልለት፤ እንዲህ ሆነልህ .... ታናሼዋ .... "ሞት ለወያኔ" በሚል ፓል ስም የምትታወቀው ዬእስልማና እምነት ተከታይ ብሄረሰቧ ኦሮሞ፤ ሀረር ተወልዳ ያደገች ብርቅዬ ውብ በ15.01.2014 ደብተራ ሩም ላይ እንዲህ አለችን። " እኛ ተሰይፈን ሳናልቅ እናንተ ዘንድ አይደርሱም። አስተውል "እኛ ተሰይፈን ሳናልቅ" እኛን ሳይጨርሱን ከእናንተ ዘንድ ድርሽ አይሉም። ቁምጥና በሽታ በመሆኑ ሀረር ላይም ድውያኑም ሆስፒታሉም አለ" በማለት አብራ ቆመች ከማንነቷ ጋር አርበኝት።
በ26.01.2012 ዛሬ ደግሞ ሲቢሊቲ በአባ መላ ሩም 1000 ታዳሚ ነበር። ቃለ ምልልስም ከዶር ጌታቸው ጋር ነበር። " አጼ ሚኒሊክ ከወገኖቼ ጋር አገናኙን። እኔ የምጠይቀው በእሳቸው ዙሪያ የጀግኖች ሀውልት እንዲሰራ ነው። ከኢትዮጵያዊነታችን አንድ ኢንች ፈቀቅ አንልም።" ድንቅ ውሳኔ! ሌላዋ እህቴም ሳራ አብዱ ትባባለች። እሷም "ጃዋር እኛን አይወክልም። ምን አለ የእስልምና ሊቃናትን አምጥታችሁ ቃለ ምልልስ ብታደርጉ። በኢትዮጵያዊነቴ እኮራለሁ።" ሳርዬ ደግሞ የጉራጌ ብሄረሰብ አባል ናት። ለአምስት ዓመት አውቃት የነበረችው ናፍቆቴ አምርትዬ ደግሞ የሰላሌ አንበሲት "በረት ገልባጭ ጀግና ስትሉ ያሳፍራል። ቀመር ዮሱፍ ወይንም አገሪ ቱሉ ሽፍታ የነበረ በረት ገልባጭ ነው። 90 በመቶው ኦሮሞ እስልማና ነው ሲል ጃዋርን አዳመጥኩት። እኔስ የተዋህዶ ልጂት የት ልጣል ነው?! በሃይማኖቴ ቀልድ የለም። እሰዋለሁ። ለነገሩ የድርጅቱ የኦሮሞ ከፍተኛ መሪዎች እኮ ከ10 ጋሻ መሬት በላይ የነበራቸው አስገባሪዎች ነበሩ። አባቴን ጨምሮ፤ ዛሬ እነ አቶ ሌንጮ ስንት ደም አስፈስሰው ሀገር ሊገቡ ነው። እጅግ ያሳዝናል። መጀመሪያ እኔን ኦሮሞዋን ያሳምኑ። አባል ነበርኩ በድርጀቱ" ሌላው እጅግ ድንቅ ነገር ዲነግዴ መቼም መብራት ነው። ከትናንት ወዲያ በ25.01.2014 ጋዲሳ በሚል ስም የሚጠሩ ፕሮፌሰርና ዳኛ ህይወት ሰጡን ብል ይቀላል። ዛሬ ደግሞ " መምህሮቼ ስሄድ ይነሱልኛል ነበር ያከብሩኛል። በጀርባዬ ሀገሬ ኢትዮጵያ አለችና።" አሉን ዘመናትን በትንግርት ያነገረ ሚስጢር ይሉኃል ይህ ነው። ክቡርነታቸው ደግሞ የጥቁር አንበሳ አንባ ጎሬ ላይ እትብታቸው የተቀበረ ... ናቸው። ይህን ዘለቅ ብለህ ገባ እያልክ ዛቅ። ሥነ ጥበብ ከማህበረሰቡ ጓሮ ይታፈሳል። ምርት ደግሞ ከሃቅ አውድማ!
ማመሳካሪያዎችህን
አብረን ....
ወይኔ!
ይህ
ማጣቀሻ
ከሆነ
"አከራዩ ደግ አማራ
ሴት፤
ለጃዋር
ምግብ
ሰጥታ፤
እሳት
አንድዳ
እያሞቀችዉ፤
ከላዩ
ላይ
ጋቢ
ደርባ
"ለምን እስኪመሽ ቆየህ
አሁን
ከመንገድ
አንድ
ጋላ
ቢያገኝህና
አንገትህን
ቢልሀስ"
አለችው።
የዚህን
ልጅ
ስሜትና
ምላሽ
ለመረዳት
ኦሮሞ
መሆን
አያስፈልግም።
ራስን
በሱ
ቦታ
ማስቀመጥና
ነገሩን
የራስን
ጎራ
ያለስስት
በመተቸት
ፈቃደኝነት
ማሰላሰል
እንጂ።"
"ልክ ጅሁርና ጋይንት፤
ቢቸናና
አንኮበር
እንደምትኖር
አንዲት
አማራ
ኢትዮጵያዊት፤
ይህቺ
ሴት
ክፋት
እንደሌላትና
የንግግሩዋን
ፖለቲካዊ
አንድምታ፤
በዚህ
ልጅ
ቀጣይ
ማንነት
ውስጥ
የሚኖረውንም
ፋይዳ
እንደማታውቅ
አሳምሮ
መገመት
ይቻላል።
ይሄንን
አጋጣሚ
የነገረን
ጃዋር
ግን
የሚለው፤
ይህቺ
የዋህ
ሴት
የኢትዮጵያ
ገዢ
መደብ
አካላት
ያሰራጩትንና
ለገዢ
መሳሪያነት
የተጠቀሙበትን
የተወሰነ
የህብረተሰብ
ክፍልን
ዝቅ
የማድረግ
አመለካከት፤
ሳታውቀው
ከነፍሱዋ
አዋህዳዋለች
ነው።
ስለዚህም፤
በቀጥታ
ይሄንን
የተወሰነ
ብሄርን
ዝቅ
የማድረግ
ባህል
በመፍጠርና
በመቅረጽ
ባትጠየቅም፤
የዚህ
ባህል
በረከት
ተቁዋዳሽ
በመሆንና
አውቃም
ሳታውቅም
ይሄንን
ባህል
እድሜ
በመስጠት
ተሳታፊ
ነች
ሲል
ተከራከረ።
በላይኛው
ጽሁፍ
ላይ
ሰፈርኩትን
የኦባንግን
ገጠመኝ
ጨምረን
ካየነው፤
የጃዋር
መከራከሪያ
ስሜት
ይሰጣል፡"
ወይ ፈጣሪዬ! .... ስሜት ከሰጠህ የጆዋር ዶክተሪን መጠቃለል ምን ችግር አለው። በነፃነት ሀገር ልመና ዬለ ... ፕሮቶኮል ሲናሪዮ ብሎ ነገር የለ ደጅ ጥናት የለ። አማረም ከፋም ፈርጆዋን በውልብልቢት ከማጣቀስ ዋና መልካም ነው .... ለነገሩ ቀዘፋ ታውቃለህን? ኧረ አስነካው ወንድም ጋሼ!
የገረመኝ የአማራር ብሄረሰብ ከቤንሻጉል ሲፈናቀል "አማራ ብሄረሰብ" አይባልም ብለህ ሲሳይን የሞገትክ ጀግና አሁን አንተ የብሄረሰቦች ተቆርቋሪና አስታራቂ ሆነህ ጉብ ስትል ትዝብት ነው። .... እዬረሳኸው ይሆን? የሚመከት ነገር ጠፍቶ ይመስልኃልን? አይመስለህ። ሥልጡን ዕያታ ነው ያሳደገን ኢትዮጵያዊነት። ይህ በነጋ በመሼ ምክንያት እዬቆነጠርክ እያጣጣልክ የምትዘልፈው የተዋህዶ ሃይማኖት ሆነ መስጥረህ በጥርስህ የያዝከው ብሄረሰብ የወያኔን ማንፌስቶ የፈጠረ ስለሆነ ጎራው የት ላይ ሊያሰርፍ እንደሚችል ስለሚታወቅ አይደንቀንም ..... መሬትም ባለቤትም ጥግም አልባ ሆኖ የሚንከረተተው ድሃ .... ወገን። "የደላው ገንፎ ያላምጣል አሉ" ብጣቂ አዘኔታ የለህም እኮ!
