ልጥፎች

የአማራ እረቀ ሰላማ እንዴት? ከእነማንስ ጋር??? #ሚስጢረኛችን ኢትዮጵያ ብቻ ናት!

ምስል
  የአማራ እረቀ ሰላማ እንዴት? ከእነማንስ ጋር??? እንዴት አደርን? የቅኔ አድባራት እንዴት ውለው አደሩ ይሆን? እነ ማህበረ ቅንነትስ እንዴት አላችሁልኝ??? #ሚስጢረኛችን #ኢትዮጵያ #ብቻ #ናት ! "የቤትህ ቅናት በላኝ።"       ይህ ጥያቄ ከ32 ዓመት በላይ ተቀንቅኗል። አማራ እንደ አማራ የጠላውም፤፦የሚጠላውም፤፦የሚያሳድደውም፤፦የሚያወግዘውም፤ ያፈናቀለውም፤፦ያሳደደውም፤ መኖሩን የቀማውም፤ ጋብቻ የከለከለውም፤ በጉርብትና ፊት የነሳውም፤ በግብይት ያገለለውም አይደለም ማህበረሰብ፤፥ተቋም ቀርቶ ግለሰብም የለም። ልብ እና ኩላሊት የሚመረምረው አምላክ አላህ ያውቀዋል። የእኛን ቅንነት እና ገራገርነት። ስለዚህም አማራ ሊታረቅም ብሎ አቤቱታ የሚቀርብለት ግለሰብ፤፥ተቋም ማህበረሰብ የለውም። ይልቁንም ከሙሉ የህሊና ካሳ ጋር ሊካስ የሚገባው የአማራ ህዝብ ነው። በዳዮቹ መበደላቸውን አቁመው ይቅርታ ጠይቀው ሊክሱት ይገባል። የመንፈስ ካሳ። ውሃ በቀጠነ ማቱ የሚወርደው በአማራ ላይ ነው። ነፃ አውጪወች ሲደራጁ የማኒፌስቷቸው ጭብጥ ፀረ አማራነት ነው። ስለዚህ ይህን ጭብጥ ቢተውት ተቋማቸው የሁሉም ይፈርሳል። እርቀ ሰላሙ ይህ እና ይህ ብቻ ይሆናል።   ህወሃት ሙሉ 47 ዓመት ሚዲያው ሊቃውንቱ ዛሬም ፀረ አማራ ዲስኩር ነው። ጦርነት የከፈተው የ፬ኪሎው ኦነግ ሆኖ ዛሬም ናዳ የሚለቀቀው በአማራ ላይ ነው። ኦነግ ፬ ኪሎ የንጉሦችን ንጉሥ የአጤ ሚኒሊክን ቤተመንግሥት በአማራ ትጋት እና ሙሉ ድምጽ አግኝቶ ዛሬም አማራ ላይ ዛሩ እንደተደረረ ነው። የከተማ ተቋማቱ፤ የጫንካ ክንፋ ውግዘቱም ምንጠራውም አማራ እና ጠረነ አማራ ብቻ ነው። የኦነግ ሊቃውንት የላንቃቸው ጠበለ ጣዲቅ ይህው ፀረ አማራነት ነው። ተማሩ አልተማሩ አንድ አይነት ማት ይ...

ቅዱስ ሲኖዶስ ስንቱን የቅድስና እረኝነቱን አግልሎ ሊዘልቀው ይሆን?

