አቶ በቀለ ገርባ ከሱሴ የተቀዳ። ለአማራ ህዝብ ቫልዬም)
«ይህን ሁሉ ችሎ ያ ህዝብ መኖሩ እውነተኛ ሰላም ወዳድ ህዝብ ስለሆነ ነው አገሪቱ እንዲህ አይነት ትርምሥ ውስጥ ለምን ገባች ለሚለትም አይቻልም ቀንና ሌሊት እንዲህ አይነት የጥላቻ ስብከት እዬተሰበከ»
( አቶ በቀለ ገርባ ከሱሴ የተቀዳ። ለአማራ ህዝብ ቫልዬም)
#ይህን ገብተው ያንብቡ። የፖለቲካ ትግልየጎርፍ ውሎ አይደለም።
ጤና ይስጥልኝ እንደምን አደርን? ደህና ነን ወይ? አጣዬ እና ኤፍራታ እንደምን አደሩ ይሆን።
ከስንብቾዬ የአቤን ሚዲያ አላዳመጥኩም። ጊዜውም የለ። ይህን የዘፍጥረቱ ደርማሽ አሉ ብሎ ከቀደመው ጋር አነፃጽሮ አቅርቦታል ከቀደመው ጋር። ቅን ሰው። ነው። የደንብያ ነገር ወተት ነው።
የሆኖ ሆኖ በወቅቱ አንድ ጭምት ፖለቲከኛ አውቅ ስለነበር በእንግሊዘኛ ይተርጉሙልኝ ብዬ አሻም አሉኝ። እና ቀረ። በጦርነቱ ወቅት ከፍተኛ ሰናይ ላይ ነበሩ።
እኩል ከመንግሥት ሚዲያ ጋር ሲሰሩ አይቻለሁኝ። ስለማከብራቸው በፍቅር ተሰነባበትን። ጦርነቱ የሆድ ዕቃውን ስለተረዳሁኝ እሞግት ስለነበረ።
ዛሬ ስለስሜን ፖለቲከኛ ይነገረናል። ጆሮ አይሰማው የለ። ትናንት እኮ ኢትዮጵያዊውን አብርኃም ሊንከን ጠብቁ ተብለን ነበር። የሆነ ሆኖ እኒያ ወዳጄ ሰሞኑን ምርር ያለ ፁሁፍ ፅፈው አነበብኩኝ። ስለ አማራ ህዝብ ተቆርቁረው።
አቶ በቀለ ገርባ አውሮፓ ስሜን አሜሪካ ህዝባቸውን ሰብስበው በሚጠዬፋት የአማርኛ ቋንቋ እዬደሰኮሩ ነው። የአማራ ድርጅቶች፣ ተቋማት ደካማነት ቢዛ አሰጣቸው። እንጂ እሳቸው በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ፍርድ ሊሰጣቸው የሚገባ ሰው ናቸው።
1) ዘፍትረትን ደርምሰዋል። የክርስትና ዕምነት ተከታይ ሁሉ ሊሞግታቸው ይገባ ነበር።
2) ግሎባላይዜሽንን ጥቁር አልብሰዋል።
3) የዓለምን የንግድ ሲስተም አውከዋል። የገባይ ህግን ተፃረዋል።
ይህን በሚመለከት ሙሉ ንግግራቸውን በአማርኛ የተፃፈውን ትርጉሙን ከኦሮምኛ ወደ አማርኛ የተረጎመውን ለተለያዩ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ አካላት እኔ ሰነዱን ልኬዋለሁኝ። ስለዚህ ፀፀት የለብኝ። በብሎጌ በተከታታይ ፁሁፍ ሞግቻለሁኝ። ስለዚህም ፀፀት የለብኝም።
ሙሉ ንግግራቸው ከወጣበት ቦታ ከደጉ ዘሐበሻ ፔጅ ተሰርዟል። ግን በተለያዩ ሚዲያወች ይኖራል ብዬ አስባለሁ። ከእኔ ዘንድም አለ። የላኩላቸው ድርጅቶችም መደበኛ ስለሆንኩ ያስቀምጡታል ብዬ አስባለሁኝ።
ችግሩ ተርጓሚወቻቸው አፍቅሮተ ህወሃት፣ አፍቅሮተ የኦሮሞ ፖለቲከኛ ከተሆነ ጋዳ ነው። ተኝቶ በለኝ ላለ ህዝብ እንዲህ እንደ ሽንብራ ቂካ ለሚገላበጥ የወለጋ የኦነግ ፖለቲካ ቀልብም፣ አደብም መስጠት አይገባም ባይ ነኝ።
#ለምን አሁን?
