ልጥፎች

"ጎንደርን እያራደ ያለው እገታ እና ግድያ ምክንያቱ ምንድን ነው? በማንስ ነው የሚፈፀመው? bbc"

 https://www.bbc.com/amharic/articles/crrl8pepgn8o   "ጎንደርን እያራደ ያለው እገታ እና ግድያ ምክንያቱ ምንድን ነው? በማንስ ነው የሚፈፀመው?   የኖላዊት እገታ እና ግድያ ነዋሪዎችን ያስቆጣ ሲሆን የጸጥታ ኃይሎች ሰልፈኞች ላይ በከፈቱት ተኩስ ቢያንስ አራት ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል። 6 መስከረም 2024, 07:05 EAT ለቤተሰቦቿ ብቸኛ ልጅ የሆነችው ኖላዊት ዘገዬ ከመኖሪያ ቤቷ ግቢ ውስጥ ታግታ የተወሰደችው ነሐሴ 24/2016 ዓ . ም ረፋድ 3 ፡ 30 ገደማ ነበር። ኖላዊት ታግታ እንደተወሰደች የታወቀው አጋቾች ወላጆቿ ተከራይተው በሚኖሩበት ግቢ ውስጥ የጣሉት ማስታወሻ ወረቀት ከተገኘ በኋላ ነው። ወረቀቱም “ እኛ አግተን ወስደናታል እስከምንደውልላችሁ ታገሱ ” የሚል ነበር። ክስተቱን ተከትሎ በግቢው ውስጥ የተሰባሰቡ ሰዎች ካልተበተኑ እንዲሁም ለፖሊስ ሪፖርት ካደረጋችሁ እንገላታለን የሚል ማስፈራሪያ ጽሑፍም ግቢው ውስጥ ተጥሎ እንደነበር ስለክስተቱ ለቢቢሲ ያስረዱ የቤተሰብ አባል ተናግረዋል። ከዚያም አጋቾቹ ሕጻኗን ለመልቀቅ አንድ ሚሊየን ብር ጠየቁ።ገንዘቡ ከታዳጊዋ ቤተሰብ አቅም በላይ መሆኑን በመግለጽ በተደረገ ድርድር 300 ሺህ ብር ለመክፈል ከአጋቾቹ ጋር ተስማሙ።ማሰባሰብ የተቻለው ገንዘብ ግን 200 ሺህ ብር ብቻ ነበር። አጋቾች የተሰበሰበውን ገንዘብ ቢወስዱም ታዳጊዋን ገድለው ከወላጆቿ መኖሪያ ቤት ጓሮ መጣላቸውን የቤተሰብ አባሉ አስረድተዋል። “ ምን አልባት 100 ሺህ ብር በመጉደሉ ይሆናል የ