ልጥፎች

"ዕውቅና ለማግኘት ሲባል ወደ ሲኦል አናመራም" የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር» BBC. የእኔ ዕይታም።

  " ዕውቅና ለማግኘት ሲባል ወደ ሲኦል አናመራም " የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር» BBC. የእኔ ዕይታ። https://www.bbc.com/amharic/articles/cge9llldzj2o (የእኔ ዕይታ። አይደለም ለሱማሌ ላንድ ለራሷ ለሱማሌም ይህ ብቃት አንቱ ነው። የአዲሱን የካቢኔ አቅም የአደረጃጀት ጥራት ሚዛን ክብደት አሳይቶኛል። የፖለቲካል አቅሙ ከገፃቸው ጋር ሳሰተውለው ቅብአም ግርማ ሞገስም አስተውያለሁ። ለቀንዱ ፖለቲካም እንዲህ በሳል አቅም ያለው ሰብእና ውድ ነው። ከምርጫው ሂደት ጀምሮ እኔ በሱማሌ ላንድ የዴሞክራሲ ሰላማዊ ስልጡን ጉዞ ምርኮኛ ሆኛለሁ። አገላለፃቸው ለሚመሩት በአት ያላቸውን ታማኝነት አሳይቶኛል። የፖለቲካ ንጽህና ማለትም ይህ ነው።) 1)                    " ህዝባችን መበልጸግ አለበት። ምጣኔ ኃብታችንን ልናሻሽል ይገባል። በዕውቅና ስም ግፍን አንቀበልም ። የትኛዋም አገር ብትሆን ይሄን ወስጄ ዕውቅና እሰጥሃለሁ የሚባል ነገር የለም። ዕውቅና የሚሰጠው አምላክ ነው፤ በጊዜው ይመጣል " 2)                    ለዓመታት ፖለቲከኞቿ አገራቸው ዕውቅና እንድታገኝ እየሰሩ ቢሆንም አዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለዕውቅና ሲባል " ህዝባችንን የሚጎዳ ነገ...