#አሳቻው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የተዋህዶን ዶግማን ለመዘንቆል አድብተዋል አሉ።

 

#አሳቻው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የተዋህዶን ዶግማን ለመዘንቆል አድብተዋል አሉ።

"የቤትህ ቅናት በላኝ"

 No photo description available.

በህይወት ዙሪያ ያሉ የሳይንቲስት፣ የፍልስፍና ዘርፎች እሳቸው ያልዳከሩበት አይገኝም። ድርብርብ የትምህርት ማዕረግ ያገኙትን ሁሉ ቁጭ አድርገው ሲያስተምሩ ቅጭጭ አይላቸውም። እኔ አውቃለሁ፣ እበልጣለሁ ብለው ሲቀናጡ እናያለን። ምን ቸገረን መላዕክ ነኝስ ቢሉ።

በፓርቲ አደረጃጀት፣ አመራር በስማ በለው ተነሳስተው በፋንታዚ ምን ያህል እዬዳከሩ እንደሆንም እናስተውላለን። ነገ ብትንትኑ ወጥቶ ይፈርሳል። መሠረት የለውም። መርህ የለውም። የሚመራ ዲስፕሊን የለውም።

የሆነ ሆኖ በገዳቸው ዙሪያ ያሻቸውን ባሻቸው ሰዓት ቢያደርጉ ከልካይ የለባቸውም። "በብልጽግና" ወንጌላቻውም ይተርትሩት፣ ይሸንትሩት፣ ይዘክትሉት አይመለከተነም። በእስልምናም ቢሆን #ባለቤት ስላለው አያገባንም።

በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምድር እና ሰማይን በሚያገናኘው ረቂቅ የመንፈስ ቅዱስ እዮራዊ ዶግማ ሚስጢር፣ ዕድምታ፣ ቅኔ፣ ተደሞ ግን ገብተው እንዲያነኩሩ ሊፈቀድላቸው አይገባም። ፈጽሞ! ፈፅሞ! ሃግ ሊባሉ ይገባል። ልካቸውን ይወቁ። ሲበዛ ይገለማል #ይጎፈንናልም

ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለሳቸው ልካቸው አይደለችም። በምንም መስፈርት የቅድስት ኦርቶዶክስ አቨውን ሰብስበው የማሰልጠን ሞራሉም፣ ክህሎቱም፣ አቅሙም፣ #ቅባውም ችሎታውም፣ ፀጋውም፣ ተስጥዖውም የላቸውም።

"ማድ ብናጣ አብረን ቆረስን" ካልሆነ በስተቀር። "ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል" ይላሉ ባለ ቅኔወቹ ጎንደሮች እሳቸው "ሸኔ" ያሏቸው #አቅፈው እዬተኙ።

ድፍረታቸው፣ ዓይን ዓውጣነታቸው ይገርማል። አይሸማቀቁም። እጅግ ይገርማል። ቅድስት ተዋህዶ አርቲፊሻል የዕምነት የኩሬ ውኃ መሰለቻቸውን? ቅድስት ተዋህዶ የሾላ ዛፍ መሰለቻቸውን?

ቅድስት ተዋህዶ የጓሯቸው ቆስጣ እና ሰላጣ መሰላቸው? ቅድስት ተዋህዶ ሜካፕ እና ማይክ መሰላቸውን? ቅድስት ተዋህዶ የፒኮክ ሙሽራ መሰለቻቸው? ይገለማሉ ይጎለምማሉ። ሁሉ ቦታ ማነኮር። ሁሉ ቦታ መዳከር።

ቅድስት ተዋህዶ እኮ እጅግ #ጥልቅ እና #ምጥቅ ተመራምረው የማይደርሱባት ርቁቅ ሚስጢር ናት። ሰው ሰራሽ አይደለችም። ጥበቃዋም ልቅናዋም ዩንቨርስ ነው። የአውሮፓ ስልጣኔ መሠረት እኮ እሷው ናት። ዕድሜ ልካቸውን የሚያልሟት።

የሰው ልጅ አፈጣጠር በአምላክ ሥራ ይመረመራልን? ይቻላልን? አይቻልም። ሰውን የሠራ ሳይንቲስት ፈላስፋ አለን? ቅድስት ተዋህዶም እንደዛው ናት።

እንደ እሳቸው ዓዬነት የፋንታዚ አውራ፣ ከእሳት ከውኃ ዬሚል ላልሰከነ፣ አብዝቶ ለሚቁነጠነጥ፣ አደብ ለነሳው፣ ጤዛ መንፈስ እሳት ናት እናታችን። እሳት ናት ቋያ። ባይዳፈሯት ጥሩ ነው። እሳቸው ለእሷ ሊያስተምሩ? እሷን ሊያሰለጥኑ? እንዴት ተቀለደ? ሰው ጠፋ? ምን ይሁን።

የሆነ ሆኖ ድፍረታቸውን #በልክ ያድርጉት። እንደ የኔታ ዲያቆን አባይነህ ካሴ የትናንት ፕሮግራም ገለፃ #የተመረጡ ምልምል የቤተ - እግዚአብሔር ሰወች ለሥልጠና ታጭተዋል አሉ። ዝርዝሩ ደርሶኛል ብለዋል። አብዛኞቹ የዞጋቸው እንደሚሆኑ አስባለሁኝ። በሽታው አዞ ተሰንቅሮ ያለው ከዛ ላይ ነው።

በውነቱ ከብልጽግና ወንጌል ፓስተር ሥር ሄዶ ጥምቀተ ሞጋሳን መውሰድ ይህ ወራዳነት ብቻ ሳይሆን #ውርዴም ነው።

ከእሳቸው ሥር ወድቃ ቅድሥታችን ወንጌል ልትማር?

የኔታችን #ጥበብ ልትቀስም?

#መሆን ልትገበይ?

በምን አቅም እና ወርድ?

በምንስ ቁመና?

እጃቸው መንፈሳቸው ከደም #ንፁህ ነውን? #ጲላጦስ!

አገር መምራቱን በቻሉበት። ክልላቸውን መምራት ተስኗቸው ነው ቀውስ ጠንስሰው ቀውስ ሲዘልሉ ውለው የሚያድሩት። የሰው ሊኳንዳ ቤት ከፍተው ፓርክ ሲመርቁ ይውላሉ።

አመድ ከምረው ቆስጣ ሲያስጎበኙ ይገኛሉ። አቅም ቢኖር ክልላቸውን በመሩ። አንድ ቀን #መሰብሰብ አልቻሉም ክልላቸውን። ፈፅሞ።

#ትቅማጥ እንደ ያዘው ሰው አሁንም ቅድምም የሚመላለሱት አማራ ክልል ብቻ ነው። እዛማ ማን ያስገባል። ማን ድርሽ ያደርጋል?

ሙታን በቤተ መንግሥት ቀብራቸው ሲፈፀም እናያለን።

ከሳቸው ሥር ወድቆ መማር ከሞት ሞት ነው። የቁም ሞት። "አሟሟቴን አሳምረው" ትል ነበር እሚታዬ ጽግሽ። አብሮ ረክሶ መስመጥ። አበስኩ ገበርኩኝ።

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

30/04/2022

ከሞትም ለካ የክብር ሞትም አለ።

ፈጣሪ ለክብር ሞት ያብቃን። አሜን።

Formularbeginn

 

Formularende

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።