ምስል
      ቅዱስ ሲኖዶስ ስንቱን የቅድስና እረኝነቱን አግልሎ ሊዘልቀው ይሆን? "ከነገር፡ ሁሉ፡ አስቀድሞ፡ ሄኖክ፡ ተሠወረ። ከሰውም፡ ልጆች፡ በተሠወረበት፡ ቦታ፡ ሳለ፡ የሚያውቀው፡ አልነበረም፡ ይሙት፡ ይዳንም፡ የሚያውቅ፡ የለም። ሥራው፡ ሁሉ፡ በተሠወረበት፡ ወራት፡ በቅዳሴያቸው፡ ከሚተጉ፡ መላዕክት ጋርና፤ ከቅዱሳን ጋር ነበር። (መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ ፬ ቁ ከ፩ - ፫) የፀጋ // የበረከት /// የምርቃት /// የቅብዓ // የትንግርት// የትንቢት// የመሰጠት// የምኞት // የራዕይ// የቅዱሳን// የደናግል፤ የሰማዕታት፦ ባዕት ፍልስፍናዊት ኢትዮጵያ የእኛ! ቅድስ ሲኖዶስ ዬቅዱስ ላሊበላን ብጽዕና፤ ልዕልና ሞገሥ እና ግርማ አግልሏል። ቅዱስ ሲኖዶስ የቅኔው ደብረ ኤልያስ ገዳምን ሰማዕትነት አግልሏል። ቅዱስ ሲኖዶስ የቅዱስ ደብረ ማርቆስን #ካስማነት አግልሏል። እንዲህ በሁለገብ ሸፍት ቅድስናው ሲስተጓጎል??? ዝምታ??? ቅዱስ ሲኖዶስ እያንዳንዱ በዕት የሊቀ - ሊቃውንት መፈጠሪያ የሆኑትን መላ የአማራ ክልል ገጠራም ቅዱስ ባድማወችን አግልሏል። ቅዱስ ሲኖዶስ የሻሸመኔን ሰማዕታት ገድል እና ታምራትን አግልሏል። ከዕጬጌው ጀምሮ ብፁዓኑ እዛው ሄደው ጉባኤ ሊያካሂዱ ይገባ ነበር። ግን በነበር ተከዘነ። ይህ ማለት ቅዱስ ሲኖዶስ አስተዳደራዊ ተግባሩን እንጂ የዶግማውን መተግበሪያ ቋቱን በሚመለከት ዝሏል። ለዚህም ነው ብፁዓንወቅዱሳን አባቶቻችን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የሚገናኙበትን መሰላል መዘርጋት ግድ የሚላቻው። የወሉ ወይንም የጋራው ሱባኤ ሳይሆን ለእኔ ከሊቅ እስከ ደቂቅ አቨው ብፁዓን ሊቀ ጳጳሳት ገዳምን በሱባኤ የሚያገኙበት ትልም ሊኖራቸው እንደሚገባ ይሰማኛል። የተከበሩ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ የንስኃ አባት ሊሆኑ አይችሉም! ፈጽሞ! ግን...

19.11.2020 ረመጥ ነው ወልቃይትወጠገዴ።

ምስል
  ረመጥ ነው ወልቃይትወጠገዴ።   እፍታ። በድጋሚ ለጥ ብዬ እጅ እነሳለሁኝ። ህወሃት ከድል እስከ ውድቀቱ የጎንደር ሁነት ምን ነበር የሚለውን የነበርኩበትን በምልሰት ቅኝት አቅርቤያለሁ። ማንበብ ፀጋቸው ለሆኑ ወገኖቼ፣ ታሪክን እንደ አግባቡ ለሚያዳምጡ፣ ለሚይዙ ወገኖቼ፣ በጭልፋ ፕሮፖጋንዳ የወልቃይትጠገዴ ጉዳይ ላይ ለሚያላግጠው የኦዳ ሥርዕዎ መንግሥትም ነገረ ሥራው የሳሙና አረፋ ነውና ውስጤን ያይ ዘንድ የፃፍኩት ነው። ልቀት። የወልቃይት እና የጠገዴ ጥያቄ ከአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ዘመን መባቻ ብቻ የሚመስላቸው አሉ። ህወሃት ጫካ ሆኖ ሲወስን ከህወሃት ጋር የነበሩ የጠገዴ፣ የወልቃይት ልጆች አፈንግጠው ወጥተው በለመዱት ዱር ገደል ሲታገሉ ነበር። ውጭ የወጡትም ለአንዲት ሰከንድ ከተጋድሏቸው ዝንፍ አላሉም። በዘመነ ህወሃት ረጅሙ ተጋድሎ ጋር የዘለቅን በርካታ ጎንደሬዎች የህሊናችን ሞተር እርስታችን ነው። ይህ ሊታወቅ ይገባል። ውስጣችን የማይበርድ ረመጥ አለ። የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ሲነሳ አቶ አሥራት አብርኃ የገብያ ግርግር ሲሉት ወጥቼ ቅጥ አስይዠዋለሁ። ማንነት ሸቀጥ አይደለም በገብያ ህግ የሚተዳደር። ድፍረታቸው ልክ ስላልነበረው ነበር ወጥቼ የሞገትኳቸው በደጉ ሳተናው ድህረ ገፅ። ኢሳትም ሳቢያ እያለ ሲያላግጥ፣ ግንቦት ሰባትም የነፃነት ኃይል ተጋድሎ እያለ ሲለነቁጥ ልካቸውን እንዲይዙ የብዕር ቦንብ ተልኮላቸዋል። ጠቅላዩ ወደ ሥልጣን ሳይመጡ ጭምጭምታ ሳይኖር በዝርዝር ለዛን ጊዜው የኦህዴድ ሥራ አስፈፃሚ የፅህፈት ቤት ኃላፊ፣ ለዛሬው ጠቅላይ በስክነት አስረድቻቸዋለሁኝ። የወልቃይትወጠገዴ ጉዳይ አገር በማስቀጠል ጉዳይ ምክንያታዊ ነው። ገዢ መሬት ነው። ህወሃት ሞተ ተብሎ ማወጅ የሚቻለውም ይህ ርስት ወደ ባለቤቱ ሲመለስ ...

