ለስሜን ጎንደር በአለፋ ጣቁሳ #ፋኖ አገልግሎት መስጫወችን ማቃጠል የድል እርከን ከሆነ እንኳን ደስ አላችሁ¡¡¡¡

 

ለስሜን ጎንደር በአለፋ ጣቁሳ #ፋኖ አገልግሎት መስጫወችን ማቃጠል የድል እርከን ከሆነ እንኳን ደስ አላችሁ¡¡¡¡
የአለፋ ጥቁሳን መንደድ ከአቶ ዳንኤል በቀለ ፔጅ ላይ ነው ያገኜሁት። ህወሃት የተነሳበት ዓላማ እየተሳካለት ነው። 
 
"አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።" አሜን።
 
 May be an image of ‎map and ‎text that says '‎AI Qadarif رف القضارف Debre DebreDamo Damo Damo Aksum አክሱም Ras Dashen ራስ ስዳሽን Mekele መቐለ Gondar ጎንደር Takusa usa Ta ጣቁሳ Lalibela ላሊባላ Bahir Dar ባሕርዳር ባሕር ዳር Dese ደሴ ir Nekemte ነቀምት Ambo አምቦ Addis Aba አዲስ አበባ Ethiopia ن View Google Maps limp‎'‎‎
#ምዕራፍ ፲፰።
 
#በምልሰት የጣና ወርቅ ትዝታን።
 
ጭልጋ አውራጃ ጭልጋ ወረዳ፤ ማጠቢያ ወረዳ፤ ቋራ ወረዳ ውስጥ አንዱ አለፋ ጣቁሳ ነበር። አለፋ ጣቁሳ የቅቤ፤ የማር፤ የእህል ዘር ብቻ ሳይሆን ማንኛውም #የቅመማቅመም ዓይነት የሚመረትበት፤ በእንሰሳት ተዋፆ ከአሳ ጀምሮ ዕምቅ ሃብት ያለው፤ በዕት ነው። እራሱ ደልጊ ከመድረሳችሁ በፊት የመኪና መስኮቱን ስትከፍቱት የደንቢያን ለጥ ያለ የሽንብራ አዝመራ ሲዘናጠፍ እያያችሁ የደልጊ የቅመማቅመም ህብር ጠረን አቀባበል ያደርግላችቿል።
 
ሆቴል ይዛችሁ ምሳ ስታዙ #ዓሳ በዓይነት ይቀርባል። እኔ ጎርጎራ እና ደልጊ የበላሁት የዓሳ ጥብስ ጣዕሙ አብሮኝ ይኖራል። ጎንደር ከተማ ክርምትን ተከትሎ የዓሳ ገብያ የደራ ነው። የዓሳ መሰናዶም በየቤታችን ልዩ ነው። ያው በልጅነት እሾ ቢያስቸግረንም።
 
የሆነ ሆኖ ወዛችሁን እርፍ አድርጋችሁ ሥራ እስክትጀምሩ ድረስ #ሰላምለኪ ጣና ለማለት ወደ ወደቡ ጎራ ትላላችሁ። ጣና እራሱ #አገር ነው። ዲካ የለውም። በሁሉም አቅጣጫ ብትዘዋወሩ ጣናን የዓይኔ ጥግ እስከዚህ ድረስ አይቶታል ብላችሁ መወሰን አትችሉም።
የእቴጌ ጎንደር ዝክረ - ማንነትም ከዚህ መሰል እዮራዊ #ትንግርት የተቀዳ ነው። እንዴት ዋልክ ጣናሻ/ እንዴት ሰነበትክ ጣናወርቅ? እንደምን ባጀህ የእኔ ጣና ብላችሁ የቤተ - ዘመዱን፤ የዘመዳ ዘመዱን ወግ ካደረሳችሁ በኋላ ወደ ገብያ ወጣ ትላላችሁ። 
 
ወደ ገብያ ወጣ ስትሉ በትንሽ ብልቄያጥ ቤት የምታስቀምጡት #ቅመማቅመም አና ብሎ #በመቶ ኪሎ በሚመዝኑ ኬሻወች መደብሮች ሁሉ ቲፍ ብሎ ታገኙታላችሁ። ያለው የገብያ ጠረን ልነግራችሁ አልችልም።
 
የደልጊ ሰው፤ የአለፋ ጣቁሳ ሰው ከዓሳ ጋር ስለሚያድግ እንደ #ጎጄ የተሰጠው ዓዋቂ - ብልህ - ንቁ ነው። ገበሬው እራሱ ቀልጣፋ፤ ትንታግ፤ ርትዑ ነው። አቶ ገብያው የደልጊ አካባቢ የአምራቾች ህብረት ሥራ ማህበራት ሊቀመንበር ነበር። የኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሜቴ ተለዋጭ አባልም ነበር። አንድ ጊዜ ጓድ ኮነሬል መንግሥቱ ኃይለማርያም በአካል ተገኝተው ጎብኝተውት ነበር።
 
