በጎንደር ከተማ የመስቀል በዓል ዕለት “የፈራ ይመለስ”የሚል ቀይ ጽሁፍ የታተመባቸው ቀያይ ቲሸርቶች የለበሱ ወጣቶች ተቃውሞ ሲያሰሙ ዋሉ October 1, 2015, 8:42 am
በጎንደር ከተማ የመስቀል በዓል ዕለት “የፈራ ይመለስ”የሚል ቀይ ጽሁፍ የታተመባቸው ቀያይ ቲሸርቶች የለበሱ ወጣቶች ተቃውሞ ሲያሰሙ ዋሉ
የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ) በክርስትና እምነት ተከታዮች የመስቀል በዓል ዕለት የጎንደር ከተማ “የፈራ ይመለስ” የሚል ፅሁፍ የታተመባቸው ቀያይ ቲሸርቶች በለበሱ ወጣቶች ተጥለቅልቃ ከፍተኛ የሆነ አመፅን አስተናገደች
የጎንደር ከተማ ለውጥ የሻቱ ወጣቶች ከ500 በላይ የፈራ ይመለስ የሚል ፅሁፍ የታተመባቸው ቀያይ ቲሸርቶች አሳትመው በማሰራጨት በጎንደር በከፍተኛ ድምቀት በየአመቱ መስከረም 17 ቀን የሚከበረውን የመስቀል በዓል ለመታደም ደመራው ወደ ሚለኮስበት መስቀል አደባባይ ይተማሉ፡፡
ቀጥሎም ደመራው የሚለኮስበት መስቀል አደባባይ ከምዕመኑ ቁጥር ባልተናነሰ ሁኔታ በፌደራልና በልዩ ኃይል የህወሓት ፖሊሶች ተወሮ በማግኘታቸው የደመራውን በተለመደው ሰዓት አለመለኮስ በምክንያትነት በመጠቀም በአምባገነኑ የህወሓት ዘረኛ አገዛዝ ላይ ተቃውሟቸውንና በጉልበት አንገዛም ባይነታቸውን በተለያዩ መንገዶች ገልፀዋል፡፡
የህወሓት ፌደራልና ልዩ ኃይል ፖሊሶች ለአገዛዙ ያላቸውን ጥላቻና ተቃውሞ የገለፁትን “የፈራ ይመለስ” ያሉ ባለቀያይ ቲሸርት የጎንደር ወጣቶችን በቆመጥና በአፈሙዝ በብርቱ በመደብደብ ተቃውሞውን ለማርገብ ሞክረዋል፡፡ በመሆኑም በወጣቶቹ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎች በርካታ ምዕመናን ላይም ጉዳት ደርሷል፡፡
ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የከተማዋ ወጣቶች እና ነዋሪዎች ጭምር በህወሓት ፖሊሶች እየታፈሱ ወደ ዘብጥያ ተወስደዋል፡፡ በተለይም ደግሞ “የፈራ ይመለስ” የሚል ቀያይ ቲሸርቶች የለበሱ ወጣቶች በልዩ ሁኔታ እየታደኑ ታፍነው እየተወሰዱ መሆናቸው ታውቋል፡፡
ከ100 በላይ የሚሆኑ የጎንደር ወጣቶች በልዩ ኃይል ካምፕ ውስጥ ብቻ ታጉረው ከፍተኛ ድብደባ እየተፈፀመባቸው እንደሚገኝ ተረጋግጧል፡፡
በወልቃይት በርካታ አካባቢዎች የሚገኙ ገበሬዎች አዝመራቸውን እንዳይሰበስቡ በፌ. ፖሊስ በመታገዳቸው ጥይት ያታኮሰ ከፍተኛ ግጭት መቀስቀሱ ተሰማ
https://zehabesha9.rssing.com/chan-19552299/all_p216.html
ተኸለ አምባ እና በሌሎች የወልቃይት በርካታ አካባቢዎች የሚገኙ ገበሬዎች አዝመራቸውን እንዳይሰበስቡ በፌደራል ፖሊስ በመታገዳቸው ጥይት ያታኮሰ ከፍተኛ ግጭት መቀስቀሱ ተሰማ ውጥረቱ አሁንም ተባብሶ እንደቀጠለ ነው፡፡
በወልቃይት የሚገኙ ገበሬዎች ማንኛውም ሰው ተነስቶ የሚያርሰውን በተለምዶ “ሞፈር ዘመት” እየተባለ የሚጠራውን መንገድ ተጠቅመው በግንቦትና በሰኔ ወራት ጫካ መንጥረው ምድረ በዳውን በማረስ የተለያዩ አዝዕርቶችን በተለይም ሰሊጥ ዘርተው ያበቀሉ ሲሆን አሁን በመኸር ክወና ላይ ተሰማርተው ባሉበት የህወሓት አገዛዝ ደን ጨፍጭፋችሁ አርሳችኋል በሚል ተልኮሻ ምክንያት ፌደራል ፖሊስ በየማሳቸው በማሰማራት ለማገድ በመሞከሩ ነው “ግንቦት እና ሰኔ ገና መሬቱን ማልማት ስንጀምር ከተቆረቆራችሁ ለምን አልከለከላችሁንም?” በሚል ህዝቡ በአንድነት ተነስቶ ግጭት የተቀሰቀሰው የህወሓት ፌደራል ፖሊሶች ተክላይ የተባለውን ገበሬ ከማሳው አስረው ወስደው አደባይ ላይ በመረሸናቸው የዘርባቢትና እድሪስ ቀበሌዎች ነዋሪዎች በአንድነት “ሆ” ብለው ተነስተው ፖሊሶችን ትንቅንቅ ገጥመዋቸዋል፡፡
በተለይም የአካባቢው ሚሊሻዎች ከህዝቡ ጎን በመቆም በፌደራል ፖሊሶች ላይ ተኩስ ከፍተው ውጊያ በመግጠም ሁለት ፖሊሶችን አቁስለዋል፡፡
በአካባቢው የታጠቁ ሚሊሻዎችና ገበሬዎች የደረሰ አዝመራቸውን እንዳይሰበስቡ ለማገድ በየማሳው በተሰማሩ ፌደራል ፖሊሶች መካከል የተከፈተው ጦርነት ለማስቆም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ኃይል በአካባቢው ተሰማርቶ ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን ግጭቱ የባሰውን ተቀጣጥሎ የሰፈነውን ውጥረት እንዲያይል አደረገው እንጂ ሊያረግበው እንዳልቻለ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገልፀዋል፡፡
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