ልጥፎች

መልካም ዕድል #ለእምዬ ለሲዊዝ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን። #የሰላም #ንግሥቷ። #Viel Erfolg.

ምስል
  መልካም ዕድል #ለእምዬ ለሲዊዝ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን። #Viel Erfolg.   "የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፥ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።"   (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)         ዕለተ ቅዳሜ ልክ 18.00 ሰዓት #የእምዬ ሲዊዝ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን ከአቻው የእንግሊዙ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን ጋር በጀርመን በዶርትሙንድ ሲቲዲዮም ወሳኝ ግጥሚያ አላቸው።   ትናንት ባዬነው ጨዋታ ስፔን ጀርመንን በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ፤ ፈረንሳይ ፖርቹጋልን በተጨማሪ ጊዜ፤ በዛም መሸናነፍ አልችል ብለው በፔናሊቲ ዳኝነት ፈረንሳይ ለቀጣዩ ፍልሚያ እንደ ስፔን አልፈዋል።    ለጀርመን የእግር ኳስ ጨዋታ ማለት #አገር ማለት ነው። #ትውልድ ማለት ነው። እንደ አስተናጋጅ አገር ጀርመኖች ቀጥለው ቢሆን የጨዋታው አትሞስፌር ልዩ ይሆን ነበር። ለመጨረሻ ጊዜ ሊሆን ይችላል ብዬ የማስበው የዕውቁ ተጫዋቻቸው የቶኒ ስንብትም ቢያንስ ለፋይናል ደርሰው ቢሆን ምኞቴ ነበር። ዕውነት ለመናገር ልቤ ተንጠልጥሎ ነበር የተከታተልኩት። መራር ስንብት። ለፔናሊቲ ደርሰው ቢሆን ምን አልባት ሊቀናቸው ይችል ነበር።    በጨዋታው ላይ ከፍ ያለ ተጽዕኖም ያሳድራል። ጀርመኖች ብዙ ተፋልመዋል። የመጀመሪያ ጎል ስትገባባቸው ደነገጥኩ። ጥንካሬያቸው በቀጣይነት አሳሳቢ ስለሆነ በባህሬው። የሆነ ሆኖ የጀርመን ብሄራዊ ቡድን የሌለበት ጨዋታ ቀዝቀዝም፤ ለብም ብሎ በአገረ ጀርመን ይቀጥላል። ፖርቸጋልም ለፔፔ የመጨረሻው ይመስለኛል ለአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ። መራራ ስንብት።    ለሲዊዝ ጨዋታው #ተራዝሞ #ከፔናሊቲ ከተደረስ #ስጋቴ ከፍ ያለ ነው። እግዚአብሄር አምልክ ስንት...

የሰባዕዊነት #ሐዋርያዊት ቅድስት አገር #ሲዊዘርላንድ።

ምስል

#ፈለገ ሰላማዊቷ - ሲዊዝሻ። ቅን ነሽ እና ይቅናሽ። አሜን። #መልካም #ዕድል ልባሟ ሲዊዝሻ። አሜን።

ምስል
  Viel Erfolg. Ich hoofe es. Stolz. #ፈለገ ሰላማዊቷ - ሲዊዝሻ። ቅን ነሽ እና ይቅናሽ። አሜን።     ነገ 06.07.2024 በጀርመን ዶርቱሙንድ ላይ ሲዊዚሻ ወሳኝ ጨዋታ ልክ 18.00 #ከእንግሊዝ ጋር ግጥሚያ ይኖራታል። መልካሙን ሁሉ ለቅድስት አገር ሲዊዘርላንድ ዲስፕሊንድ ለሆነው የእግር ኳስ ቲም እመኛለሁኝ።    እርግጥ ስጋት አለኝ። ጨዋታው #ከተራዘመ ፤ በተራዘመው የጨዋታው ክፍለ ጊዜ ግብ ማስቆጠር ካልተቻለ #ፔናሊቲ መለያው ከሆነ ስጋቴ ከፍ ያለ ነው። የእንግሊዝ ቲም በጥሎ ማለፋ ጨዋታ የአጨዋወት አርቱ ፈፅሞ አልገባኝም ነበር። ይህም ሆኖ እግዚአብሄር አድሎት ለነገው ፍልሚያ ከሲዊዚሽ ጋር ደርሶታል።    ለቅኒት ሲዊዝርላንድ ከስንት ጊዜ #ትዕግሥታዊ #ጥበቃ በኋላ የተገኜ #ዕንቁ ዕድል ነው። ሲዊዝ ለሰው ልጆች ሁሉ የምታበረክተው ታላቁ ስጦታ #የሰላም ፍለጋ መንፈሳዊ ብቃት ለዓለማችን ሰፊውን ድርሻ የያዘ የጎላ ሚናም ነው።    ዛሬ ዓለም በሚታመስበት የጦርነት ስጋት ውስጥ የበዛ #ቁጥብነቷ ለግሎባሉ ትውልድ ታላቅ ተቋም ነው ብዬ አስባለሁ። ቅድስት አገር ሲዊዝ ውስጥ የጥይት ድምጽ የማይሰማበት ምድራዊ #ገነት ነው ብል ማጋነን አይሆንም። የጥይት ድምጽ ሰምቼ አላውቅም።   ሌላው ቀርቶ በአዘቦት ቀን ፀጥታው ይደንቃል። እኔ ከቤቴ ውስጥ ሆኜ ነው ራዲዮ ፕሮግራሜን እማሰናዳው፤ አውዲዮም ለዩቱብ ቻናሌ የምሠራው። የምኖርበት አፓርትመንት ውስጥ ጎረቤቶች አሉኝ። #ልጆች አሉ። በአቅራቢዬ ኮሌጅ አለ። ግን #ፀጥ - #ረጭ ያለ ነው።    አንዳንድ ቀን የክሪስመስ ዋዜማ ምሽት ይመስል ፀጥታው #በግርማ መንፈስን ይገዛል። እኔ ፀጥታ ነ...

