ያረጠው 50በ60 የአብይዝም ነፍስ ማሰንበቻ የመርዶ ትልም። 29.04.2020
ያረጠው 50በ60 የአብይዝም ነፍስ ማሰንበቻ የመርዶ ትልም።
ኮሮና ደልቶታል ያረጠው የ50በ60 የመቃብር ሥፍራው የኦሮሙማ ፖለቲካ። ባለፋት ቀናት ኢትዮ 360 ይህው መንፈስ ስልጣኑን ለማራዘም በድብቅ የጨረቃ ቤቱን የኦነጋዊውን ብልፅግና ሥራ አስፈፃሚውን በድብቅ እንደ ሰበሰበ ተደምጧል።
አሁን በትናንቱ የዛሬ ምን አለ የኢትዮ 360 ውይይትም ቀጣይ ስብሰባዎች የተወካዮች ምክር ቤት፣ ከሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ስብሰባ እንደሚኖርም ተጠቁሟል።
በሌላ በኩልም ከተደማሪው አውራ ሥጋጃ አንጣፊያን፣ እንዲሁም ከወሮ ማዕዛ አሸናፊ ጋርም ንግግሩ መቀጠሉ ተደምጧል። ድርጅታዊ ሥራ መሆኑ ነው። በህግ የተደገፈ የሥልጣን ማራዘሚያ ቀዳዳ ለማግኜት ጥረቱ በሁሉም መስክ ቀጥሏል። ከዛ የማህበራዊ ሚዲያ ሰራዊት ይለቀቃል።
የሆነ ሆኖ የህግ አግባቡን በሚመለከት ለህግ ባለሙያዎች ትቼ የዚህ ጨካኝ፣ ኢሰባአዊ፣ እርህርህና ያልሰራለት፣ በሰው ልጅ ሰቆቃ የሚሳለቅ፣ ተውኔት የሚሠራ የመቃብር ሥፍራ የሥልጣን ዘመን መራዘም መርዶ ነው ለኢትዮጵያ ህዝብ።
መራራ ነው። እጅግ ጎምዛዛ።
ሁለት ዓመት ሙሉ ዕንባ የተዘከረበት፣ ሰኔል እና ቹቻ የደላቸው አፈር ዘመን ነበር። መፈናቀሉ መስቃው፣ የጀምላ እረሸናው፣ አሰቃቂ ግድያው፣ መታገቱ፣ ጭንቀቱ፣ ስጋቱ፣ ማላገጡ ልክ አይወጣለትም። የተረገመ ወቅት ነበር።
ውሸቱ፣ ማስመሰሉ፣ ማጭበርበሩ፣ ዘረፋው፣ አድሎው፣ መገለሉ፣ መከፋቱ ዲስክርምኔሽኑ፣ ልክ አይወጣለትም። ይህ ሲኦል ሥርዓት ባነሰ ለአንድ ዓመት ሆነ ለሁለት ሦስት ዓመት ይቀጥል ብሎ ማሰቡ እራሱ ይሰቀጥጣል።
እዬከሰሙ፣ እዬተገደሉ፣ እዬጤሱ፣ እዬነደዱ፣ እዬተናዱ፣ እዬፈረሱ፣ እዬተወረሩ፣ እዬታሰሩ፣ እዬተንገላቱ ቀጥሉ መባል ቀራኒዮ ነው። በሃይማኖት ዘርፍ ይህ ሥርዓት ከቀጠለ ወዮልሽ ተዋህዶ ነው።
መንፈሱ እራሱ ሰውኛ አይደለም። በባህሬው ተጫኝ፣ ትዕቢተኛ እና በአንድ ጨካኝ ሰው ህሊና ብቻ ታጥሮ መከራ የተሰነቀበት ነው።
የታለፈው ጊዜ ስለሰው ልጅ ሰባዕዊ መብት ግድ ለሚለው ነፍስ ለአንድ ቀን ቀርቶ ለአንድ ሰዓት መንፈሳችን ወህ ያላለበት የሃዘን ወቅት ነበር።
አንዲት አሊ የማትባለው ሚዲያ ላይ ያለችው ብልጭ ድርግም የምትለው መብት ብቻ ናት። እሱም የጊዜ ጉዳይ ነው። ይወረራል በሞጋሳውያን።
ሁሉን ነገር በጥቅማ ጥቅም ጠርንፎ አንደበቶችን ዘጋግቶ በቂም እና በበቀል ኢትዮጵያን ኦሮማይዝድ ለማድረግ አረመኔያዊ እርምጃዎችን እዬወሰደ ያለ እጅግ ክፋ ጨለማ ሥርዓት ነው ያለው። ለአንድ ወርም ዕድል ሊሰጠው የማይገባ አሻሮ ሥርዓት። የአመራር ክህሎትም ቅብዕም የሌለው ፍግፍግ። ስለሆነም በቃህ ሊባልም ይገባል።
እርግጥ ነው አውራው ተደማሪ ሃሳበ ቢስ ስለሆነ፣ በእጁ አለኝ የሚለው ማህበራዊ መሰረት ስሌለው፣ የአዲስ ሃሳብ ደሃም ስለሆነ እልል ብሎ እንደሚቀበለው ውሳኔውን ይታወቃል።
እንደ ኢትዮ 360 ጥቆማ ከሆነ ማህበረ ድንኳን ሰባሪ መግለጫም ሊያወጡ እንደሚችል ተተንብዮዋል። ድሮም አዬር ላይ እዬተነ ነበር ዛሬም እንዲሁ። ሌላው የመግለጫ ትርዒት በግርባው ብአዴን እና በመሰሎቹ ቀጣይ ይሆናል።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
29.04.2020
ፈጣሪ ሆይ በጥበብህ ማህበረ ደራጎንን አትንንልን።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