"አማራ ብሄረሰብ" ለማለት አንደበትህ አልደፈረም። ከላይ ያነሰኃት ቅን ሴት የሰው ልጅ ከነነፍሱ ገደል ሲጣል በቅርብት የሰማች ናት .... በሙሉ መፈረጀህ ደግሞ እጅግ አሳዛኙ ገጠመኝ ነው። እኔ እኔን አውቀዋለሁ። በድፈረትም የመናገር አቅሙም ሆነ ብቃቱ አለኝ። ያሳደገኝ ማህበረሰም አሳምሮ ኢትዮጵያዊነትን አጠጥቶ በእሱ አቁርቦ ነው። ይህ ነው የጃዋር ዶክተሪን መሰረት .... የአንዲት ሴት ቀንጣ ዕይታ ታሪክና ሀገርን ለመበተን ያስነሳው። አንተም የምታጅበለት? አልተደመጠም? ምን? ሞትን ነው ማደማጥ የነበረብን ወይንስ 18000 ፊርማ ተሰብስቦ "የፍቅር ጉዞ መታገዱ" .... እስኪ የበለጠህን ቴዲ ከአዲስ አድማስ ጋር የሰጠውን ቃለ ምልስ ከልብህ ሆነህ እንደ ለመድከው ምስባክ ገፋ አድርገህ ሂድበት ለቤትህ ቀናተኛ ነህ ብዬ ነው የማስበው። የትውልዱ መንፈስ ተነግሮኃል። "እግዚአብሄር በአንድም መንገድ በሌላም ይነገራል ሰው ግን አያስተውለውም" ይላል አካል የሌለው የመዳህኒዓለም አገልጋይ ቃለ ወንጌል። ከአንተ ያነሰው ቴዲ ዘመኑን - የሚመራን ትእዛዝ ከአምላኩ ተላከለት። ለእኛ አቀበለን .... ካበቀልከው። የዕድሜ አቻውም ወጣቱ ጃዋር ካደመጠው ድህነቱ ከዛ ላይ አለለት .... ቂም በቀል ቋሳ የሌለበት የተረገጋ ንዑድ መንፈስ ....
"ወዳጄ ገረሱ ቱፋም፤ እንዲሁ ልጅ ሆኖ ሳለ፤ ጾም መሆኑን ረሳና፤ ወተት ጠጣ። እናቱ ወደንስሀ አባታቸው ላኩት። ቄሱ ቃል በቃል ምን ብለው እንደመለሱለትና ልቡን እንዳደሙት የነገረኝን በደንብ አላስታውሰውም። ብቻ፤ "ኤድያ ደግሞ፤ የጋላ ጹዋሚ ብሎ ነገር የለም" ብለው መለሱለት። "ለጋላ ንስሀ አባት ዲያቆን መች አነሰው" አይነት የሚለውን፤ የተለመደውን ክብረ-ነክ ተረት የሚያጠናክርና የሚያናንቅ መልስ ነው። በወቅቱ ገረሱ የሱ ጣፋት መስሎት ነበር። ነፍስ እያወቀ ሲመጣ ግን የሱ ጥፋት ሳይሆን ልክ እንደጃዋር ቀላቢ፤ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ፤ በቄሱ ውስጥ የተተከለውን የሱን ብሄር ዝቅ የሚያደርግ ገዢው መደብ የፈጠረው ንቀትና ጥላቻ ተገለጸለት። ከአመታት በሁዋላ፤ እነሆ በገረሱ ነፍስ ውስጥ አብሮ የሚኖርና ዘወትር ቄሱ ስለወጡበት ህብረተሰብ ሲያስብና እኛ ጋር ክርክር በገጠመ ቁጥር ትዝ የሚለው መርዝ አጋጣሚ ሆነ። እንደውም ኢትዮጵያ ስትባል፤ የኚህን ቄስ ጋቢ የደረበች የአማሮች ፈጠራ መስላ ታየችው።ጉርሶ አይደለም አንተን የጎረበጠህ" ኢትዮጵያ ስትባል የኚህ ቄስ ጋቢ የደረበች የአማሮች ፈጠራ መስላ ታዬው"
ሎቱ ስብኃት! ጉርሶ አይደለም አንተን የጎረበጠህ" ኢትዮጵያ ስትባል የኚህ ቄስ ጋቢ የደረበች የአማሮች ፈጠራ መስላ ታዬው" እግዚአብሄር ይቅር ይበልህ። ለምን እራስህን ማወረድ አስፈለገህ? ማንነትህ እኮ አለ "ኢትዮጵያ" ከምትባል ሀገር። ደፈጠጥከው። ሃዘን ቢጤ እኮ ፈለሰበት .... እናትዬ .... አቤት አቤት ማረን!
.... መጀመሪያ
አፍሪካዊ ወይስ
ኢትዮጵያዊ?
"ባለፈው ሰሞን፤ አልጀዚራ ላይ በቀጥታ ስርጭት ይመስለኛል፤ ጃዋር ፖለቲካዊ አጣብቂኝ ውስጥ የሚከተውን ጥያቄ ተጠየቀ። "መጀመሪያ ኦሮሞ ነህ፤ ኢትዮጵዊ?" የሚል። የሚቀጥለው ምሳሌ መቶ በመቶ ላይመሳሰል ይችላል። የተወሰነ መመሳሰል ግን አለው። አንድ ሰላሳ አመት ካናዳ ወይም አሜሪካ ውስጥ የኖረ ኢትዮጵያ፤ ወይንም እነዚህ አገር ውስጥ የተወለደ ናይጄሪዊ ይህንን ጥያቄ ቢጠየቅና፤ መጀመሪያ ናይጄሪያዊ ነኝ ብሎ ቢናገር፤ አሜሪካኖችን ወይንም ካናዳዎችን የሚያስቆጣ አይመስለኝም። ጃዋር ከኢትዮጵ በፊት መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ ብሎ ሲናገር ግን ብዙዎች አኮረፉ። ንትርክ ተጀመረ። የነቁና የበቁ የሚመስሉ የአንድነት አቀንቃኞች ራሱ ተቆጡ። አሁን በእመብርሀን ይሄ ምኑ ያበሳጫል? በዚህ መደንገጥም መቆጣትም የለብንም። ማድረግ ካለብን መጠየቅ ብቻ ነው። ችግሩ፤ እንድንሸመድድ እንጂ፤ እንድንጠይቅ በሚያበረታታ ባህል ውስጥ አላደግንምና፤ ከመጠየቅ ይልቅ፤ ልጁን ወደመዘልዘሉ ዘለልን።"
አንደኛ፤ ከአገሬ በፊት ብሄሬን ነኝ የሚለው መልስ እንደየአመለካከታችን ትክክል ሊሆን ይችላል። በርግጥም ሰው ከአገሩ በፊት ብሄሩን ነው። አንድ ኢትዮጵያዊ መጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ነህ አፍሪካዊ ቢባልና መጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ ቢመልስ፤ ምንም ብዙ ቁጣ የሚቀሰቅስ አይመስለኝም።ጥምር ዜግነት የሚሉትን ጽንሰሀሳብም ማስታወስ አይጎዳም። ኢትዮጵያዊ መሆንም ሙሉ በሙሉ የስራችንና የምርጫችን ውጤት ሳይሆን፤ የትውልድና የሕግ ጉዳይ ነው።"
"ከሰደበኝ መልሶ የነገረኝ እንዳልባል እንጂ፤" አልከን ነገርከን እናመሰግንኃለን - ። ይህን ምሳሌ ዳር ዳር ከምትለው እኔ ብሆን ብለህ እንቅጩን ለምን አትነግረንም ነበር?! በብዕርህ ያለን ፍቅር እርሙን አውጥቶ ቦታ ፍለጋ ሊዝ ይገዛ ነበር። እርፍ ባልንም ነበር። እንዲህ በሺህ ምሳሌ ድርድር ከምታባካነን .... አናሳዝንህም ከቶ? ... አንተም ወቅተህን፤ ወያኔም ቀጥቅጦን፤ ... ዘረኛውም ደንፍቶብን - ዝቶብን - ቁምጥናችን ታቅፈን። ፈረደብን ---- በህግ አምላክ!
