ልጥፎች

ከጃንዋሪ, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የልቅና የቅንነት አሳር።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  የልቅና የቅንነት አሳር ። „መከራን ያጸኑብሽ ባንቺ ጥፋት ደስ ያላቸው ይጎሳቀላሉ።“ መጽሐፈ ባሮክ ፬ ቁጥር ፲፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 30.01.2019 እመ ዝምታ ሲወዘርላንድ።                         የእኔ ድንግልዬ ትጠብቃችሁ!     አንድ ዜና ተከታተልኩኝ። ለነገሩ እኔም ጠፍተውብኝ ነበር የሰነበትኩት ዶር ለማ መገርሳ። በተደጋጋሚ ታመሙ፤ ለህክማና ሄዱ የሚለው ዜና ሁልጊዜ ይረብሸኛል። ቅን ሰው የማያበረክተው ዕድላችን በምን ዓይነት ሁኔታ ይህን ዘመን ሊያሻግረን እንደሚችል ግራ ይገባል።    አንድ ጠንከር ያለ ዘገባ OBN አቅርቧል። ታዩት ዘንድ ከሥር ለጥፌያለሁኝ። ይህን መሰል ተግባር የዛሬ ዓመት በትጋት ይሠራ ነበር ሚዲያው።   ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከተመረጡ በኋዋላ ግን አቁሞት ቆይቷል። በዚህ ጉዳይ ቢተጋ ብዙ መንፈሶችን መሰብሰብ ይችል ነበር ሚዲያው። ይህን ዘመን ለመታደግ ይህ ሚዲያ ቁልፍ ድርሻ አለው። ስለዚህ ዘመኑን ሳያቃጥል በትጋት በዚህ መሰል ተግባር ላይ ቢያተኩር መልካም ይሆናል።   የሆነ ሆኖ ቅኑ፤ ትሁቱ፤ ለስላሳው የዴሞክራሲ አባት ዶር ለማ መገርሳ በርከት ላሉ ቀናት ከሚዲያ የሉም። መቼም ኦነጋውያን፤ ህወሃታውያን ያህል ጸረ ሰብ ደርጅቶች አስቀምጦ በመዘናገት የተፈጠረ ችግር ከኖረ እጅግ ሚያሳዝን ነው የሚሆነው።   ምክንያቱም እኔ እራሴ ከውጥኑ ጀምሮ ይጠነቀቁ ዘንድ በስፋት ጽፌያለሁኝ ህዳር ላይ ከ2017 ጀምሮ። ይህ መሰል ህፃፅ የሥልጣን ሱስ ብቻ...

የተመስገን አዬር ሻታ!

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  የተመስገን አዬር  ሻታ! „ፍለጋውም ( ኢታምልክ ) አለገኙትም፤   ልጆቻቸውም አልተቀበሉትም፤ ከህጋቸውም ራቁ። የከነዓን ሰዎች ይህን አልሰመሙም፤  የቴምናንም ሰዎች አላዩም።“   መጽሐፈ ባሮክ   ፫ ቁጥር ከ፲፱ እስከ ፳ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 30.01.2019 እመ ዝምታ ሲወዘርላንድ።                                                                 ነባቢት! ·        ጠ ብታ። ቪንቲ ዛሬ ንፋስ አለ። ወጀቡ አዬል ብሏል። አንዲህ ዓይነት ወጀብ ለጤና መልካም አይደለም። እትጌም አትሞቅም እንጂ በመቁንን ለቀቅ እድርጋ ነበር እኩለ ቀን ጨረሯን … ግን በመቁንን ነው ...  ·        ሻታ … ሻታ መዞር አለ። ሻታው የጤና ነው። እዮር የላከውን ተስፋ ጸበለ ጣዲቅ ይድረሳችሁ እናንት ግፉዕና እያለ ነው። የተመስገን ሻታ ቀን ሰጥቶት አላችሁን? እንዴት ባጃችሁ? ለመሆኑ ከወጀቡ፤ ከማእበሉ ከበቀሉ፤ ከቁርሾው የተረፋቸው የአገር ፒላሮች እንዴት ናችሁ? ሰው መሆናችሁን ያዬ ሻታ እናንተ ዘንድ ብቅ ማለቱን አዳመጥን ይላል የሰሞናቱ አዬር … ኢትዮጵያ ከሰጣት መልካም ቅን ብርቱ ወ...

ዜና እረፍት እና ዕድምታው በጨረፋታ በተያይዞ።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ዜና እረፍት እና ዕድምታው በጨረፋታ በተ ያ ይዞ። „ሁሉን የሚያውቅ ጌታ ያውቃታል፤ ሰማይንና ምድርን የፈጠረ እግዚአብሔር  በእውቀት አገኛት።“ መጽሐፈ ባሮክ ፬ ቁጥር ፳፮ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 30.01.2019 እመ ዝምታ ሲወዘርላንድ።   ነፍስ ይማር።  ·        እ ፍታ። ውዶቼ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ? ትናንት ብቅ አላልኩም። ለሳተናው ጹሑፎቼን በምልክበት ጊዜ እሱን እንዳላጨናንቅ ስለምሰጋ በሳምንት አንዲት ወይንም ቢበዛ ሁለት ወግ ነው እምጽፈው። ያ ለጤናዬ በጣም የሚመች ነበር። እንዲህ ብቻዬን ስሰራ ግን አገሬ ሥራ ስለሆነ ካለምንም ሰቀቀን ስለምሰራ ጫና በጤናዬ ላይ እፈጥራለሁኝ። ስለዚህ አልፎ አልፎ እረፈት ራሴን አስገድጄ እወሰዳለሁኝ። በሌላ በኩልም የሃሳብ ቀንም ታቅዶ ይከወናል። ·        ማደረጀት እና መምራት።  ስለ ማደራጀት እና የመምራት ሁኔታ ስለ ጽንሰ ሃሳቡ በጸጋዬ ድህረ ገጽ በስፋት እንዲሁም በሌላም ጉዳይ አስታክኬ ብዙ ጽፌያለሁኝ። ከሰሞናቱ ዜና እረፍት አዳምጫለሁኝ። የጓድ ለገሰ አስፋውን። ነፍሳቸውን ፈጣሪ አምላክ በአጸደ ነፍስ ያኑር። አሜን።  ጓድ ለገሰ አስፋው የማዕከላዊ ኮሚቴ የፖለቲ ቢሮ አባል እና የድርጅት መምሪያ ሃላፊ የነበሩ ናቸው። ስለዚህ እኔ ለሠራሁበት ዘርፍ የአለቆቼ አለቃ ነበሩ። እኔ አሞኝ አልተገኘሁም ነበር እንጂ እሳቸው በተገኙበት ስብሰባ ጓዶቼ እንደ ነገሩኝ በአንድ ወቅት በድርጅታዊ ተግባራት ላይ በሰጡት ትንተና ጠንከር ያለ አቅም እን...