ልጥፎች
ርግቦቼ። ያዬሁትን ላጋራችሁ።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ር ግቦቼ። ያዬሁትን ላጋራችሁ። "……… ርግብ ባሏ ከሞተ በኋላ ከሌሎች አዕዋፋት ጋር አትገናኝም። # በጥፍሯም # ምላስዋን # ትሰነጥቃለች ። ሌላ ወፍ ስንኳን ሊቀርባት ቢፈልግ በታላቅ ጩኽት ጓደኞቿን ጠርታ ሁሉም ተረዳድተው ይገድሉት የለምን ………" ( ድርሳነ ሚኬኤልና ሩፋኤል በግዕዝና በአማርኛ ዘሰኔ ምዕራፍ ፳፱ እና ፴ ገጽ ፼፸፱ ) ከመታደል በላይ ምን ይባላል። ታማኝነት፤ ፍፁም ታማኝነት ተማላ ያልሆነ፦ ምነው ለሰው ልጆች በሆነ። የእኔ ፯ኛ መጽሐፌ " #ርግብ #በር " ይላል። ደጉ ንጉሥ ከአነፁት ፋሲል ግንብ መግቢያ በሮች ውስጥ አንዱን ወስጄ ነው። ፀጋዬ ድህረ ገጽም መክሊት የሚለው ክፍል #ርግብ ከእነ ጎጆዋ ነበር። በሌላ በኩል በፀጋዬ ራዲዮ ለረጅም ጊዜ መግቢዬ ዬርግብ ድምጽ ነበር። ለምን ? ስለምን ብላችሁ አትጠይቁኝ። እኔም አላውቀውም እና። አሁን ከሆነ በምኖርበት ገዳማዊት ከተማ #ቪንተርቱር ርግብ በስፋት አያለሁ። ከዓመት በፊት ድርስ ምልስ ይሉ የነበሩ ርግቦች በእኛ ጣሪያ ነበሩ። ቋሚ መኖሪያቸው አላደረጉትም ነበር። አሁን ከሆነ ወደ እኔ ቤት ጎራ ማለት አዘወተሩ። ስድስት ወራት ይሆናቸዋል። በቋሚነት ያዘነ፤ የተከዘ ርግብ ብቻውን ለረጅም ጊዜ ነበር። ስለሚያሳዝነኝ የአጃ ክክ ገዝቼ መስኮቴ ላይ መመገብ ጀመርኩኝ። ከዛ በለታት አንድ ቀን #ጠፋብኝ ። የት አባቴ ልፈልገው ??? ሥም አውጥቼ #ቀለሜ እለዋለሁ። ሙሉ ግራጫ ነው። እግሩ እን...