".... ነፍስ እንደዜግነት በህግ አትገደድም። ነፍስ ዜግነቱዋን ወይም ማንነትዋን ትመርጣለች እንጂ። ነፍሱ ማንነትዋን መረጠች። የኛ ስራ መሆን ያለበት፤ መናደድ ወይም ማበድ ሳይሆን፤" ማን ነው የተናደደው? ማን ነውስ ያአበደው? ሀቅ ላይ ተሁኖ ... ንዴትም ማበድም የለም። በተከታታይ የወጡትን የኔን ጹሑፎች ስለማንነት አንብባቸው። እንኳንም ሩሙን ከፈቱት። ምን ያህል ምርት እንዳታፈሰ ጥንግ ገበሬዎች የተግባር ጀግኖች ያወቁታል። ይልቅ ያበደ ካለ አንተ የምታውቀው የቆምክለት ስሜትን አስረህ አስጠምቀው አንተው በነካ አፍህ .... " ኢትዮጵያዊነት" የተረጋጋገ መንፈስ የረበበት ማንነት ነው። እሺ ወንድም ጋሼ! ተገፈቶ የማይገፋ ተንቆ የማይንቅ ገናና ተፈሪ ማንነት!
"እነዚህ ወጣቶችም ሆኑ የፖለቲካ ንስሀ አባቶቻቸው፤ በዚህ በአልጀዚራ ላይ የሰማነውን አይነት፤ ኢትዮጵዊነትን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ፤ ለኛ ለመቀበል የሚያስቸግረን ንግግር ሲናገሩ፤ የቆሰለውና እንዲህ ወዳለው ስሜት ውስጥ የሰነቀራቸውን ፖለቲካዊ ሕመም በማከም ፈንታ፤ እንደጠላት የሚፈርጅ አካሄዳችንና ራሳችንን የኢትዮጵያ አንድነት ጋሻዣግሬዎች አድርጎ የመሾም ባህላችንን ነው፤ እነዚህን ሰዎች ወደጽንፈንነት የሚመራቸው። ያ ደግሞ ለኛም ለኢትዮጵያም አይበጅም። በዚህ ረገድ ይሄን ያህል አመት በኢህአዴግ መበለጣችን ሁሌም ይገርመኛል። ምክንያቱም፤ ኢህአዴግ ለነጃዋር፤ የአንድነቱ ሀይል ለመቀበል የሚያዳግተውን፤ ኦሮሚያ የሚባል ክልል/ካርታ፤ ሙሉ ነጻነት ባይኖረውም በራሱ ቁዋንቁዋ የሚተዳደር መንግስት ሰጥቶዋቸዋልና። ስለዚህ ከአንድነት ሀይሉ ውግዘት ጋር ሲወዳደር ብቻ ሳይሆን፤ ራሱን ችሎም፤ ኢህአዴግ ለብሄር ፖለቲከኞች የሰጠው ፖለቲካዊ ገጸ-በረከት፤ ልብ የሚማርክ ነው።"
ለነገሩ ባለፈው "ወያኔ ቀማን ሰልፋችን" አልከን ዛሬ ደግሞ ወያኔ በለጠችሁ ትለናለህ .... ሀገር በማፈረስ፤ በመሸጥ በመለወጥ፤ ሰው በማጨረስ ጎሳና ጎሳ በማዋጋት፤ ሃይማኖት ሃይማኖትን በማጋጨት፤ በማፈን በመግደል በማሰረ አዎን በረኃብ በመቅጣት። ይበልጠናል። እኛ ስለ አብሮነት ስለ አንድነት ስለ ፍቅር ስለ ነፃነት ነው የሚያንገግበን ... ከቶረንቶ ሽልማት ቢጤ ላክ አድርግለት ለሙጃው ወያኔ ... ማንነትህን ለመቀማት እዬተጋለህ ነው።
"አማሮችና ትግሬዎች እየተፈራረቁ ይህቺን አገር መርተዋል። አሁን ደግሞ እኛ እንምራ ነው ነገሩ። በትግሬ ታኮ ወይንም በአማራ ጥላ ስር ሳይሆን፤ በራሳችን መታወቂያ። አገሪቱን መምራት ካልቻልንም፤ ቢያንስ የራሳችንን እጣ ፈንታ እንወስን ነው። የኛ ምላሽ .... "
እንዴት ከት ብዬ እንደሳቅኩኝ። ለመሆኑ መቼ ነው አማራ ብቻ ሀገር መርቶ የሚያውቀው? የትኛው ዘመን ላይ ነው ያለኸው? "ወያኔን" አዎን እያዬን ነው .... ይበቃኝ .... ናፍቆቱ ሳያባትለኝ ከች በልልኝና ምን አልባት ዳግም እንፋለም ይሆናል። .... በናፍቆት ይጠበቃል ቀጣዩ ዘላፈህ ደግሞ ... "ችኮ" "ማነው ምንትስ" አለ ጋሼ ጸጋዬ "ማመናጨቅቅ" ቅብጥርስ የምትለው ፖለቲካና ፖለቲከኞችን፤ .... ለነገሩ ... እስኪ ወኔው ካለህ ዘሀበሻን ጠይቃቸው ስጡት እላቸዋለሁ ኢሜሌንና ዲቤት ማደረግ እንችላለን። አንተ ሙሑር ነህ እኔ ግን መሃይም ...... ደግመህ አንበበው። ጽንሰ ሃሳቡን ብቻ ተከተሎ አጠቃላይ እይታ ማቅረቡ ተመራጭ ነው .... ወደ ቀድሞዋ ውበት መልሳት ብእርህን በፈጠረህ። እኔ ለቀለማም ብዕር አብዝቼ ስስታም ነኝና።
ውዶቼ ይህ ኮበሌ እኮ አደከመን። በሉ ለነበረን መልካም የብዕር የጉጉሥ ትዕይንት በጎውን ሁሉ ተመኘሁላችሁ። መንፈሳችሁን ስለሸላማችሁኝ ወደድኳችሁ። አሁን ደግሞ በተክሌ ብዕር በነካ እጅ የተክሌ ደጋፊውች ውቁኝ። ይመቻችሁ ....
ልቦና ይስጠን። አሜን! ማስተዋልን እንደ ሰጠን እንጠቀምበት ዘንድ አዕምሯችን አምላካችን ያብራ። አሜን!
ኢትዮጵያዊነቴን የሰጠኝ አምላክ ክብሩ ይስፋ! ማህተም አለበት - የጸጋዬ ድህረ ገጽና ራዲዮ!
እግዚአብሄር ይስጥልኝ!
·
https://ethiopiazare.com/amharic/articles/opinion/3300-semotegnaw-by-sergute-selase
ሙርቅርቅ (ሥርጉተ – ሥላሴ)
December 19, 2017 Derege Negash - ደረጀ ነጋሽ
ለመሆኑ የአንድ ሀገራዊ የፖለቲካ ድርጅት ስብሰባ ሂደት አፈጻጸም፤
አካሄድ እና አመራር መርህ ወይንስ ሽምግልና እና ገላጋይ?
