«የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ከሥልጣን እንደሚለቁ አሳወቁ» BBC. የእኔ ዕይታ። የህሊና ብቁ ስልጣኔ ትሩፋት። ኢጎን ያሸነፍ የብቃት ልዕልና። ድንቅነትም። ብልህነት።
«የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ሥልጣናቸውን መልቀቃቸውን ገለጹ። https://www.bbc.com/amharic/articles/c4gxn2dkg4lo በቀጣይ ወራት የሚተካቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ለማወቅ እንደጓጉ ተናግረዋል። ትሩዶ ማምሻውን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ምክር ቤታቸው " ለወራት መሥራት እንዳልቻለ " ተናግረዋል። ምክር ቤቱ እስከ መጋቢት 24 ድረስ በሥራ ላይ እንደሚቆይም ገልጸዋል። የትሩዶ ሊበራል ፓርቲ በ 2021 ነበር ለሦስተኛ ጊዜ የተመረጠው። ከኮቪድ -19 ወረርሽኝ በኋላ የተቀዛቀዘውን ምጣኔ ሃብት ለማነቃቃት ፓርቲያቸው ቃል ገብቶ ነበር። ይሄ አገር " እውነተኛ ምርጫ ይፈልጋል " ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። " በውስጣዊ ሽኩቻ " ውስጥ እንደሆኑ ገልጸው ይህም ለካናዳውያን የሚጠቅም እንዳልሆነ ገልጸዋል። ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመመካከር ሥልጣን ለመልቀቅ መወሰናቸውን አክለዋል። ከፓርቲው ሊቀ መንበርነታቸውና ከጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው ነው የተነሱት። ትሩዶ ፓርቲያቸው አዲስ መሪ እስከሚመርጥ ድረስ ሥልጣን ላይ እንደሚቆዩ ገልጸዋል። እሳቸውን የሚተካው መሪ በሚካሄድበት ምርጫ ላይ " ይቺ አገር እውነተኛ ምርጫ ትፈልጋለች " ብለዋል። ትሩዶ በሕዝብ ያላቸው ድጋፍ እየቀነሰ የመጣ ሲሆን ፓርቲያቸው በጠቅላላ ምርጫ ሊሸነፍም ይችላል። የትሩዶ መልቀቅ በካናዳ ፖለቲካ አንድ ምዕራፍ የመገባደድ ያህል ነው። " ፓርላማው ባለፉት ወራት ሥራውን በአግባቡ...