ልጥፎች

በአፍሪካ ቀንድ ያለው ውጥረት ወደ ግጭት ያመራ ይሆን? ድርድሮችስ ውጤታማ ይሆናሉ? bbc

  https://www.bbc.com/amharic/articles/c7498yd93e7o በአፍሪካ ቀንድ ያለው ውጥረት ወደ ግጭት ያመራ ይሆን ? ድርድሮችስ ውጤታማ ይሆናሉ ?   19 መስከረም 2024 በአፍሪካ ቀንድ ያለው ውጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጋጋለ እየመጣ ነው። አንደኛው ውጥረት በኢትዮጵያ በሶማሊያ መካከል ያለው ነው። ሁለተኛው ደግሞ በግብፅ እና በኢትዮጵያ መካከል። በኢትዮጵያና በሶማሊያ መንግሥት ባለሥልጣናት መካከል እየተካሄደ ያለው የቃላት ጦርነት በተለይ ካለፉት ቅርብ ሳምንታት ወዲህ እየተባባሰ መጥቷል። ይህ ደግሞ ወደ ቀጥተኛ አሊያም የእጅ አዙር ግጭት ሊያመራ ይችላል የሚል ስጋት ጭሯል። ከሁሉም የላቀ አስጊ የሆነው ሶማሊያ በከተሙት የግብፅ እና የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች መካከል ግጭት እንዳይነሳ ነው። ሶማሊያ በአውሮፓውያኑ መስከረም 16/2024 ለምስራቅ አፍሪካ በይነ - መንግሥታት ድርጅት ( ኢጋድ ) በላከችው ደብዳቤ ድርጅቱ ጉዳዩን እንዲያሸማግል ጠይቃለች። ይህ ምናልባቱ ውጥረቱ ሊበርድ ይችላል የሚል ፍንጭ ሰጥቷል። እዚህ እንዴት ደረስን ? በአውሮፓውያኑ ነሃሴ 26 2024 ምሽት ሁለት አውሮፕላኖች የጦር ሠራዊት እና ወታደራዊ ቄሳቀሶች ጭነው የሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ አረፉ። በተመሳሳይ ሳምንት አንድ ገለልተኛ የሶማሊያ ድረ - ገፅ 1 ሺህ የግብፅ ወታደሮች ሶማሊያ መግባታቸውን እና ሁለቱ አገራት መስከረም ወር የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ለማድረግ ማቀዳቸውን አስነበበ። መስከረም 12/2024 የሶማሊያው ውጭ ጉ