ከሥርጉተ – ሥላሴ 19.12.2017 (ከጭምቷ – ሲዊዘርላንድ)
„ሰነፍ ልጅ ለአባቱ ፀፀት ነው፣ ለወለደችውም ምሬት ነው።“ (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፲፯ ቁጥር ፳፭)
የትግራይ ሥርዕዎ መንግሥት የኖረበት የጫካ ተመክሮውን እንደ ተሸከመ አሁንም በፍጥጫ ተወጥሯል። የሚገርመው እጅግም የሚደንቀው ነገር አንድን የፖለቲካ ድርጅት የሚመራው መርህ መሆን ሲገባው አይሰማ የለ ሽምግልና ሆኗል። ዬትኛውም ሀገር ፓርቲ ነው በሶሻሊስቱም ይሁን በካፒታሊስቱ ዓለም በሽምግልና የሚራው? ተስምቶ የማይታወቅ የተሙረቀረቀ ነገር እኮ ነው እዬተደመጠ ያለው። በእውነቱ የታጋሩ ቤተኞች ሊሸማቀቁበት ይገባል። ይሄ በጀርባ ሆነው ቀጥል የሚሉትን ነገር የታጋሩ ሊቃናት ማቆም አለባቸው። ምክንያቱም ከዚህ በላይ መውረድም መዋረድም የለም። ከዚህ በላይ መዝገጥም – መዛገጥም የለም። ከዚህ በላይ በሃሳብ ድህነት መጨቅዬትም – ማጨቅዬትም የለም።
ለአንድ የፖለቲካ ድርጅት በግንባርም ሆነ በህብረት መርህ አለው፤ ሲሰባሰብ ወይንም ሲደራጅ። ከተመረጡት አካላት ውጪ፤ ከሥርዓት ውጪ በሆነ ሁኔታ ሌላ ተጨማሪ አካል ሊገባ አይፈቀደለትም። በፍጹም! በፍጹም! ፍጹም! ይህ እኮ የእድር ማህበር አይደለም። ብሄራዊ ጉዳይ እኮ ነው። ብሄራዊ ጉዳይ ብቻም አይደለም አህጉራዊም ነው። የአፍሪካ ህብረት ያለባት ሀገር እኮ ናት ኢትዮጵያ። ሌላም ዓለም አቀፍ ዕውቅናቸው የተጠበቁ አካላት ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ። ይህም ማለት በኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግሥታዊ አካል (በትግራይ ሥርዕዎ መንግሥት) ሥር የሚመሩ ማህበራዊ፤ ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ የውጭ ግንኙነቱን፤ ሀገራዊ ደህንነቱን ሁሉ ከአህጉራዊ እና ከዐለምአቀፋዊ ሁነቶች ጋር በጥብቅ የተያያዙ ናቸው። ይህን ሃላፊነት የተሸከመ አካል እንደ ጸበለ ጻዲቅ አንተም እንዳትቀር ምግብ ታሳልፍልኛለህ፤ አንቺም መጥተሺ ትንሽ እንግዳ ታስተናግጂልኛለሽ አይነት እኮ ነው እዬታዬ ያለው ጉድ። የእቃ እቃ የልጆች ጨዋታ – ጥሙርሙር።
አንድ የፖለቲካ ድርጅት መተዳደሪያው መርህ ብቻ ነው። በፍጹም ሁኔታ ለደቂቃም ሌላ ተጨማሪ ተሳታፊ እንዲገባ መፈቀድ የለበትም። በዬትኛው ህግ? በዬትኛው መርህ? እንዲህ መላቅጡ ያጣ ውልቅልቁ የወጣ ጉድን ተሸክሞ ነው የኢትዮጵያ ህዝብ 27 ዓመት የኖረው። ይሄን እንኳን የማያውቅ፤ መርህ ለመከተል የማይፈቅድ፤ ባስነጠሰው ቁጥር ከሥርዓት ውጪ በመሆን መደገፊያ፤ ምርኩዝ የሚፈልግ ሰንበሌጥ አሽኮኮ አድርጎ መኖር እልህ ያለወለደው የኢትዮጵያ ዘመነ ምጥ ነው። እጅግ ያሳዝናል።
- ትንሽ ስለ አጀንዳ።
በቅድሚያ አጀንዳዎች በሰብሳቢውም ወይንም በጸሐፊው በንባብ ይቀርባል።
ምሳሌ አጀንዳ አንድ „መኖር“
አጀንዳ ሁለት „መተንፈስ“
አጀንዳ ሦስት „ማቀሰት“
አጀንዳ አራት „ቃ“ ማለት
አጀንዳ አምስት „ጭካኔ“ ሊሆኑ ይችላሉ።
ስበሰባው ሁልጊዜ ቃለ ጉባኤ ያዥ ይኖረዋል። ከዚህ በኋዋላ ስለ መጀመሪያው አጀንዳ „ስለ መኖር“ ሰብሳቢው ትንሽ ማብራሪያ ይሰጡና አጀንዳውን የሚደግፍ ሃሳብ እንዳለ ይጠይቃሉ። አጀንዳ አንድ „ስለመኖር“ ከተሳታፊዎች አንዱ አስፈላጊነቱን ይገልጻል። ከዚህ ቀጥሎ „መኖር“ አስፈላጊ አይደለም የሚል ካለ ሃሳቡን እንዲያቀርብ ይጠየቃል። ሌላው ደግሞ „መኖር“ አያስፈልግም ሊል ይችላል። በሁለቱም የልዩነት ሃሳቦች ድምጽ ይሰጣል። ድምጽ ሲሰጥ ደጋፊ፤ ተቃዋሚ እና ድምጸ ተዕቅቦ ሊኖር ይችላል። አሸናፊው ሃሳብ „መንኖር ቁጥር አንድ እንደ አጀንዳ ይያዘ ከሆነ፤ ቁጥር አንድ አጀንዳ „መኖር“ ሆኖ ይመዘገባል። ሁለተኛው አጀንዳ „ስለመተንፈስ“ ሊሆን ይችላል። በተመሳሳይ ሂደት ይከናወናል። እንዲህ እያለ አጀንዳዎች ሁሉ የሚጸድቁት ይጸድቃሉ የሚወድቁት ይወድቃሉ።
- የጸደቁት
አጀንዳ አንድ „መኖር“
አጀንዳ ሁለት „መተንፈስ“
አጀንዳ ሦስት „ማቀሰት“
አጀንዳ አራት „ቃ ማለት“
- የወደቀው
„ጭካኔ“
ሁሎችም በድጋሚ የጸደቁትና ያልጸደቁት እስከ አገኙት ድምጽ ድረስ ለተሳታፊዎች በንባብ በድጋሚ ይቀርባሉ።
- የሰብሳቢው ሚና።
ስብሰባውን በሰብሳቢነት መምርት።
እኩል ድምጽ ከመጣ ድምጽ መስጠት። ሰብሳቢው የሚሰጠው ድምጽ ወሳኝ ይሆናል።
- የውይይት ክ/ጊዜ
