"የተባረከ ትውልድ ለተባረከች አገር“ አዲስ እሸታዊ ራዕይ!

„የተባረከ ትውልድ ለተባረከች አገር“
የደልዳላዋ የቀዳማዊት እምቤት የወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው እሸታዊ ራዕይ

„አድርገህልኛል እና ለዘላለም አመሰግንህአለሁ“
መዝሙር ፶ ቁጥር ፱

ከሥርጉተ© ሥላሴ
 Sergute© Selassie
 31.12.2018
ከገዳማዊት ሲዊዝሻ፤





·       ፍታ።

በቅድሚያ ያ ጉማም እና ጎማም ዘመን በፈጣሪ እርዳታ አልፎ ለዛሬ ቃናዊ የበረከት ትንፋሽ ስለበቃን አምላካችን ልዑል እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን። አሜን! በርካታ ስደት ሲያንገላታቸው የኖሩ ወገኖቻችን፤ እንዲሁም የቅድስት ሃይማኖታችን የኦርቶዶክስ ተዋህዱ ብጸፁዐነ ሊቀ ጳጳሳት ሊቃውንተ ቤተክርስትያንትም ከ27 ዓመት የስደት ጊዜ በዋላ በእናት ምድራቸው ሆነው ነው ይህን አዲሰ የፈረንጆች ዓመት 2019 የስደት ዘመናቸውን በምልሰት አስበወት የሚውሉት። ለምሳሳላቸው ብፁዐን አባቶቼ እንኳን ለዚህ አበቃቸው። ፆም ጸሎታቸው፤ ስግደታቸው ሱባኤዋቸው አስብሏል።

 በሌላ በኩል ለመጪው ኢትዮጵያዊ ገና እና አሰተሮዬም ወደ እናት ምድራችን የሚሄዱ ወገኖችም እንደሚኖሩ ተስፋ አደርጋለሁኝ። ድንግል ጥላ ከለላ ሆና መንገዳቸውን ጠብቃ ካሰቡት ታድርሳቸው። ሳይከፉ እና ከቁጥር ሳይጎድሉም እንደ ሃሳባቸው የሃሳባቸውን ያገኙ ዘንድ ምኞቴ ዘለግ ያለ ነው። ለሚጓጉት እህቶች እና እናቶችም ለዓይነ ሥጋ ያብቃቸው።

ውዴቼ የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች እንኳን ለአውሮፓውያኖቹ አዲስ ዘመን ለ2019 በሰላም ደረሳችሁ አደረሰን። ይህ የምሥራች ዜና ስለነበር ለአዲስ ዓመት ያቆዬሁት ጥሩ ተስፋ ነው። ትውልድ ተስፋ ነውና።  እንሆ …

·       መነሻ።
የዶ/ አብይ አህመድ ሚስት ዝናሽ ታያቸው በአለም መድረክ ላይ ያደረገችው አስገራሚ ንግግር |
Abey Ahmed Wife Zinash Tayachew speech

 

ራህብን እና የተመጣጠነ ምግብን እጦትን ለመቀነስ መገስገስ በሚል ባንኮክ በተዘጋጀ ጉባኤ የሶስት ቀናት የርህርህና  ደልዳለዋ ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።

 
„Accelerating the End of Hunger and Malnutrition Event »


ንግግራቸው በአማርኛ ስለሆነ ከልባችሁ ሆናችሁ ታዳምጡት ዘንድ በትህትና እገብዛለሁኝ። እንዲህ አዲስ ዓመት በአዲስ ተስፋ ብቅ ሲል መቼም እንደ እኔ ለላ ስለ ድምጽ አልባዎቹ የኢትዮጵያ እናቶች እና የትውልዱ ብከነት ጉዳይ ግድ ለሚለው ቅን ዜጋ ሁሉ ታላቅ የምሥራች ነው።

 

እንደ አራት ልጆች እናትኔተ ልጆቹ ሲራቡ ብሎ ማሰብ ልቤን ይሰብራዋል፤ ለልጆቼ የተሻለ ህይወት እንዲኖራቸው የተቻለኝን ሁሉ ከማድረግ አልተቆጠብኩም ፤ታዲያ እንደ ቀዳሚት እመቤቴ እና በአገሬ መሰል ችግር ውስጥ ለሚያልፉት ሁሉ እናት ነኝ እና የአመጋገብ ጉዳዮችን ጨምሮ በተለያዩ ቤተሰባዊ ችግሮች አትኩሬ በመስራት ላይ እገኛለሁ“   ከቀዳሚዊት እቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታየቸው ንግግር የተወሰደ።