የመንግሥት ኃይሎች በአማራ ክልል የጤና ተቋማት እና ባለሙያዎች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል፡ሂዩማን ራይትስ ዋች

ምስል
  "የመንግሥት ኃይሎች በአማራ ክልል የጤና ተቋማት እና ባለሙያዎች ላይ ጥቃት ፈጽመ ዋል፡ሂዩማን ራይትስ ዋች" የፎቶው ባለመብት, Amhara Health Bureau ከ 8 ሰአት በፊት የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሎች በአማራ ክልል ከጦር ወንጀል ጋር የሚስተካከሉ መጠነ ሰፊ ጥቃቶችን በጤና ባለሙያዎች፣ በህሙማን እና በጤና ተቋማት ላይ ፈጽመዋል ሲል የመብት ተሟጋቹ ሂማን ራይትስ ዋች ከሰሰ።   https://www.bbc.com/amharic/articles/c97832pz01mo "የመንግሥት ኃይሎች በአማራ ክልል የጤና ተቋማት እና ባለሙያዎች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል፡ሂዩማን ራይትስ ዋች ታማሚ እና አስታማሚ"   የፎቶው ባለመብት, Amhara Health Bureau ከ 8 ሰአት በፊት   "የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሎች በአማራ ክልል ከጦር ወንጀል ጋር የሚስተካከሉ መጠነ ሰፊ ጥቃቶችን በጤና ባለሙያዎች፣ በህሙማን እና በጤና ተቋማት ላይ ፈጽመዋል ሲል የመብት ተሟጋቹ ሂማን ራይትስ ዋች ከሰሰ።   አንድ ዓመት ሊሞላው በተቃረበው በአማራ ክልል በፌደራሉ መንግሥት ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል እየተካሄደ ባለው ግጭት፣ የመንግሥቱ ኃይሎች እና ተባባሪ ሚሊሻዎች በክልሉ የጤና ተቋማት ላይ ፈጽመዋቸዋል ያላቸውን ጥቃቶች በተመለከተ ሂዩማን ራይትስ ዋች ዝርዝር ሪፖርት አውጥቷል።   ሪፖርቱ በክልሉ ግጭቱ ከተቀሰቀሰበት ካለፈው ዓመት ማብቂያ አንስቶ የመንግሥት ኃይሎች ቢያንስ 13 በሚደርሱ ከተሞች በጤና ተቋማት እና በሠራተኞች እንዲሁም በትራንስፖርት አገልግሎቶች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን የሚያመለክቱ መረጃዎችን ማሰባሰቡን አመልክቷል።   የሂማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ላቲሺያ ባድር “የኢትዮጵያ ፌደራል ኃይሎች ለሰላማዊ ...