ከአጀንዳ አንድ ጀምሮ ቃለ ጉባኤ እዬተያዘ በጥልቀት በአራቱም አጀንዳዎች ላይ ውይይት ይካሄዳል። ከሃሳብ ፍጭት በኋዋላም፤ በእያንዳንዱ አጀንዳ ላይ የድጋፍ – የተቃውሞ – የተዕቅቦ ሂደት ይከናዋናል። በድምጽ ብልጫ ያሸናፈው ሃሳብ ውሳኔ ይሆናል። በቃ በዚህ ሂደት ማሳሰቢያ ከኖረ ሁልጊዜ ቅድሚያ ይሰጣል። ከውሳኔው በኋዋላ ሁሉም ይፍርማበታል፤ ይጸድቃል። ከጸደቀበት ሰአት ጀምሮ ተፈጻሚ ይሆናል። ይሄንን አንድ የገበሬ መንደር ሥ/አ /ኮሜቴ ይሠራዋል። አንድ የሀገር ጠ/ሚር ለዛውም በማስተር ደረጃ የተመረቁ፤ በበርካታ የሥራ ሃላፊነት የሠሩ፣ ይህን በሥርዓቱ መፈጸም ሳይችሉ ቀርተው እንደ ሮቦት የኤሌትሪክ ገመድ ይቀጠልልኝ ሲሉ መስማት ማሰፍር ብቻ ሳይሆን እጅግ ያስደነግጣል። ሰብሳቢ እኮ መርህን ማስፈጸም ነው ሥራው። ይሄ የድንጋይ ፈለጣ ሥራ አይደለም። ወይንም የጦር ሜዳ ውሎ አይደለም። ደንብን ሥርዓትን ተከትሎ መምራት። ለነገሩ ተጽፎ የተሰጣቸውን እንኳን አስተካክለው ማንበብ ያልቻሉ በምን ወርድና ቁምት ይህን ሃላፊነትን ሊወጡ ይችላሉ። ገበርዲን አይችለው የለ በኪነ ጥበቡ ነው ያሉት። እኔ እኮ የማይችሉ ከሆነ ከክብር ጋር ስለምን አልችልም ብለው አይለቁም። የእውነት አሁን በቀደም ለት „የሀዘን መግለጫ“ ሲያነቡ፤ በጀርባቸው ጨንገር የያዘ ሰው ያለ እስኪመስል ድረስ እንደዛ ተወጥረው፤ በፍርሃት ቆፈን ተውጠው፤ የተተኮሰባት ሚዲያቋ መስለው፤ እዬፈሩ – እየተቡ – እያማተቡ ነበር ያነበቡት። ሲያነቡም ይሁን ሲናገሩ ከውስጣቸው፤ ከነፍሳቸው ይሾልካሉ። የአትኩሮት ችግር አለባቸው። የተሰባሰበ ስሜት የላቸውም። የተቆራረጠ ነው። እርግጥ ካለፈው የሠመራ ንግግር የተፈጠረውን የንባብ ግድፈትን ለማስተካከል ባይቻልም እረጋ ብለው ለማንበብ ሞክረዋል። ቢሞክሩም ግን የማይሆን ነገር አልሆነም። በፍጹም ሁኔታ ለዚህ የሃላፊነት ደረጃ አልተሰጣቸውም። ከመምህሩ ፊት እንደሚቀጣ ተማሪ የሆድ ዕቃቸው እዬተጯጯኽ ነበር ያቀረቡት። ደግሞ ስለምን ብዙ ገጻት የፈጁ ዲስኩሮችን ጽፈው እንደሚሰጧቸው አይገባኝም። ቢበዛ ሦስት ደቂቃ በቂያቸው ነው። አይችሉማ ማንበብ። እኔ እንዲያውም አሳቸው አፋቸው እዬተንቀሳቀሰ በሰለጠነው ነገር ሌላ ሰው ቢያነበው ይሻል ይመስለኛል። የሆነ ሆኖ ምን አለ ከነክብራቸው ቢለቁ፤ ሞዕ ኢብራሂም ፋውንዴሽንም ይሸልማቸዋል። ራስን ማወቅ ከሁሉ የሚበልጥ ዕወቀት ነው። ካለ መክሊቱ አይሆንም። ያልተሳካለት ሰው ስለ አለመሳካቱ ማመን፤ ያመነውን መቀበል፤ የተቀበለውን መፈጸም አለበት።
የአንድ ሀገር መሪ ስብሰባ መምራት አቅቶት ድርጅቱን በሽምግልና እና በምልጃ እንዲመራ ሲፈቅድ መቼም ጠ/ሚር ሃለማርያም ደስአለኝ በምድር የመጀመሪያው መሁር ናቸው። የእውነት። ትዳር የሚባለው ነገርስ ምንድነው? የትዳር አጋራቸው ይህን እንደ ክብር አይተውት ይሆን? እንዴት ለዚህ ሀገራዊ ገማና የትዳር አጋራቸው ራሳቸው መቁረጥ ተሳናቸው? እውነት የጠ/ ሚር ሃይለማርያም ትዳር፤ ቤተሰቦች ሁሉ መክረው ሊወስኑበት ይገባል። የሀገር ገመና የአስፓልት ላይ ቄጠማ ሆኖ ዜጋው ቅስሙ ሲሰበር ጉሮ ወሸባዬ የሚያሰኝ አይደለም። በዬደቂቃው የሚደመጠው ሞቱ፤ ጭንቀቱ፤ ስጋቱ አልበቃ ብሎ አንድ ስብሰባን መምራት እንኳን አልቻሉም? ምን ያደርጋሉ መምራት ካልቻሉ? የማንን ጎፈሬ ሊያበጥሩ ነው የተቀመጡት? ይህ በታሪክም ለቤተሰብም፤ እንደ ሀገር ልጅነት እጅግ ያሸማቅቃል። ሸሽጉኝም ያስብላል። ከሃፍረትም በላይ ነው። መሞት በስንት ጣዕሙ።
ባለፈው የመስቀል በዓል በ2010 ዓ.ም አንድ የተጋሩ አንጋፋ ጋዜጠኛ ከነባለቤታቸው የክብር እንግዳ ነበሩ። እና በልበ ሙሉነት „ከኢህአድግ የተሻለ ድርጅት የለም እያሉ“ ሲፎክሩ፤ እጅግም ሲመጻደቁ አዳምጬ ነበር። እንዲያውም በቀጣዩ ሂደት በፖለቲካ ሊሳተፉ እንደሚያስቡ ሰምቻለሁ። የሚፎከርበት፤ የሚቅራራበት ለዚህ ነውን ያሰኛል። ይህስ ከሆነ ምን ማቄን ጨርቄን ያሰኛል። መርህ እንጂ ሽምግልናን አንድ የፖለቲካ ድርጅት በዬትኛውም ዘመን፤ በዬትኛው ሀገርም፤ በዬትኛው ታሪክ መርቶት አያውቅም። የአስተሳሰብ ድህንት እኮ አለው ዓይነት። ቁልጭ ያለ የክህሎት፤ የልምድ፤ የአምክንዮ አቅም ድርቀት ነው። አሁን ያለው ሁኔታ እኮ እንኳንስ ኢትዮጵያን ወረዳ ለማስተዳደር የማይችል ሁኔታ እኮ ነው የተከሰተው። ሙርቅርቅ።
ምን ሲባል ከተመራጮች ሌላ ተጨማሪ ሃላፊነት የሌለው ሰው ገብቶ የመወያያ አጀንዳውን የሀገር ሚስጢር የመስማት ሆነ፤ ሃሳብ የማቅረብ ሆነ፤ በድምጽ የመሳተፍ ዕድል ይሰጠዋል። ሚዲያም አይፈቀደም። ይሄ እኮ የሀገር ጉዳይ እንጂ የቁቤ፤ የእድር፤ የሰንበቴ፤ የሰርግ ወይንም የልደት ዝግጅት ሴሪሞኒያዊ ጉዳይ አይደለም። በህሊናቸው እራሳቸውን ለጠ/ሚር ማእረግ ያጩት ዶር ደብረጽዮን ገብረሚኬኤል ሆኑ አሁን ያሉት ጠ/ሚር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ አቅማቸው አይፈቅድም፤ አሁን ያለውን ይህን ውስብሰብ ሁኔታ መልክ ለማስያዝ፤ በችግር ሰምጠዋል። ስለዚህም ነው ምርኩዝ የፈለጉት። ሺህ ምርኩዝ ቢደረደር ማዕበሉን አያግደውም። ግዝፈቱ ሊታያቸው አልቻለም። ከምናስበው በላይ መጪው ጊዜ በማያዳግም መፍትሄ መንገዱ ካልተቀዬሰ ወዮ ነው።
