ኦሮምማ እና የአብይዝም ብልፅግና አንድ ናቸው።
ኦሮምማ እና የአብይዝም ብልፅግና አንድ ናቸው።
የሥም ልዩነት ካልሆነ በሰተቀር ሁለት ሳይሆን መንፈሱ አንድ ነው። መነሻውም መድረሻውም ገዳ ነው።
ፍኖተ ካርታ አያስፈልግም የሚሉት የገዳ ሰንድን ይፋዊ ላለማድረግ ነው። አሁን ደግሞ አዲስ የተኃድሶ ዜማ ከች ብሏል። የአብይዝም ብልፅግና ፀረ ኦሮሙማ እንደሆነ ተደርጎ እዬተቀነቀነ ነው። ማዘናጊያው ለደጉ የአማራ ማህበረሰብ ነው።
ገዳ ወረራ ነው። ገዳ መስፋፋት ነው። ገዳ ጭካኔ ነው። ገዳ ማስገበር ነው። ገዳ ባርነት ነው። መገበር ለፈለገ፣ ባርነት ላሰኜው፣ ሎሌነት ሽው ላለው መንገዱን ጨርቅ ያድርግለት።
የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ህዝብ ሎሌም፣ ገባሪም፣ አሽከርም ሆኖ አያውቅም። ባርነት ሳይሆን ክብራችን የነፃነት ዓርማነታችን ሉላዊ ነው።
ይህ ሉላዊነት በወጋ ወግ የተገኜ አይደለም። በተራ ነጋ ጠባ የማይክ ክሽፈት ስብከትም አይደለም። በጠንካራ የመስዋዕትነት ገድል የከበረ ነው። ለዚህ የገድል ክብር አማራም እንደ ማህበረሰብ ቤተኛ ነው።
ስለሆነም የአቶ ለማ መገርሳ ዴሞግራፊ የዶር አብይ አህመድም ትልም ነው። ኦሮሙማ ግቡ አፍሪካዊነትን መበወዝ ነው። ለዚህም የሚዲያ ተጋድሎው ተጀምሯል። የዲፕሎማሲውም አሁን አሁን ተፍረክርኮ ዕዳው ለሁሉም ሆነ እንጂ ጉዞው ያ ነበር።
በአሉታ ዴሞግራፊ ውስጥ ዕውነት፣ መርህ፣ ፍትህ፣ ሰላም፣ ነፃነት፣ ዴሞክራሲ የለም። ይህ የሰቀቀን ዳመና ሁለት ዓመት የተኖረበት ሲሆን ይህ እንዲቀጥል መፍቀድ መኖርን በቁሙ መግደል ነው።
በአንደበታቸው ዶር አብይ አህመድ ሲናገሩ ያላፈሩበትን በትርጉም ለማቃናት ማሰብ ጤነኝነት አይመስለኝም።
"ብልፅግና የማን ነው ብለው ይጠይቁናል። ብልፅግና የኦሮሞ ነው እንላቸዋለን። መደመር ከገዳ ሥርዓት የተቀዳ ነው። ብልፅግና የሚለው ሥም እራሱ የመጣው ከኦሮሞ ነው" ይህን አላፈሩበትም። ደረታቸውን ነፍተው ነግረውናል።
ሌላም ተባራሪ ታጋች ኢትዮጵያዊ ዜጋ እንዳለም ነግረውናል። አባራሪ እና አጋች ማን እንደሆን ስለነገሩ አስተርጓሚም ፕሮፖጋንዲስትም አያስፈልገንም።
ሌላው የዶር አብይ አህመድ ኢትዮጵያዊነት ነው። ኢትዮጵያዊነታቸውን የካደ የለም። ለዚህ ሁሉ ክብር ያበቃ ከጠባቂነት አውጥቶ ኢትዮጵያዊነት ነው።
በኢትዮጵያዊነት ፀጋ፣ ትሩፋት፣ ዕሴት፣ ታሪካዊ አቅም፣ ጥበባዊ ክህሎት ግን እሳቸውን ያልሰሩት ስለሆነ ድብን ብለው ይቀናሉ።