የሰባዕዊነት #ሐዋርያዊት ቅድስት አገር #ሲዊዘርላንድ።

ምስል
  የሰባዕዊነት #ሐዋርያዊት ቅድስት አገር #ሲዊዘርላንድ ።   "አድርገኽልኛል እና አመሰግንኃለሁ። "       እንደ አገር አስተዋይ አገር ብርክታዊቷ ሲዊዘርላንድ። እንደ ሕዝብም አስተዋይ ህዝብ ሲዊዛውያን። በብዙ አጋጣሚወች ብዙ ሲዊዛውያንን አግኝቻለሁ፤ የማድመጥ አቅማቸው፤ ልታይ ልታይ አለማለታቸው፤ ለሰው ልጅ ያላቸው ጥልቅ ፍቅር እና አክብሮት፤ ለመርዳት ያላቸው ፍጥነት፤ ለውሳኔ ቁጥብነታቸው ይገርማል። ይደንቃል። ያስተምራል።    አንዱ ወይንም አንዷ ሲዊዛዊት በራሳቸው የትምህርት ተቋማት ናቸው። እንደ እኔ ሲዊዞች በተፈጥሯቸው ፖዘቲብ ቲንከር ናቸው። ካቀረቡ ከውስጣቸው፤ ሲለዩም በነበረው የፍቅር ደረጃን ሳያጓድሉ፤ ሳያስተጓጉሉ ነው። ሁልጊዜ በሚገጥሙኝ ዕድሎች ሁሉ ተምሬባቸዋለሁ። ልዩ ናቸው እና።    መፃህፍት ሦስቱን በአንድ ላይ አሳተምኩኝ። ቤቴ አራተኛ ፎቅ ላይ ነው። መፃህፍቶችን በእሷ መኪና ጭነን አምጥተን ተሸክመን አመላልሰን ቤት አስገባነው። ጓደኛዬ ሲዊዛዊ የህክምና ዶር ናት። ይህ ትህትና፤ ይህ ታዛዥነት ለአንዲት ስደተኛ #ማንም ፤ #ምንም ለሌላት ባተሌ። ከጨረስን በኋላ ምን ነክቶን ነው ግን አጋዥ ሰው እኮ መቅጠር እንችል ነበር አለች እና ጅልነታችን ያስቃል አለች። ሌላ ጊዜ ደግሞ የገዛሁት እና የመጣልኝ ዕቃ ትክክል አልሆን አለ። ክርክሩ በሙያ እንዲታገዝ አማካሪዬ ከቦታው ድረስ አብረውኝ ሄደው ከእኔ ጋር ሞገቱል። ሌላም ሌላም ነገር ማንሳት እችላለሁ። የትም ሄጄ #ተከፍቼ እምመጣበት ሁኔታ የለም።    ጭምት - ቅን፤ ሰባዕዊ - ተፈጥሯዊ፤ አጽናኝ - ደግ፤ ሥልጡን - ሩህሩህ፤ ትጉህ - ታጋሽ፤ ድንቅ - ውብ፤ ፈርኃ እግዚአብሄር የሰከነባት፤ ዲሞክራሲ ...

እንኳን ደስ አለሽ ቅድስቴ ሲዊዚሻ።

ምስል
  እንኳን ደስ አለሽ ቅድስቴ ሲዊዚሻ። የሲዊዝ ድንቆች በውብ ትዕይንት በበርሊን ስታዲዮ #ኢጣሊያንን 2 - ለ0 በሆነ ውጤት ለቀጣይ ዙር ጨዋታ የመጀመሪያው ቲም ሆነዋል። ጨዋታቸው እጅግ ውብ፤ የተረጋጋ፤ ሥርዓት የነበረው ነበር። የሲዊዝ ቲም በአጨራረስ ላይ በነበረ ግድፈትብዙ #የግብ ዕድል አምልጧቸው ነው እንጂ ቢያንስ 4ቷን የማምጣት ዕድል ነበራቸው። ዛሬ ሲዊዞች ምንም ዓይነት ቢጫም፤ ማስጠንቀቂያም አልገጠማቸውም። በፍፁም የተረጋጋ መንፈስ ነበር የተጫወቱት። ጣሊያኖች #በሦስት ቢጫ #ዜሯቸውን ይዘው ይጓዛሉ። የጣሊያን ቡድን እጅግ ጠንካራ የነበረ ሲሆን ጉልበታቸው አሁንም አለ። ቢሆንም ግን ጉልበታቸው ለቀጣይ ጨዋታ አላሳለፋቸውም። እስከ 25 ደቂቃ ድረስ እንደ ኤክስፐርቶች አገላለጽ 65/% በሲዊዝ ቲም ቁጥጥር ሥር ነበረች እሜቴ ድንቡልቡል። ከረፍት በፊት የሲዊዘርላንድ ቲም በአንድ ግብ ለእረፍት ሲወጣ፤ ከረፍት መልስ በሰከንዶች ልዩነት ሁለተኛዋን ደገሙ እና የጣሊያን ቡድን ተስፋ ደመና አለበሱት። የዕለቱ ዳኛ ፍፁም የተረጋጉ ስለነበረ ለዲስፕሊን ጨዋታ ምቹ ነበሩ። ከእረፍት መልስ እሜቴ ድንቡልቡል 65% በሲዊዝ ቲም ሥር ነበረች። ዕውነት ለመናገር ጎል ጠባቂ ሶመር ብዙም ሥራ አልነበረበትም ማለት ይቻላል። የጣሊያን ቲም አመዛኙ ጊዜው በመከላከል፤ የሲዊዝ ቲም በማጥቃት እና በመከላከል ጥምር ቅልጥፍና ድፍረትም ታክሎበት በጥሩ ጨዋታ ለውጤት በቅቷል። የሲዊዝ የዕለቱ አሰላለፍ 3.4.3 ነበር ከጀርመን ጋር በነበረው ግጥሚያ አሰላለፋ የተለዬ ነበረ። ጀርመንን ሙሉ 90 ደቂቃ አንድ ለምንም የመራው የሲዊዝ ቲም በተጨማሪ ጊዜ ነበር ጀርመን አንድ ግብ በማስቆጠር ከምድቡ የመሪነቱን ቦታ ሳያስነካ ያጠናቀቀው። በዛ ጨዋታም የቅድስት አገር ሲዊዝ ቲም የጨዋታ ብልጫ...