- „ከሞቱ አሟሟቱ“
አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ኢትዮጵያን ሊታደግ የሚችለው የአቅም ክህሎት ብቻ እንጂ የጫካ ተመክሮ፤ ወይንም የአራዊትነት ተግባር ወይንም የውስኪ ማህበር ሴራ አይደለም። አቅም እና ጡንቻ ተፋጠዋል። ችግሩ ደግሞ በዬሰከንዱ መንፈስን ወጥሮታል። በዚህ ማህል አንድ ሁኔታ ቢፈጠር ሁሉ ነገር የዶግ አመድ ይሆናል። ቢያንስ የትግራይ ሥርዕዎ መንግሥት ሲኖር ባያምርበት ሲሞት እንኳን አምሮበት ለመሰናበት ስለምን አይቆርጥም። አዬሩ፤ ንፋሱ እራሱ ቆርጧል – ተቆጥቷልም – ተበሳጭቷል። አስፍስፏል ግፍ የበላው መንፈስ ሊውጠው አውሬውን ተሰናድቷል። ቢያንስ ራስን ማዳን እንዴት ያቅታል? ደጋፊን ማዳን እንዴት ያቅታል? የእውነት ነው እኔ እምናገረው ግጽና ቀጥተኛ ነኝ። „ከሞቱ አሟሟቱ“ ይባላል። ለዚህ ነው አባቶቻችን „አሟሟቴን አብጀው“ የሚሉት። ቢያንስ አሟሟትን ማሳመር፤ አወዳደቅን ማሳማር፤ በክብር መልቀቅ ብልህነትም አስተዋይነትም ነው። ሽንፈት በፍጹም አይደለም። ክብር ነው አቅም አልመጥን ሲል አልቻልነውም ብሎ መልቀቅ የሚያሰመሰግን ነው። ይቅርታንም የሚያሰጥ። ኢትዮጵያ የይቅርታ መንበር ናት። ይህ ካልሆነ ግን በዚህ የአያያዝ ድክመት ሚሊዮኖች ሰለባ ይሆናሉ። የሚብሰውም ለትግራይ ልጆች ነው። አዎን እውነቱ ይሄ ነው። ከለላ፤ ማቆያ፤ ማኖሪያ የሚሆነው መፍትሄውን ቆርጦ ከሥልጣን መልቀቅ። እርግጥ ነው ሥልጣን ይቀራል ግን ህዝብ ይተርፋል። ሥልጣን ይቀራል ግን የወል ዕሴት ይተርፋል። ሥልጣን ይቀራል ግን አብሮነት ይተርፋል። ሥልጣን ይቀራል የህዝብ ጥሪት ይተረፋል። ሥልጣን ይቀራል የህፃነት ሳቅ ይተርፋል። ታሪክ እሰከ ፈቀደ ድረስ ተሰብሮም፤ አንክሶም እስከ አሁን ድረስ የትግራይ ሥርዕዎ መንግሥት ቆይቷል። አሁን ግን በምንም መደለያ እና ጥገና ምኞቱን ሊያቆይ የሚችል ምንም የመንፈስ ቋሚ ጥሪት ልቅላቂ በእጁ የለም። የሁሉም ኢትዮጵያዊ ልብ ከሸፈተ ቆይቷል። እንደ እሱ/ እሷ የሸፈተች ቀን ነው የሚጠብቀው/ የምትጠብቀው። ዘንበል ካለ አበቃ ነኮተ። የሸፈተ ልብ በከረንቡላ ከብለሌ አይመለስም። „ቁርጥ ያጠግባል“ እንዲሉ መቁረጥ – መወሰን – በፈቃድ ለሚችል አቅምን በሰላም ማስረከብ። ድምጹ ያልተሰማ፤ ሰቀቀን ያማይደመጥበት ሰላማዊ ሽግግር ማድረግ። አንድ ፋፍሪካ ውስጥ አንዱ ምርት ሌላውን ሲተካ ሥርዓቱን ተከትሎ የፊቱንም የኋዋላውንም ሳያውክ ነው። ልክ እንደዛ ያለ ሥልጡን፤ ሃላፊነት የሚሰማው፤ ትውልድን የሚያተረፍ ብስጩ ያልሆነ ርክክብ ያስፈልጋል። „ልብ ያለው ሸብ“ ይላል ጎንደሬ።
- አቅም ማወቅ ብቻ ያድናል።
እኔ እኮ የሚገርመኝ ፈጣሪ አምላክ ኢትዮጵያን እንዴት ቢወዳት ነው በዚህ እጅግ ሥርዓት ባጣ፤ በደረቀ፤ በቆረፈደ አስተሳሰብ እና አመራር ህልውናዋ መኖሩ የሚገርም፤ የሚደንቅ የሰማይ ታምር ነው። ትንግርት ነው። ኢትዮጵያ አቅም ያለው ሰው እያላት ሳታጣ ስትነጣ ደግሞ እጅግ ያሳዝናል። እንኳንስ ለኢትዮጵያ ለአፍሪካ እጅግ ባጠረ ጊዜ በተመደቡበት በሳይንስና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ውጤት ያለው የመንፈስ ዲታዎች ያላት ሀገር እኮ ናት። እነዚህን ሊቃናት ለመምራት ለዛውም ከሥልጡኑ ዘመን ጋር በአቻነት ለመራመድ ከጫካ ተመክሮ ከዬት የተሻለ የአያያዝ ጥበብ ይምጣል። አይዘረፍ አንደ ገንዘብ። አይሰረቅ አንደ ቅርስ፤ አይወረር እንደ መሬት። የት ይምጣ? በአራጣም፣ በወለድ አገደም አይቻል ነገር። በሎቢ ሥራም አይሆን ነገር። የመፍትሄው መናህሪያ አሁን ባለው እጅግ ጠባብ ዕድል አቅምን ማወቅ ብቻ ነው ወያኔ ሃርነት ትግራይን ከጉድ የሚያድነው። እኔ ሳዬው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ፍርፋሪ፤ ነፍስ የሚያሰነበት የህሊና ብቃት ነገር የለውም። የተሟጠጠ ነው ለዛውም ሽሁራር የበላው። መርህ እያለ የፓርቲ አመራር በሽምግልና፤ በአማላጅ ሆኖም አያወቅም። የአንድ የፖለቲካ ሥርዓት ላዕላይ መዋቅር አማራር ወንዝ ወርዶ በዬተራ እውሃ እየቀዳ ማደል አይነት እኮ ነው የሆነው። የማይመለከታቸውን ሰዎች አንደ ሰንበቴ ሰብስቦ ዝክሬን ቅመሱ ይላል ወያኔ ሃርነት ትግራይ። ጥምልምል።
የሀገር ሚስጢር እንዲህ የማይመለከታቸው ሁሉ የሚዳክሩበት፤ የሚያቦኩት፤ የሚጋጋሩት ይሁን? ምን ይባል እብደት ወይንስ መንቀዥቀዥ? እንኩሮ።
- መሪነት በዬደራጃው በዚህ ስሌት?