የሳቸው ትናት የተፈጠረ ስልምልም የጨረቃው ቤት ብልፅግና የሺህ ዓመት የዕሴት ድርብ ታሪክ እዬተፈታተነው ነው። ስለ የንጉሦች ንጉሥ አጤ ሚኒልክ እድሳት ብዙ መወድስ እሰማለሁ። ምን እንደተነሳ አናውቅም። ብዙ ሸፍጥ አለበት። ብዙ ንብርብር ሴራ አለበት።
የቅርስ ጉዳይ የሚመለከተውን ባለሥልጣን እንኳን አላማከሩም። የቢሮው ኃላፊ ጥያቄ ሲያነሱ አቶ ዮናስ ደስታን በቀላጤ ደብዳቤ ነው ያነሷቸው።
ክህሎታቸውን፣ ልቅናቸውን ያውቁታል። እንደሚበልጧቸውም አስቀድመው ተረድተዋል። ክህሎታዊ አመክኖያዊ በሆነ ሁኔታም ሞግተው እንደማያሸንፏቸው ያውቃሉ።
ዶር አብይ አህመድ ከተሾሙ ጀምሮ በቅብ ያረገደ የበቀል ተግባር በሁሉም ዘርፍ እዬከወኑ ነው። ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አገር ናት አሉ ነገር ግን አገር አልባ እያደረጓት ነው። መክሊቷን፣ ትውፊቷን፣ ማንነቷን እዬሸራረፋ እዬተዳፈሩት ነው። እርሰ መዲናዋንም ነፍገዋታል።
ያልገባው ብዙ ሰው አዲስ አበባ ለኦሮሙማ መሰጠቷ ነው። ሰነዳዊ አይደለም። ዕውነታዊ የሆነው ነገር አዲስ አበባ የምትተዳደረው በክልል ኦሮምያ ነው።
ብሄራዊ፣ ሉላዊ፣ አህጉራዊ የሆኑ ጉዳዮች ሁሉ በዚህ ክልል ሥር ናቸው። ዛሬ አይገለጥም የአብይዝም ብልፅግና ከቀጠለ ግን ነገ ይፋዊ ሆኖ ታዩታላችሁ።
ሌላው በፍርድ ቤት ሊከሰሱበት የሚገባ ጉዳይ በኢትዮጵያ አንጡራ ሃብት ተምረው፣ ተሹመው፣ ግን ኢትዮጵያን ሲሰልሉ፣ ለአማፅያን መረጃ ሲያቀብሉ የነበሩ ስለመሆናቸው ሐረር ላይ ነግረውናል። እና ይህ የአገር ክህደት ወንጀል ይሆን ምርጥ ኢትዮጵያዊ የሚያደርጋቸውን?
እሳቸውም ኦሮሞ ፈርስት ናቸው። አቶ ለማ መገርሳ ካህዲ ዶር አብይ ታማኝ ተደርገው የሚወሰዱበት ምክንያት አይገባኝም። እንዲገባኝም አልፈቅድም።
በቃላቸው ፀንተው አያውቁም። ሰብዕናቸው ውሸት ነው። ያሉትን እንደካዱ ውለው ያድራሉ። ለማንም ለምንም ታማኝ አይደሉም። ስለ ኢትዮጵያ ባለውለታዎችም ደንታ አይሰጣቸውም። ስለህዝቡም።
አንድ መቶ ሺህ ሰው በቀን እገላለሁ ያለ ነፍስ እንደሰው ማዬቱ በእግዚአብሄር ፊት ያስጠይቃል። ከዚህ ሲኦል መንፈስ ቅድስናም እርህርህናም የለም። ያለው እርኩሰት እና የመቃብር ሥፍራ ብቻ ነው።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
30.04.2020
መርኽን እንደግፍ እባካችሁን?
የተልባ ሥፍርም አንሁን እባካችሁን?
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