#አሳቻው ዘመን #ከእኔ ምን ይጠይቃል??? መልስ። የጭካኔ መንፈስ ቤተኛ እንዳልሆን #እራሴን ማዳን። BBC "በሰሜን ሸዋ ደራ ስለ ተከሰተው እና ስለ አሰቃቂው ቪዲዮ እስካሁን የምናውቀው"
# አሳቻው ዘመን # ከእኔ ምን ይጠይቃል ??? መልስ። የጭካኔ መንፈስ ቤተኛ እንዳልሆን # እራሴን ማዳን። " የቤትህ ቅናት በላኝ። " ግን ደራወች በፋኖ ተደራጅተዋልን ? ከ 30 ዓመት በላይ ቀራኒዮ ስለሆነ ኑሯቸው። ኢትዮጵያ በአሳቸ ዘመን ላይ ትገኛለች ብዬ ወደ # አምስት ዓመት ጽፌያለሁኝ። መስቀለኛ ለሚሉት ፖለቲከኞች አይመቸኝም። አይደለም በዛች ቅድስት አገር ቀርቶ በሌላም ታሪክ ተሰምተው የማይታወቁ አሰቃቂ፦ ሰቅጣጭ፤ አስደንጋጭ አረማዊነት መስማት ከጀመርን ስድስት ዓመት አለፈ። በቀደሙት ጊዚያት ብዙ አሰቃቂ የሰባአዊ መብት ጥሰቶች በነፃ አውጪ ግንባሮች እንደ ተፈፀሙ ይነገራል። ያን ጊዜ እንደ ዛሬው ማህበራዊ ሚዲያ ስላልኖረ ሊሆንም ይችላል። ወይንም የእኔም ከእኔ የቀደመውም ትውልድ በሰባዊ መብት ጥሰት የነበረው አትኩሮት # ደብዛዛ ሆኖ ሊሆን ይችላል። ዛሬ ግን መሻገሬያውም # አሳቻ ፤ ዘመኑም አሳቻ፤ መሪወችም # አሳቻ ስለሆኑ የችግሩን መንስኤ፤ የመፍትሄ ጎዳናውን ለመቀዬስ እጅግ እዬከበደ መጥቷል። የሚሰሙ ሰቅጣጭ ነገሮች ሁሉ ለህመም ዳርገውናል። ለበጎ ነገርም ቢሆን እኔ ተያይዘው የሚላኩልኝን የቪዲዮ ክሊኮች አልከፍትም። ውስጤ ያለው ሃዘን ነው። ዕንባዬ ደርቋል። ዓይኔም በተደጋጋሚ ለኦፕራሲወን ተጋልጧል። ውስጤም ተጎድቷል። ስለሆነም እኔ የተለቀቀውን ቪዲዮ አላዬሁትም። ወ / ሮ ሃንሻ ከወረባቦ በህወሃት ሰራዊት አዛውንት እናታቸው ተገድለው እያዩ አካላቸው ለጅብ ሲሰጥ የዚህች ወ...