እነዚህ የክልል ፕሬዚዳንት የሚባሉት ስንት ሊሂቃንን በዬአካባቢያቸው ይመራሉ? አሁን ደግሞ አትችሉም እናንተ፤ ለዚህ አትበቁም ብሎ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ተጨማሪ ተሳታፊዎችን ከሥርዓት ውጪ በሆነ ሁኔታ አምጥቷል። የሚገርመው ተሳታፊዎች ይህን መቀበላቸው ነው። ይሄ አፋር፣ ይሄ ጋቤላ፣ ይህ ቤንሻጉል ጉምዝ የሚባለው ግን ከህሊናው የሆነ ሰው የለውንም? ቢያንስ መርህ እንጂ ሽምግልና አይመራንም ማለት እንዴት ይሳነዋል? እንዲሁም ተጨማሪ ሰውም አያስፈልገንም ህገ -ደንባችን አይፈቅድም ማለት አይችልም? እኛ ሮቦት አይደለንም፤ እኛ ዕቃ አይደለነም አይልምን? ሥልጣናችን አሳልፈን አንሰጥም አይልም፤ ተጨማሪ የጠላ ማህበርተኛ ወያኔ እንዳሻው መወታተፊያ ሲያከል ሰውነታቸው በእልህ አይነድም። አይቆጡም። መጠረዣ ሽቦ፤ ወይንም መለበጃ ጀሶ እንሻም አይሉም። ይህ እኮ ሰው መሆን ማለት እኮ ነው። ሰው ክብሩን፤ ነፃነቱን እንዴት ቁጭ ብሎ ለሌላ አሳልፎ ይሰጣል። በሬሳ ውስጥ እንደመኖር ማለት እኮ ነው። የክልል ፕሬዚዳንት ተሁኖ ስንት ጉዳይ በሃላፊነት እዬተማራ ለምስል ብቻ ተቀመጥ ሲባል እንዴተስ በጅ ይላል? እንደ ሌሉ እኮ ነው የቆጠራቸው የወያኔ ሃርነት ትግራይ። ዕቃ ናችሁ እኮ ነው የሚላቸው። ለምስል እንደ ሃውልት ተጎለቱ እኮ ነው የሚላቸው። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ወጀቡ ከገረደሰው አብሮ መውደቅ እንዳለም ልብ ሊሉት ይገባል። ሱናሜው ሁሉንም አይምሬ ነው። ራሳቸውን ለማዳን ጊዜው አሁን ነው፤ ከጠንካሮች ጎን የመሰለፍ። ምስጥ የበላው እንጨት እንኳንስ ለሌላው ለራሱም መሆን አይችልም። ተያይዞ ከመውደቅ ተያይዞ መዳን ያስፈልጋል፤ የተሻለውን ኦህዲድን ደግፎ ከጎኑ በጽናት መቆም ያተርፋል። የሁሉም መዳኛው አንድ መንገድ ብቻ ነው። አሁን ህዝብ ወያኔ ሃርነትን ትግራይን ድምጹን ራሱ መስማት አለርጅኩ ሆኗል። የድምጻቸው ቃና እራሱ ማድመጥ ያማል። አይደለም የድምጻቸው ቃና ፎቷቸውን ጹሑፍ ላይ ማያት አፍን ደም ደም ነው የሚለው። በቃቷል። አብቃቷልም።
ክውና።
ገዢው ፓርቲ ሁለመናው ያለቀ ነው። የተቀደደ። ሊጣፍም – ሊሰፋም – ሊጠገነም የማይችል። እራሱም ሳይጠፋ፣ ሀገርም ሳያጠፋ አንድ ወሳኝ እርምጃ መውሰድ አለበት እንደ ስብስብ „ኢህአድግ“ የሚሉት ቢሆን ጠንካሮቹ ወይ ከእሱ መላቀቅ ወይ ደግሞ ጠንክረው የተሸለ አመራር ሆነው መውጣት አለባቸው። ሁሎችም የኦህዲድን አቅምን በብልህነት እና በማስተዋል ሆነው አቅም ሊሆኑት ይገባል። ምክንያቱም ሥርዓቱ እንደ ሥርዓት ከፈረሰ አደጋው ከዚህ የከፋ ነው የሚሆነው። ለራሳቸውም። አደጋን መለካት ወይንም ማቀድ አይቻልም። የሚቻለው የአደጋውን ስፋት እና እርዝምት በሃሳብ መዝኖ ጊዜ ሳያጠፉ የሰከነ መፍትሄ መስጠት ብቻ ነው። መፍትሄው ደግሞ የማያገረሽ፤ የማያዳግም ሥርነቀል የፖሊሲ ለውጥ በሚያመጣ መልኩ ብቻ ሳይሆን፤ የመዳን ጉዞውን ሊመራ ለሚችል አቅም ፈቅዶ ቦታውን መስጠት። ፓሊሲ ብቻውን ፖሰተር ነው። ፖሊሲውን ዕውን ማደረግ የሚችል የህሊና አቅምና ክህሎት ያሰፈልጋል። እስከ ዛሬ እኮ የወያኔ ሃርነት ትግራይ በሽፍንፍን ካለ ክህሎቱ ነው ኢትዮጵያን ያህል ሀገር በሙህራኑ ግዴዬለሽነት፤ ቸለልተኝነት እና ዕውነትን ያለመድፈር ምክንያት ነው ይህን ያህል እንዲህ ቅብጥ እና ቅልጥ ሲል የኖረው።
ክወና።
ለእኔ ራሱ የዩንቨርስቲ ት/ ሚር ሃላፊነት ቢሰማው ተማሪዎች ሁሉ ወደ ወላጆቻቸው ቢመለሱ ነው የምመኘው። ምክንያቱ አዬሩ የሞት፣ የሰቀቀን፣ እና የዋይታ ነው … ሰላም እንኳንስ በሰው ውስጥ ምድሪቱም ሰማዩም ሁሉም ከጸጥታቸው ጋር አይደሉም። የጭንቅ አውሎ ነው ያለው። ይህን በትዕቢት፤ በማንህሎኝነት፤ በጉልበት፤ በሴራ ድርደራ፤ በለበጣ፤ በግድዬለሽነት፤ በጥገና አይደለም መሻገር የሚቻለው። ሁሉ ነገር በእውነት ውስጥ መለወጥ አለበት ግን በስክነት። ይህን ለማግኘት በመፍቀድ – በማድመጥ – በመሆን – በመቁረጥ – በመወሰን – ሰው በመሆን ብቻ ነው ይህንን የመከራ ቀን መሻገር የሚቻለው። ለዚህ ደግሞ የወያኔ ሃርነት ትግራይ በቀዳሚነት፤ በተከታይነት ጠ/ሚር ሃይለማርያም ደስአለኝ እስከ ቀዳማይ እመቤታቸው ድረስ እጅግ የገዘፈ ሃላፊነት አለባቸው። ለመልቀቅ ቆርጦ መወሰን። ህዝብ ይትረፍ። ተሰሩ የሚባሉት ነገሮችም ከኖሩ ይትረፉ። ነገ ይትረፍ። ትውልድ ይትረፍ። እንደ ፍጡር እሰቡ። ሳያመልጥ፤ ሳይመልጥም ወደ ራስ ተመልሶ ቢያንስ ቀደም ብዬ እንዳልኩት አሟሟትን ማሳመር ይበጃል። ድላላው እንኳንስ ሌላውን ራስን የማሳመን አቅም የለውም። ምክንያቱም ባዶነቱን የሚያውቀው ባዶው ብቻ ነው። ለቅሶ ድረሱኝም አያወጣም። ሰሚው ቢበዛ ሰባት ቀን ነው ለቀስተኛውን የሚያስተዛዝነው። ተያይዞ ከማለቅ፤ ተፈጥፍጦ ከሞሞትም መትረፍ። ሥልጣን ማጣትን በድፍረት ለራስ መንገር ይበጃል። አስፈላጊ ከሆነም „ሥልጣኔን በፈቃዴ እለቃለሁ“ ብሎ መጻፍ እና ማቃጠል። ጉልበት ይሆናል። የሥነ – ልቦና አቅም ይፈጥራል። ይረዳል። የተቆጣ ህዝብ እንዲራዳችሁ አወዳደቃችሁን ለማሳመር እሰቡት። መረዳዳት ለመወቃቀስ እንኳን ጊዜ ይሰጣል። የወያኔ ሃርነት ልዑላን የላችሁም። አለመኖራችሁን እወቁት። ተቀበሉትም። ባለመኖራችሁ ውስጥ እንኖራለን ብትሉ ትግሉ ከተፈጥሮ ጋር ይሆናል። የሥልጣን ቀጣይነቱ ሴራዊ ትብትብም እድገቱ አብቅቷል። አከተመ። ከባህር የወጣ አሳ ህይወት የለውም። ይብቃኝ።
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። መሸቢያ ጊዜ።
Advertisements
እንደ ጦርነቱ ምርጫውም ቀጣይ 7 ወር ያስቆጥር ይሆን...??? ሥርጉተ©ሥላሴ
Posted by admin
እንደ ጦርነቱ ምርጫውም ቀጣይ 7 ወር ያስቆጥር ይሆን…???