#ውድመት እና ፈቃዱ።
 
በየሰፈራቸው ሄዶ ፈጽሞ ፋኖወች ባላሰቡት አቅጣጫ ተጉዘው የፋንታዚ የእርጎ ባህርን ያስቀዘፈው #ዕብን ዛሬ እንሆ ደስ ይበለው¡¡¿¿¿ አማራ ክልልን እንዲህ አድቅቆ ማንን ለማስደሰት ይህን ዝልቦ የመከራ ዓይነት እንደ #ወጠነው ፈጣሪ ይወቀው። አለፋ ጣቁሳ እኮ የመኪና መንገድም እኮ አልነበረውም። 
 
ያ ምንም ያልነበረው #ተረስቶ የኖረ ወረዳ አለች የተባለችውን በጭቃ ምርጊት የተሠሩ አገልግሎት መስጫውን አውዶሞ፤ መሰሉን ለማግኜት በ30 ዓመታትም አይቻል። ጥቅሙ ህወሃትን ከማስፈንደቅ፤ ቀጥሉ እያሉ ማይክ ላይ ውለው ከሚያድሩት በስተቀር ለነገ ከአመድ በረከት ፈጽሞ የለም። የጎንደር ሊቃናት አለቁ፤ አሁን ደግሞ መሬቱ በነዲድ እንሆ ይገረፋል። ይህን ተሸክሞ አገር መምራት ከወዴት ይገኝ ይሆን??።
 
አለፋ ጣቁሳ በደርግ ዘመን ህወሃት ያልደረሰበት ነበር። በብልጽግና እና በህወሃት በነበረው ጦርነት ወሎ፤ ሰሜን እና ደቡብ ጎንደር ያን ያህል ሲነዱ አለፋ ጣቁሳ የህወሃት ሰለባ አልነበረም። ህወሃትሻ መቀሌ #ቁጭ ብሎ ድቅቅቅቅቅ፤ እምሽክሽክ እያደረገው ነው። የልቡን ያደረሱለት የፋንታዚ ሉዑላን እንሆ ደስ ይበላቸው¡¡¡¿¿¿
 
በዚህ አያያዝ ነገ ደባርቅ፤ ዳባት፤ አይከል፤ ጎንደር ከተማን እያላችሁ ትቀጥላላችሁ¡¡ እራስን ማንደድ፤ እራስን ፈቅዶ #ማቃጠል፤ እራስን ፈቅዶ ጢስ #ማጎናጸፍ ምኑ መሪነት እንደሆን አይገባኝም። እንዲገባኝም አልፈቅድም። 
 
ሥርጉትሻ 06/02/2026
 
****====****//////*******/////
 
"በአማራ ክልል ማእከላዊ ጎንደር ዞን የጣቁሳ ወረዳ አስተዳደር፣ "ጽንፈኛ" ሲል የጠራው ታጣቂ ቡድን፣ ባለፈው ሐሙስ የካቲት 19 በወረዳው በርካታ የመንግሥት ተቋማት ላይ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል አለ። 
 
ቡድኑ ከወረዳዉ 35 የመንግሥት ተቋማት ውስጥ በ28ቱ ላይ ጉዳት አድርሷል ያለው አስተዳዳሩ፣ ሦስቱ ተቋማት ሙሉ በሙሉ በእሳት ተቃጥለው መውደማቸውን ገልጧል። 
 
በ25ቱ ተቋማት ተሽከርካሪዎች፣ ኮምፒውተሮች እና ሠነዶች እንደተቃጠሉ፣ የቢሮዎች በሮችና መስኮቶች እንደተሠበሩ እና በዚሁ ምክንያት የመንግሥት አገልግሎቶችን ለመስጠት አዳጋች ሁኔታ መፈጠሩንም አስተዳደሩ አውስቷል። 
 
የወረዳው አስተዳደር፣ ቡድኑ ጥቃቱን የፈጸመው የጸጥታ ኃይሎች የሕዝብን ደኅንነት ለመጠበቅ ከተማውን ለቀው በወጡበት አጋጣሚ በመጠቀም ነበር ብሏል።"
 
ዋዜማ ራዲዮ
March 2, 2026
በጎንደር የሚገኙ ከተሞችና ተቁዋማት ቀስ በቀስ አየወደሙ ነው። ሆን ተብሎ ነው?

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።