ልጥፎች

ቋንቋን የቻለ ሁሉ የአንድ አገር ፖሊሲን መተርጎም ይችላልን?

ምስል
  # ቋንቋን የቻለ ሁሉ የአንድ አገር ፖሊሲን መተርጎም ይችላልን ?   " እኔ ችግረኛ እና ምስኪን ነኝ፦ ጌታ ግን ያስበኛል፥ አንተ ረዳቴ እና መዳህኒቴ ነህ፤ አምላኬ ሆይ አትዘገይ። " ( መዝሙረ ዳዊትምዕራፍ ፴፱ ቁጥር ፲፮ )     ከ ሰሞኑ ዘለግ ያለ የፖለቲካ ሃሳቦችን የያዘ የአሜሪካ አቋም በአንባሳደሩ አማክኝነት ተገልጧል። እንግሊዘኛ ቋንቋ የቻለ ሁሉ እፍታውን በጥድፊያ በራሱ የፖለቲካ ዝንባሌ ተንትኖታል። አንደኛ ችኮላው ገርሞኛል። ሁለተኛው ሁሉም ተንታኝ ሆኖ መቅረቡ አስደንቆኛል። ዲፕሎሚሲያዊ ጉዳዮች ተደሞን፤ አንክሮን አብዝተው ይሻሉ።   # ተዚህ ላይ ወግ ቢጤ እምር አለኝ።   እኔ በአማርኛ ቋንቋ ከ 7 ዓመቴ ጀምሮ ክትትሉ አለኝ። ትጋቱም እንዲሁ።   # ምክንያት ።   ወላጅ አባቴ አቨይ መምህር እና የቤተ መፀሐፍት ኃላፊ ስለነበር፤ ለእኔም ልዩ የህሊና እንክብካቤ ያደርግ ስለነበር አማርኛ ቋንቋን የኦክስጅን ያህል ሰውነቴ ይጠቀምበታል። እናላችሁ ከሁለት ሳምንት በፊት የቅኔውን ልዑል የብላቴ ሎሬት ፀጋዬ ገ / መድህን ራዲዮ በሲዊዘርላንድ ዙሪክ ከተማ አለኝ። በወር ሁለት ጊዜ በዕለተ ሃሙስ ከ 15.00- 16.00 ሰዓት በአማርኛ ቋንቋ በበዛ ጥንቃቄ እና ጥራት ለ 16 ዓመት እዬሠራሁ ስላለ በቀጣይ የብላቴውን የሎሬት ግጥም ሙሉ ፕሮግራም ልሥራበት ብዬ ጀመርኩላችሁ።   ዕውነት ልንገራችሁ አማርኛ # ቋንቋዬን ...