"የተባረከ ትውልድ ለተባረከች አገር“ አዲስ እሸታዊ ራዕይ!
„የተባረከ ትውልድ ለተባረከች አገር“ የደልዳላዋ የቀዳማዊት እምቤት የወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው እሸታዊ ራዕይ ። „አድርገህልኛል እና ለዘላለም አመሰግንህአለሁ“ መዝሙር ፶ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ© ሥላሴ Sergute© Selassie 31.12.2018 ከገዳማዊት ሲዊዝሻ፤ · እ ፍታ። በቅድሚያ ያ ጉማም እና ጎማም ዘመን በፈጣሪ እርዳታ አልፎ ለዛሬ ቃናዊ የበረከት ትንፋሽ ስለበቃን አምላካችን ልዑል እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን። አሜን! በርካታ ስደት ሲያንገላታቸው የኖሩ ወገኖቻችን፤ እንዲሁም የቅድስት ሃይማኖታችን የኦርቶዶክስ ተዋህዱ ብጸፁዐነ ሊቀ ጳጳሳት ሊቃውንተ ቤተክርስትያንትም ከ27 ዓመት የስደት ጊዜ በ ሆ ዋላ በእናት ምድራቸው ሆነው ነው ይህን አዲሰ የፈረንጆች ዓመት 2019 የስደት ዘመናቸውን በምልሰት አስበወት የሚውሉት። ለምሳሳላቸው ብፁዐን አባቶቼ እንኳን ለዚህ አበቃቸው። ፆም ጸሎታቸው፤ ስግደታቸው ሱባኤዋቸው አስብሏል። በሌላ በኩል ለመጪው ኢትዮጵያዊ ገና እና አሰተሮዬም ወደ እናት ምድራችን የሚሄዱ ወገኖችም እንደሚኖሩ ተስፋ አደርጋለሁኝ። ድንግል ጥላ ከለላ ሆና መንገዳቸውን ጠብቃ ካሰቡት ታድርሳቸው። ሳይከፉ እና ከቁጥር ሳይጎድሉም እንደ ሃሳባቸው የሃሳባቸውን ያገኙ ዘንድ ምኞቴ ዘለግ ያለ ነው። ለሚጓጉት እህቶች እና እናቶችም ለዓይነ ሥጋ ያብቃቸው። ውዴቼ የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች እንኳን ለአውሮፓውያኖቹ አዲስ ዘመን ለ2019 በሰላም ደረሳችሁ አደረሰን። ይህ የምሥራች ዜና ስለነበር ለአዲስ ዓመት ያቆዬሁት ጥሩ ተስፋ ነው። ትውልድ ተስፋ ነውና። እንሆ … · ...