... የሚሉት ቀዳማዊት እምቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ራዕያቸው „የተባረከ ትውልድ ለተባረከች አገር ነው።“ ታላቅ ተልዕኮ ነው። ንግግራቸውን ሲፈጽሙም ይህኑን ምኞታቸውን ለሉላዊ ማህበረሰበም የተባረከ ትውልድ ለመፍጠረ አብረን በአንድ ሁነን እንትጋ ሲሉ በአጽህኖት አስገንዝበዋል።



 

ይህን ራዕይ የገለጹት ለሉላዊ ዓለም መድረክ ላይ ሲሆን መደረኩም ይህ የመጀመሪያ ጊዜያቸው ነው። በዚህ መቅደመ መድረክ ላይ ያሰተላለፉት መልዕክት ጭብጥ ልብ የሚነካ ነው። በቀደመው ዘመን ኢትዮጵያ ለተማሪዎቿ ወተት ታቀርብ እንደነበረ አውስተዋል። ገርሞኛል ይህ በራሱ መነሳቱ። ለተማሪዎቿ ወተት ጥዋት ጥዋት ታቀርብ የነበረች አገር - ኢትዮጵያ? ዛሬስ ብለን ራሳችን ብንጠይቅ 2 ሚሊዮን ህዝብ በሰው ሰራሽ ችግር ከተፈናቀሉት ውስጥ ምን ያህሉ ህጻናት ግፍ ተፈጸማቸው? አሰበነው እናውቃለን?እራሳችን እንደ ዳንቴል በሰራነው ችግር ውስጥ የነገ ተስፋዎች አብረው ተማግደዋል። ያልታደልን።

 

ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደረግ አባቶቻችን ምን ያህል ለትወልድ ይጨነቁ እነደነበር ቀዳማት እመቤት አመሳጥረውልናል። ቀደም ባለው ጊዜ ለልጆች የተመጣጠነ ምግብ ለማቀረብ ወተት በዬትምህርት ቤት መቅረቡ ከውስጡ የገባው የጠ/ሚር አብይ ካቤኔ ይህንም  ከንድፉ ውስጥ ማስገባቱን ቀዳመዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታዬቸው ዛሬአ ዲስ መረጃ ሰጥተውናል። ይህን ራዕይ መንግሥታችን ይዞ ተነስቷል የሚል አዲስ ተስፋ ነው የነገሩን

 

እኒህ ርህርህት የኢትዮጵያ ልጆች እናትነትን ከውስጣቸው የተቀበሉ ትሁት ኢትዮጵያዊት እናት የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤትን ለማሰራት የመሰረት ድንጋይ እንዳስቀመጡ፤ ት/ቤት በሚበዛባቸው ቦታዎች የዳቦ መጋጋሪያዎችን ለማስፋፋት፤ ወላጅ ለሌላቸው ልጆች የማሳደጊያ ተቋማትን ለመገንባት፤ በዕዕምሮ ጉዳት ለደረሰባቸውም አትኩሮታዊ ድርጊት ለመፈጸም ቢሯቸዋቸው ማቀዱን አውሰተው በተጨማሪም ገላቸውን መተዳደሪያ ላደረጉ እህቶቻችንም የታሰበ ነገር እንዳለ ጠቁሟል ንግግራቸው።



 

ሰብዕዊነት እና ተፈጥሯዊነት የሚመራው የጠ/ሚር አብይ አህመድ ካቤኔ በሁሉም መስክ የተቀናጁ ተግባርትን ለመከወን እዬባተለ ነው። መልካምነት በትውልድ ለመተክል ተልዕኮዬ ብሎ ይዞታል። በሁለመነው በመንፈስም፤ በሞራልም ለባከነው ትውልድ አዲስ ውሃ ያልነካው ራዕይ መኖሩን አብሳሪ ነው መረጃው።


„የተባረከ ትውልድ ለተባረከች አገር“ የሚደንቅ ራ ዕይ ነው። እኔ አገሬ ስለሚናፈቀኝ እንደሆን አላውቅም እንዲህ መሰል ንግግሮችን ሳዳምጥ ዕንባዬ ከዬት እንደሚመጣ አላውቅም። ዝም ብሎ ነው በፈቃዱ የሚፈሰው… „የተባረከ ትውልድ ለተበረከች አገር“ እስኪ መዳህኒተ ዓለም አባቴ ይጨመርበት። ድንግልም ትርዳን።



 

