ልጥፎች

«መርካቶ የኤስፔራንቶ የቋንቋ አገር» Merkato ist Afrikas größtes Einkaufszentrum. By ...

ምስል

"ኢትዮጵያ በኢንተርኔት ነፃነት ዝቅተኛ ነጥብ ማስመዝገቧ እና የመንግሥታት ቁጥጥር የደቀነው ስጋት bbc

  ·      "  ኢትዮጵያ በኢንተርኔት ነፃነት ዝቅተኛ ነጥብ ማስመዝገቧ እና የመንግሥታት ቁጥጥር የደቀነው ስጋት" https://www.bbc.com/amharic/articles/c0wwz5l2nvwo 17 ጥቅምት 2024 «በአፍሪካ የኢንተርኔት ነጻነት እየተሻሻለ ቢሆንም ኢትዮጵያ በግጭቶች እና በባለሥልጣናት እርምጃ ምክንያት በይነ መረብ ነጻ ያልሆነባት አገር መሆኗን ፍሪደም ሐውስ የተባለው የመብቶች ተቋም ያወጣው ሪፖርት አመለከተ። ተቋሙ በአውሮፓውያኑ 2024 የዓለም የኢንተርኔት ነጻነትን በተመለከተ ባወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያን ጨምሮ አስራ ሰባት የአፍሪካ አገራትን የነጻነት ይዞታን ያጠና ሲሆን፣ በዚህም ኢትዮጵያ ዝቅተኛውን ነጥብ አስመዝጋባለች። ጥናቱ ከአፍሪካ አገራት መካከል አንጎላ፣ ግብፅ፣ ኢትዮጵያ፣ ጋምቢያ፣ ጋና፣ ኬንያ፣ ሊቢያ፣ ማላዊ፣ ሞሮኮ፣ ናይጄሪያ፣ ሩዋንዳ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሱዳን፣ ቱኒዚያ፣ ኡጋንዳ፣ ዛምቢያ እና ዚምባብዌን የዳሰሰ ነው። በዚህም መሻሻሎች እንዳሉ የጠቀሰ ቢሆንም ኢትዮጵያን ጨምሮ በአንዳንድ አገራት የበይነ መረብ ነጻነት ተሸርሽሯል ብሏል። ጥናቱ የአገራቱን የኢንተርኔት ነጻነት ይዞታ በ 100 ነጥቦች የመዘነ ሲሆን፣ ዝቅተኛውን ወይም “ ነጻ ያልሆነ ” የሚል ደረጃን ያገኘችው ኢትዮጵያ 27 ነጥቦችን አግኝታለች። ደቡብ አፍሪካ ደግሞ ከፍተኛውን 74 ነጥብ በማግኘት የኢንተርኔት ነጻነት ያለባት አገር እንደሆነች ሪፖርቱ ጠቅሷል። ፍሪደም ሐውስ ካጠናቸው የአፍሪካ አገራት ...