ሥርጉተ ሥላሴ
*…. የፀጥታው ሁኔታ አዲስ አበባ ባልቦላው ያለው ከዶር አብይ አህመድ ዘንድ ነው። ዘረፋ ሲያስፈልግ ባንክ አሰብረው ያዘርፋሉ፣ ሽብር ሲፈልጉ አሸባሪ አደራጅተው ይገድላሉ፣ እንዲህ ሲያሰኛቸው ደግሞ ባልቦላውን ይዘጋሉ። የሀጫሉ ነፍስ ለዚህ የኮረጆ ቀን የጦስ ዶሮ ነበር።
ዕለተ አርብ ማዕዶተ ኢትዮጵያ
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በቢሆነኝ የተብራራ ብራ
በሰብለ ሕይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራራ።
“ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።”
(ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯)
አንድ ነገር አሰኩኝ። ዶር ታምራት ነገራ ስለ ወት ብርቱካን ስኬት¡ እና ማሸነፍ¡ ዕንባ ይተናነቀው ነበር። ሲቃ ቢጤ። እኔ ምን እንዳሰብኩ ታውቃላችሁ የዕንባ ማዳረቂያ ሽክ ያለች የእጅ ማህረብ።
ስለ ትናንት ከሆነ ሥርጉተ የፈፀመችው፣ የተቀበለችው መካራ ወዘተረፈ ነው። ስለዚህ ፕሮፖጋንዲስት አያስፈልገንም።
ስለዛሬ ከሆነ ደግሞ አንድ አባል የሌለው መሥራች ፎርም ሞልተው ያልተመዘገቡበት ከህወሃት ሙራሹ ያለቀ ዕዳ ወደ አዲሱ ዕዳ በካሬታ እዬተጫነ የተገለበጠ ውራጅ አባል ተሸክሞ ለዛ ዕውቅና አሰጥቶ አሸነፈ ውርዴት ነው።
ይህም ብቻ አይደለም ሦስቱ ሰኔወች፣ ሦስቱ ጥቅምቶች ለዚህው የሸፍጥ ኮረጆ ጥርጊያ ነበር። በሰላም ተጠናቀቀ ለማስባል ርሸናው እስሩ ጦርነቱ ለዚህው የገዳ የምርጫ ኳኳቴ። እንደ አንድ በሳል ተንታይ ይህን ገመና ተሸክሞ ብርቱካን አሸነፈች የገማ እንቁላል ጫጩት ሆነ ይሆናል።
ይህም ሆኖ እስከ አሁን ውጤት ለመንገር ምጥ ነው የሆነው። ጋንቤላ ቤንሻንጉል ሲዳማ ምርጫው ቀጥሎ በማግስቱ ነበር። ቁሳቁስ እንኳን በቅጡ ለማስተዳደር ያልቻለ ዕንቅልፍ አቅም “አሸነፈች” ፌዝ፣ ስላቅ ነው።
በዓለም አራተኛ መዲና በዘመነ ዲጂታል ይህን መሰል ዝልግልግ ተግባር ብርቅ ሲሆን ከዕውር ቤት ዓንድ አይና ብርቅ መሆኑ አይደንቀኝም።
ተመክሮ የለም ተሰጥዖም የለም። ማደራጀት የማይክ፣ የፋሽን ውሎ አይደለም። ቢሮ እያደሩ እዬዋሉ የሰከነ ተግባርን ይጠይቃል። ምንም ምንም ነው።
የፀጥታው ሁኔታ አዲስ አበባ ባልቦላው ያለው ከዶር አብይ አህመድ ዘንድ ነው። ዘረፋ ሲያስፈልግ ባንክ አሰብረው ያዘርፋሉ፣ ሽብር ሲፈልጉ አሸባሪ አደራጅተው ይገድላሉ፣ እንዲህ ሲያሰኛቸው ደግሞ ባልቦላውን ይዘጋሉ። የሀጫሉ ነፍስ ለዚህ የኮረጆ ቀን የጦስ ዶሮ ነበር።
ብዙ ጊዜ ፅፌያለሁ እኔ ይህ ሁሉ መፈናቀል፣ ግድያ፣ ጭፍጨፋ፣ ግፍ አብይዝምት ካለተቀናቃኝ ዙፋን ለመድፋት የገዳ ልዕልት መንገዳቸው ጨርቅ እንዲሆን የተሰናዳ የሞገድ ልብወለድ ትራጀዲ ትወና ነው።
እራሱ ወሮ አዳነች አበቤ ም/ ከንቲባ ከመሆናቸው በፊት የተፈፀመው የባልደራስ መሥራቾች እስር ለዚህ ቀን መሰናዶ ነው። ከንቲባዋ በድሎት፣ በምቾት ካለ ጫና የገዳን ወሩራ፣ የገዳን አስምሌሽን፣ የገዳን መስፋፋት እንዲያስፈፅሙ ነው።
ቲም እስክንድር ባይታሠር ሙሉለሙሉ ባልደራስ ያሸንፍ ነበር። ይህ ብቻ አይደለም ዶር ታምራት ከሰይፋ ሾው ጋር ወት ብርቱካን ሚዲቅሳ ጋር የተደረገው ቃለ ምልልስ አዲስ አበቤ ግልብጥ ብሎ ወጥቶ እንዲመርጥ አድርጓል አለ። ወቷ በተወዳደሩ እና ያያት ነበር።
አዲስ አበቤ የወጣው አቶ እስክንድር ነጋ ይወዳደራል ስለተባለ ብቻ ነው። ምስሉ ተለጥፎ ንቅንቅ አላለም ነበር። የተመዘገበው አንድ ሚሊዮን የመሙላት አቅም አልነበረውም።
አዲስ አበቤ ለኢትዮጵያዊነት ክትር አይሻም። ማን ምን እንደሆን ፕሮፖጋንዲስት አይሻም። አዲስ አበቤ ሙያ በልብ ነው። ቲም እስክንድር ባይሠር በተፈጠረበት መክሊቱ ልክ በንፅህና ይጓዝ ስለነበር ድሉ ይታይ ነበር። ግን ሰላዩ ጠቅላይ ሚር ከ97 ጀምሮ ባጠኑት ማስተር ፕላን አሁን ባለበት ሁኔታ ሂደት ይተክዛል።
አዲስ አበቤ ለኢትዮጵያዊነቱ ዘብ አደር ነው። ማገዶም!
አቶ እስክንድር ነጋ ቅባዕው ታይቷል። ዘመን መሰከረ። ግሎባል ታሪክ በኢትዮጵያ ምድር ተሰርቷል። የእሱ ተፅዕኖ ፈጣሪነት በቅናት ላበዱት ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ መስጥረው የያዙት በሽታ ነው።
ሰንሰለቱ ትብትቡ ከኢትዮጵያዊነት ጋር ግብግብ ነው። አዲስ አበቤ ካሸነፈ ሰንሰለቱም፣ ትብትቡም ይፈታል። ከተሸነፈ መከራው የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያዊነት ይሆናል።
እንደ ጉም ሽንት ወደ ኋላ ዬሚጓዘው ዝርክርኩ የገዳ ምርጫ ቦርድ ሽርክትክት ዕድምታው ቀጣይ ነው። ያልቦካ የምርጊት ጭቃ። ኢትዮጵያ ካለ አቅሙ በሚቆለል ኃላፊ ፍዳዋን አዬች። የካህዲው ብዛት ወዘተረፈ ነው። ግን ኢትዮጵያ አምላክ አላት። ቀኑን ጠብቆ ይቀጠቅጠዋል ማህበረ ካህዲን።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
የኢትዮጵያ አምላክ ካህዲን ቅጣልን። እባክህን?
Filed in: Amharic
https://ethioreference.com/archives/28259
https://ethioreference.com/archives/28259
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