ሌላው በዚህ ንግግር አትኩሮት የሳበው ለባህል እና አገራዊ የአመጋጋብ እና የአስተዳደግ ሥርዓቶች ያላቸው እክብሮት ብቻ ሳይሆን እራህብ መለያዋ ተድርጎ በራህብ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ለተለጠፈችው እናት ምድር የምግብ አለመማጠን የሉላዊ ጥናታዊ መረጃ ዋቢ አድርገው ችግሩ ዓለም አካላይ እንደሆነም ጠቆም አድርገው አልፈዋል። ይህም በሥነ ልቦና ለተጎዳው ኢትዮጵያዊ መንፈስ አንድ አድነኝ የሆነ የሥነ - ልቦና ግንባታ ነው። ለሉላዊው ዓለም ሊሂቃንም አብሶ ለጋዜጠኞች እና ለጸሐፍት እንዲሁም ለሚዲያዎች አንድ የማነጸጻሪያ የማመዛዘኛ ማስተዋሻ ነው።

 

በተረፈ የጦርነት ራህብተኞች ፉከራ ላይ ላላችሁት ሁሉ ቢያንስ ለትውልዱ ራዕይ ስትሉ እባካችሁ የዚህን ቅድስና መንፈስ አትወኩት። አትናፍቃችሁም የተባረከች አገር የተባረከ ትውልድ ሲኖራት? ከቶ ከምኑ ይሆን የተሠራችሁት?

 

ራዕዩ ከውስጤ ነው የገባው። „የተባረከ ትውልድ ለተባረከች አገር“  መንፈሴን ነው የገዛው። እኔ ብቻዬን ሆኜ ብዙ ለፍቸበታለሁኝ ፍሬ ባያፈራም። ግን መንፈሱ እንዲህ ሁነኛ ባለቤት ሲያገኝ ውስጤ ተክሷልኝናል። ዛሬ በዕጥፍ ሻማ ሲበራ ያድራል። አንድ ጊዜ  በኤድስ ቤተሰባቸውን ያጡ ልጆችን በእሷ እና በባለቤቷ ደሞዝ ብቻ ስትባትል የነበረች ጀግና ሴትን በሃሳብ እረዳት ነበር።

 

ቤት አጥታ ስትንከራትት ሁሉ ነበር። ያን ጊዜ በነበረኝ አቅም ልክ አይዞሽ እላት ነበር። ዛሬ ያች ቅድስት ተልዕኮዋን የት አድርሳው ትሆን እላለሁኝ እንዲህ ዘመን እራሱ አለሁሽ ሲላት አስተውሳታለሁኝ። ቤት ስትከራይ የልጆች ጩኸት በረከተ እዬተባለች ቤት ፍለጋ ስትንከራተት በመጨረሻ ከወላጅ አባቷ ቤት ይዛቸው እንደገባች ነበር የተቋረጥነው። ህይወት እና ዕድል እዚህ ሲዊዝ አመጣኝ ያ የተጀመረ መልካም ተግባርም ተቋረጠ።


የሆነ ሆኖ ዘመኑም የተባረከ ነው ባይ ነው። ለዚህ ነው ይህ ዘመን የተመረቀ ነው እምለው። እንዲህ ስለ ሰው ጭንቅ ጥብብ የሚለው መንፈስ ፈጣሪ ሰጠን። ለዚህም ነው ምርቃታችን እንዳይወሰድ እንጠንቀቅለት የምለው። ተመስገን!

 


ክወና።

 

https://sergute.blogspot.com/2018/05/01.html

አብይ ክስተት ነው ክፍል 5 የዛሬ ዓመት 01.01.2018 የተጻፈ ነው።

የዛሬ ዓመት ትጋቴ ፈሶ ባለመቅረቱ ከተመሰገን በላይ ነው። የተባረከው ሳተናው መባተልም አፍርቷለታል። ይህ ዜና ራሱ ቸር ወሬ ነው። 

 

እውነት ለመናገር ራሱን በቻለ የፈቃድ ሱባኤ ይህን ምኞቴን ላሳካልኝ ነጉሴ እና አምላኬ ማቅረብ ይኖርብኛል። ይህን ናፍቆኝ ነበር የተጋሁለት። እንዲህ ርህርህና ናፈቆኝ ነበር። እንዲህ ትህትና ሽው ብሎኝ ነበር። እንዲህ ተስፋ ያለው ነገር ለትውልዱ ተመኝቼ ነበር።

 

ይህን ላሰማኝ፤ ይህን ዘመን ላሳዬኝ ለመዳህኒዓለም ክርስቶስ ምስጋና አቀርባለሁኝ። የዛሬ ቸር ወሬ መረጃውን ላላገኘችሁ እስኪ ለተስፋ ስንቅ ይሁናችሁ በማለት ተጣፈ። መልካም ዓውዳዓመት።

 

ሴቶች ጥበብ ናቸው!

ሴቶች ቅኔዎች ናቸው!

ሴቶች የመኖር ሥነ - ህይወቱ ናቸው!

 

የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ!


 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።