ልጥፎች

BBC. "አምነስቲ፤ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት ሴቶችን "በወሲብ ባርነት" ይዘዋል እና "በቡድን ደፍረዋል" ሲል ከሰሰ

  ·        የአምንስቲ ዘገባ። BBC. https://www.bbc.com/amharic/articles/c74334ywn0jo "አምነስቲ፤ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት ሴቶችን " በወሲብ ባርነት " ይዘዋል እና " በቡድን ደፍረዋል " ሲል ከሰሰ ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተቋም አምነስቲ ኢንተርናሽናል፤ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት በሴቶች እና ሴት ልጆች ላይ " የወሲብ ባርነት " እንዲሁም " በቡድን መድፈርን " ጨምሮ የተለያዩ ወሲባዊ ጥቃቶችን ፈጽመዋል ሲል አዲስ ባወጣው ሪፖርት ከሰሰ። የታጣቂ ቡድኑ አባላት በሴቶች ላይ የፈጸሟቸው ፆታዊ ጥቃቶች፣ ከፍርድ ውጪ የሆነ ግድያ እና የንጹኃንን ንብረት የማውደም ድርጊቶች " በጦር ወንጀልነት ሊፈረጁ የሚችሉ " እንደሆነ አስታውቋል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ አርብ የካቲት 27/2018 ዓ . ም . ይፋ የደረገው የምርመራ ሪፖርት፤ በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱት የታጣቂ ቡድኑ አባላት ከአውሮፓውያኑ 2020 እስከ 2024 ባሉት ዓመታት የፈጸሟቸውን ድርጊቶች የዳሰሰ ነው። ምርመራው የተደረገው በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ውስጥ በሚገኙት ሳዮ እና አንፊሎ ወረዳዎች ውስጥ እንደሆነ ገልጿል። የሰብአዊ መብቶች ተቋሙ ምርመራውን ሲያከናውን በቡድኑ አባላት ወሲባዊ ጥቃት ለተፈጸመባቸው 10 ሴቶች ቃለ መጠይቅ ማድረጉን እንዲሁም የጤና ባለሙያዎችን ማነጋገሩን እና የሕክምና መዝገቦችን መመርመሩን አስረድቷል። በምርመራው ...

ለስሜን ጎንደር በአለፋ ጣቁሳ #ፋኖ አገልግሎት መስጫወችን ማቃጠል የድል እርከን ከሆነ እንኳን ደስ አላችሁ¡¡¡¡

ምስል
  ለስሜን ጎንደር በአለፋ ጣቁሳ #ፋኖ አገልግሎት መስጫወችን ማቃጠል የድል እርከን ከሆነ እንኳን ደስ አላችሁ¡¡¡¡ የአለፋ ጥቁሳን መንደድ ከአቶ ዳንኤል በቀለ ፔጅ ላይ ነው ያገኜሁት። ህወሃት የተነሳበት ዓላማ እየተሳካለት ነው።    "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።" አሜን።     #ምዕራፍ ፲፰።   #በምልሰት የጣና ወርቅ ትዝታን።   ጭልጋ አውራጃ ጭልጋ ወረዳ፤ ማጠቢያ ወረዳ፤ ቋራ ወረዳ ውስጥ አንዱ አለፋ ጣቁሳ ነበር። አለፋ ጣቁሳ የቅቤ፤ የማር፤ የእህል ዘር ብቻ ሳይሆን ማንኛውም #የቅመማቅመም ዓይነት የሚመረትበት፤ በእንሰሳት ተዋፆ ከአሳ ጀምሮ ዕምቅ ሃብት ያለው፤ በዕት ነው። እራሱ ደልጊ ከመድረሳችሁ በፊት የመኪና መስኮቱን ስትከፍቱት የደንቢያን ለጥ ያለ የሽንብራ አዝመራ ሲዘናጠፍ እያያችሁ የደልጊ የቅመማቅመም ህብር ጠረን አቀባበል ያደርግላችቿል።   ሆቴል ይዛችሁ ምሳ ስታዙ #ዓሳ በዓይነት ይቀርባል። እኔ ጎርጎራ እና ደልጊ የበላሁት የዓሳ ጥብስ ጣዕሙ አብሮኝ ይኖራል። ጎንደር ከተማ ክርምትን ተከትሎ የዓሳ ገብያ የደራ ነው። የዓሳ መሰናዶም በየቤታችን ልዩ ነው። ያው በልጅነት እሾ ቢያስቸግረንም።   የሆነ ሆኖ ወዛችሁን እርፍ አድርጋችሁ ሥራ እስክትጀምሩ ድረስ #ሰላምለኪ ጣና ለማለት ወደ ወደቡ ጎራ ትላላችሁ። ጣና እራሱ #አገር ነው። ዲካ የለውም። በሁሉም አቅጣጫ ብትዘዋወሩ ጣናን የዓይኔ ጥግ እስከዚህ ድረስ አይቶታል ብላችሁ መወሰን አትችሉም። የእቴጌ ጎንደር ዝክረ - ማንነትም ከዚህ መሰል እዮራዊ #ትንግርት የተቀዳ ነው። እንዴት ዋልክ ጣናሻ/ እንዴት ሰነበትክ ጣናወርቅ? እንደምን ባጀህ የእኔ ጣና ብላችሁ የቤተ - ዘመዱን፤ የዘመዳ ዘመዱን ወግ ካደረሳችሁ በኋላ ወደ...