31.10.2020

ምስል
  በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ። አሜን።     "የሰው ልብ መንገድ ያዘጋጃል፣ እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።" ምሳሌ 16/9 የነግህ ፀሎት። 1) የተመድ ሰላም አስከባሪ ኃይል ኢትዮጵያ እንዲገባ መሻት። 2) የአማራ ክልል የከፍተኛ ተቋም ተማሪዎች ከክልላቸው ውጪ ወደ ሌላ ክልል እንዳይመደቡ መሻት። 3) በኦህዴድ ኦነግ የበቀል መሥመር እንደ ወጡ የቀሩት የአማራ እጩ ሊቃናት የደንቢደሎ ዩንቨርስቲ ተማሪዎችን መጨረሻ ለማወቅ መሻት። 4) ሰው አጥፊው የህወሃትወኦነግ ህገ መንግሥት ሙሉለሙሉ እንዲቀዬር መሻት። 5) መርዛማው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከኢትዮጵያ ይጠፋ ዘንድ መፀለይ። 6) የሥርዓት ለውጥን መሻት። ወሥብኃት ለእግዚአብሔር። ወስብኃት ለእግዚአብሔር።

19.11.2019 የኦዳ ኢንፓዬር ማፏሸኪያ ህወሃት ነው።

  የኦዳ ኢንፓዬር ማፏሸኪያ ህወሃት ነው። የኦዳ ኢንፓዬር ማፏሸኪያ ህወሃት ነው። ይህን ግርባው ብአዴን፣ ተደማሪው ግንቦት ሰባት እስከ ቲፎዞው፣ ሚዲያው ኢሳት፣ የኦዳው ኢንፓዬር መለከት ነፊ የአንድ አፍታ አወያይ ጦማሪ ስዩም ተሾመ ቀጥ ሰጥ ለጥ ብለው የማፏሸኪያ ብር አንባር በመሆን ያስፈፅማሉ። ሁሉም ሰው ህሊና ያለው ሁሉ ከማፏሸኪያ እንቅልፍነት ያወጣው ዘንድ አምላኩን ይማጠን። እኔ አፈንጋጯ ሥርጉተ ሥላሴ የኦዳ ኢንፓዬር ማፏሸኪያ፣ እንቅልፍ አማጭ ባለመሆኔ እግዚአብሄርን አመሰግናለሁ። ህወሃትን በሚመለከት የራሱን ድርጅት በቅጡ መምራት ያልቻለው የአብይ መንፈስ እኔን በዛ ቦይ ውስጥ ማስገር ፈፅሞ አይችልም። ፕሮፖጋንዲስትም አልፈልግም። ቀስቃሽም አያሰኜኝም። ምክንያት። ገና በልጅነት ዕድሜዬ በተደራጀ ፓርቲ በከፍተኛ ህዝባዊ የኃላፊነት ሆኜ ታግዬዋለሁ። ጫካውንም ካቴናውንም ስደቱንም አውቀዋለሁ። እነሱ ከህወኃት የሥልጣን ፍርፋሪ ለቃሚ ኦፋ በነበሩበት ጊዜ ሁሉ ሥርጉትሻ ህወሃትን ሞግታለች። የራሷም ወርቅ የሆነ አሻራ ከእነ ሙሉ ማስረጃው አላት። አሁን እነሱም ከፖለቲካ ድርጅት ተቆጥረው የጭካኔያቸው መለበጃ አዲስ ፀረ ህወሃት ዘመቻ ቢጀምሩ ሸማ በዬዘርፋ እንደሚለበስ ሥርጉተ ሥላሴ ጠንቅቃ ታውቃለች። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አንዲት ቀን ድርጅታቸውን መምራት ሳይችሉ ነው በአማራ አቅም የሚፎክሩት፣ የሚያቅራሩት። መቼ ነው እሳቸው ሙሉ ኢትዮጵያን የመሩት፣ ያስተዳደሩት? መቼ ይነገረና። እሩብ አገር እንኳን ይመራሉን? ይህ አቅም ሲያንሳቸው በሴራ ፖለቲካ፤ በህዝብ ሰቆቃ መንበራቸው የማይደፈር አድርገው ለማሳዬት ይጥራሉ። ውሽልሽል። ጉዳዩ የውሽማ ሞት ነው። ገናና አገር እንዲህ ላርባ መሆን እንኳን ባልቻለ አቅም ልትመራ አይገባትም። ህወሃት አረረም መረረም 27...

