ኦሮምማ እና የአብይዝም ብልፅግና አንድ ናቸው።
ኦሮምማ እና የአብይዝም ብልፅግና አንድ ናቸው። የሥም ልዩነት ካልሆነ በሰተቀር ሁለት ሳይሆን መንፈሱ አንድ ነው። መነሻውም መድረሻውም ገዳ ነው። ፍኖተ ካርታ አያስፈልግም የሚሉት የገዳ ሰንድን ይፋዊ ላለማድረግ ነው። አሁን ደግሞ አዲስ የተኃድሶ ዜማ ከች ብሏል። የአብይዝም ብልፅግና ፀረ ኦሮሙማ እንደሆነ ተደርጎ እዬተቀነቀነ ነው። ማዘናጊያው ለደጉ የአማራ ማህበረሰብ ነው። ገዳ ወረራ ነው። ገዳ መስፋፋት ነው። ገዳ ጭካኔ ነው። ገዳ ማስገበር ነው። ገዳ ባርነት ነው። መገበር ለፈለገ፣ ባርነት ላሰኜው፣ ሎሌነት ሽው ላለው መንገዱን ጨርቅ ያድርግለት። የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ህዝብ ሎሌም፣ ገባሪም፣ አሽከርም ሆኖ አያውቅም። ባርነት ሳይሆን ክብራችን የነፃነት ዓርማነታችን ሉላዊ ነው። ይህ ሉላዊነት በወጋ ወግ የተገኜ አይደለም። በተራ ነጋ ጠባ የማይክ ክሽፈት ስብከትም አይደለም። በጠንካራ የመስዋዕትነት ገድል የከበረ ነው። ለዚህ የገድል ክብር አማራም እንደ ማህበረሰብ ቤተኛ ነው። ስለሆነም የአቶ ለማ መገርሳ ዴሞግራፊ የዶር አብይ አህመድም ትልም ነው። ኦሮሙማ ግቡ አፍሪካዊነትን መበወዝ ነው። ለዚህም የሚዲያ ተጋድሎው ተጀምሯል። የዲፕሎማሲውም አሁን አሁን ተፍረክርኮ ዕዳው ለሁሉም ሆነ እንጂ ጉዞው ያ ነበር። በአሉታ ዴሞግራፊ ውስጥ ዕውነት፣ መርህ፣ ፍትህ፣ ሰላም፣ ነፃነት፣ ዴሞክራሲ የለም። ይህ የሰቀቀን ዳመና ሁለት ዓመት የተኖረበት ሲሆን ይህ እንዲቀጥል መፍቀድ መኖርን በቁሙ መግደ...