1) በቅርቡ ሄጀ እዋጋለሁ የሚል ዕድምታ ያለው ንግግራቸውን ተቆርጦ አዳምጫለሁኝ። በሌላ በኩል ከህወሃት ጋርም የውስጥነት መስመር የመዘርጋት አስፈላጊነት በአጽህኖት ሲነገር አዳምጫለሁኝ።
ይህ ማለት ህወሃት በአማራ ክልል እና በአፋር ክልል የፈፀመው ወንጀል ትክክል ነው ብሎ ከማመን ይመነጫል።
2) ይህ የኦሮሞ ፖለቲካ መራሽ መንግሥት አወዳደቁ እንዳይከፋ የመጠገን ስልት ነው። በግሎባላይዜሽን ደረጃ የአማራ ልብ ወደ የሚራራበት መንፈስ ለመመለስ የስልት ጊዚያዊ ሽፍት ነው። ዓለማችን የኦነግ ፖለቲካ አክ፣ ሃራም ከሚልበት ደረጃ ከደረሰ ወደፊት ተስፋው ይሟጠጣል፣ በሱሴ ፖለቲካ። ይህን የማዳን ሁነት ነው።
3) ይህ ሥርዓት ከወደቀ ካለ አማራ ፖለቲካ አንሳ ወሳንሳ ስለማይቻል አዲስ የፖለቲካ ኃይል ሆኖ ተሳታፊ ለመሆን የአማራ ህዝብ ቅን አይደል፣ አጋንሳን እንደ ተሸከመ በቄንም አሽኮኮ እንዲያደርግ ነው።
በሰከነ፣ አቅል ባለው፣ በረጋ፣ አደብ በገዛ ሁነት እራሳችን ችለን ለምንተጋ ፖለቲከኞች አሻንጉሊት ገዝቶ ለሚሸልመን ማንኛውምፀረ ሰው፣ ፀረ ተፈጥሮ አመክንዮ በጅ አንልም። ስለሳቸው እና ስለ ድርጅታቸው ኦፌኮ ከዚህ ቀደም በታገልኩት ልክ ይቀጥላል።
ከኦነግ ጋር የኦሮምያ መንግሥት የመሰረቱ እኮ ናቸው። ኦነግ አዲስ አበባ ሲገባ ተንሳፈው፣ በትቢትተነፋፍተው ባደረጉት ንግግርም ላይ እዚህው ብሎጌ ላይ ጽፌበታለሁኝ።
#የኦነግ ፖለቲካ አራማጆች ለህግም አይገዙም።
በሥርዓተ መንግሥት ምሥረታ ስላለፋ!
1) በዘመነ ህወሃት ፍርድ ቤት ቀጠሮ ነበራቸው አቶበቀለ ገርባ። እና ዳኞች ሲገቡ ከመቀመጫቸው ያልተነሱ ብቸኛው ተከሳሽ ነበሩ።
2) ለሁለተኛ ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ከጣሱት፣ ኮታቸውን አስተካክለው ከማይለብሱት ከአለቃቸው ከፕ/ መራራ ጉዲና ጋር የሁለተኛውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማናለብኝነት ጥሰው ወለጋ ህዝብ ስብሰባ ጠርተው ነበር።
3) በኦዴፓ ኦህዴድወኦነግ ጉባኤ ተጋብዘው ሰብሳቢውን አድሬስ ሳያደርጉ ቀርተዋል።
መሪ መርኽነት ነው። መሪነት ህጋዊነት ነው። ያሳዝነኛል የቁቤ ትውልድ። መሪ አላገኜም። ብቅ አለ ስንልከዛው ውስጥ ተዘፋፍቀው ይገኛሉ።
ማንምሰው ከህግ በላይ አይደለም። ህግ የሰማይም የምድርም አለ። ሁሉም ሰውከ ህግ በታች ነው። የፖለቲካ ድርጅት መሪም ሊጣሱ የማይችሉ ግሎባል ህጎች አሉ። ግሎባል መርሆች አሉ።
ለኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ግን ተረት ነው። ሁሉ ነው የሚጥሰው። የኦሮሞ ፖለቲከኞች ብቻ ሳይሆኑ።
ቲወሪውን ብታማረው ወደ ሥራ ስትገባ እንደ ተራራማ ሰንሰለት የተቆላለፋ መርህ፣ ህግ አለ።
የፖለቲካ ድርጅት የፓርቲ። ከዚህ አንፃር የትውልድ የሆነ፣ የሚሆንም ድርጅት የለንም። የትናንት እርሾ ዛሬን ሲሰጥ የዛሬ እርሾ ግን ነገን ለመስጠት ስጦ ላይ ነው። ልሙጥ።
የአማራ ልጅ ልብ ግዛ። ህሊናህን በፀናቋሚፍላጎት አፅና። ቃል እና ንግግር ከዓላማህ እንዳያዘናግህ።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
13/07/2022
የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ በፅናት ይቀጥላል።
የምንታገለው ኢትዮጵያ አማራ እንዲመራም ጭምር ነው!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