19.11.2019 የሞት ጠረን ለሴራ ፖለቲካ ቀመር በኦዳ ኢንፓዬር።

ምስል
  የሞት ጠረን ለሴራ ፖለቲካ ቀመር በኦዳ ኢንፓዬር።     እንዴት ናችሁ ጤና አዳሞቼ? ደህና ናችሁ ወይ? ኦዳና ጃራ ግብግባቸው በጉልህ እስኪወጣ ቀዳሚው የአህድዮሽ ጉዞ በፀረ ኢትዮጵያዊ መንፈስ ይቀጥላል።    ከዚህ መከራ የሚድነው አሁን ባለው ሁኔታ የአድዋ ሥርዕዎ መንግሥት ብቻ ይሆናል። 18 ወራት የኢትዮጵያን መከራ ያልወቀጠው እሱ ብቻ ነው ማለት ይቻላል። የቀረበት የማህል አገር ዘመናይነት ብቻ ነው። እርግጥ ነው በራሱ መስመር አገርን አምሷል። ሰፊ ስለሆነ እሱን አቁሜ ወደ ዋናው እርእሴ ልሂድ።   በዚህ 18 ወራት የበቀል ማወራረጃ፣ የጭካኔ የመሞከሪያ ጣቢያ የነፍስ ይማር ባዕት ያልሆነ አዬር ባዕት አልነበረም። ቁንጥንጡ፣ ዝርክርኩ፣ መሰሪው፣ ሸፍጠኛው የአብይወለማ ሌጋሲ ተጭኖ በያዘው የአማራ ህዝብ እና መንግሥት ከቀደሙው ዘመን ባላነሰ ፍላጎቱን ለማስፈፀም የመሞከሪያ ጥንቸል አድርጎት ባጅቷል።   አሁን ግዙፋን ኦፕሬሽን በእንደልቡ አቶ ዮኋንስ ቧያለው እና በአቶ መላኩ ፈንታ የስሜን አሜሪካ እና የለንደን ጉዞ ሀ ብሎ ይጀምራል። ሲመለሱ የእራሱ እግር የእግሩ ራስ ሆኖ ይጠበቃቸዋል።   በዚህ ማህል ሁለት አውራ ጉዳዮችን እንይ። ሃሳብን የማስተናገድ አቅም። ጥያቄ መጠዬቅ በህግ ያስቀጣል በዴሞክራሲ አሻጋሪው ጠቅላይ ሚኒስተር የህሊና አቅም። ሽብሽብ። የተገደሉት ሊሂቃን በሙሉ የሞገቱ ስለመሆናቸው እኔ በግሌ አልጠራጠርም። የታሠሩትም ቂሙ የሚመነጨው ሞገታችሁኝ ነው። ጠቅሚሩ ቶለራንሳቸው ዜሮ ነው። ፈሪም ናቸው።   መናገር መናገር መናገር ጥሪያቸው ይህ ነው። ማድመጥ አቻችሎ መጓዝ አልተፈጠረባቸውም። ስለዚህ ዴሞክራሲ ሞቶ የተቀበረው እሳቸው በህይወት የተፈጠሩበት ዕለት ነበር። እኔ ዴሞክራሲን ...