ልጥፎች

ከፌብሩዋሪ, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

በቀል፦ አመድ፤ እና ጥላቻ ለማፈስ አትሽቀዳደሙ። #እባካችሁ - ተው! #እረፋም! የጦርነት ድግስ ይቁም! የዶር ሙላቱ ተሾመ ትጋት #ለኖቤል ሽልማቱ ጥበቃ ነው። #ዘብአደርነት።

ምስል
  በቀል፦ አመድ፤ እና ጥላቻ ለማፈስ አትሽቀዳደሙ። #እባካችሁ - ተው! #እረፋም ! የጦርነት ድግስ ይቁም! የዶር ሙላቱ ተሾመ ትጋት #ለኖቤል ሽልማቱ ጥበቃ ነው። #ዘብአደርነት ።   ከሞያሌ እስከ አባይ ምንጭ፤ ከአባይ ምንጭ እስከ ሮኃ ለመስፋፋት ለአወጄ ኃይል እራስን? መታመንን? ቅንነትን ለመገበር ወረፋ መያዝ ጅልነት ወይንስ ድብነት?????   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"     ፖለቲካ ማለት ጥፋት መናፈቅ፤ ፖለቲካ ማለት እራስን ማንደድ፦ ፖለቲካ ማለት ትውልድን ሰርክ ለባሩድ መማገድ፤ ፖለቲካ ማለት በኋላቀርነት መቀጠልን መፍቀድ - መናፈቅ፤ ፖለቲካ ማለት ለሥልጣኔ ፀር መሆን፤ ፖለቲካ ማለት በቀውስ ውስጥ መዳከር፤ ፖለቲካ ማለት ለጥፋት መጣደፍ፤ ፖለቲካ ማለት ትውልድን ማቆራረጥ፤ ፖለቲካ ማለት ስጋትን ዲል ባለ ሆታ ማቆላመጥ፤ ፖለቲካ ማለት ህዝብን ከሰቀቀን ጋር ማፋለም አይደለም። ሊሆንም አይችልም።   ፖለቲካ ለህዝብ የመኖር ዋስትና ዝቅ ብሎ፦ ሎሌ ሆኖ መትጋት ማለት ነው። በቀላል አገላለጽ የህዝብን የመኖር ዘይቤ በአስተዳደር ጥበብ ማቅለል፤ ማሻሻል፤ ህዝብ መኖሩን ይወደው ዘንድ አስቻይ ሁኔታወችን በቅንነት ማመቻቸት ማለት ነው። ወደ ውስብስቡ የሳይንስ እና የፍልስፍና ተፈጥሮው ሳንዘልቅ።   ቀላሉን የህዝብ የማስተዳደር ተግባር ለመከወን ደግሞ ህዝብን በሰርክ ማገዶነት ማቅርብ ሳይሆን፦ መኖሩን ያለስጋት የሚከውንበት ፈሊጥ ተግቶ ማሰናዳት ነው። ይህ ሲያቅት ነው ብዙ ጊዜ የቀውስ ናፍቆት የሚመጣው። ለስሜን ህዝብ ጦርነት ከተፈጠረበት ዕለት ጀምሮ አስተናግዷል። ቢያንስ አሁን ይበቃዋል - ጦርነት። ስሜናውያን በቃን ጦርነት ብለው በህብረት ሊነሱ ይገባል።    በዚህ ጦርነት ኦሮምያ፤ ደቡብ፤...

የካቲት 25/2006 ሲጠዬቅ ስለ #ባለድርብ #ህሊና ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን።

ምስል
  የካቲት 25/2006 ሲጠዬቅ ስለ #ባለድርብ #ህሊና ። #አገር እና የአገር ሕይወት ጌታ ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን። ነገረ ጸጋዬ #ሚዛኔ ነው። ነገረ ጸጋዬ ተግባሩ እራሱ #የፊደል #ገበታ ነው።   "አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድድሃለሁ።" (መዝሙር ፲፯ ቁጥር ፩)       ዛሬን በነጮቹ የካቲት 25ትን ዕለቱን ከመንበሩ ጉብ ብሎ ተደላድሎ ስናገኜው እምንጠይቀው ቁልፍ ጥያቄ አገርም- አህጉርም፤ ዜግነትም - እኛነትም፤ ዕውነትም - መኖርንም፤ ሃይማኖትን - ታሪክን፤ ትውፊትን - ትሩፋትን፤ ወግ - ባህል - ልማድን፤ ሥልጣኔን ያናገረ - ያወያዬ - #ያስጠሞነ - ያመሳጠረ፥ በእነሱ ልዩ እርካታ ከፍታም የመረመረ - #የተፈላሰመ ፤ ወቅትን ከትናንት እስከ ነገ የተረጎመ - የተነበዬ ያን ታላቅ #ቁምነገር ፤ የተግባር #አንቱ ፤ #ዓራት #ዓይናማ ሊቀ - ሊቃውንት ባለ ድርብ ህሊና ኢትዮጵያዊ ስለምን አሳጣህን ተብሎ ነው? ዕለቱን ሳስበው እንደ አገር አውራ - ታቦት የማዬውን የሁለመናዬን ቅኝት፤ የትውልድ የቤት ሥራዬን በማሰብ - በማስላትም ነው።   መኖሬን ሳስበው መንፈሴ ያን ታላቅ ሰው እዘክረው ዘንድ በሕይወት እያለሁኝ በስደት አገሬ በኳሽ አይሏ በእምዬ ሲዊዘርላንድ ስለ ሥሙ፤ ስለተግባሩ፤ ስለ ሊቀ ሊቃውንትነቱ እናገር - እጽፍ - እመሰክር - #አውጅ ዘንድ አምላኬ ስለፈቀደልኝም በማመስገን ነው። በተለይ የጸጋዬ ድህረ ገጽ ስወጥን፤ ስጀምር ላገዙኝ ለተባበሩኝ ማህበረ ቅንነት እጅግ ከፍ ያለም ምስጋና አቀርባለሁኝ። ለምንጊዜውም አከብራቸዋለሁኝ። ቅንነታቸው ቁሞ አስተምሮኛል እና። ያ ጥንካሬዬ ጸሐዬ ሆኖ ነው የጸጋዬ ራዲዮን የጀመርኩት። ብርታቶቼ ግሉኮሶቼ ከሲዊዝ፤ ከአውስትራልያ እና ከአገረ አሜሪካ ...

የሌሊቱ የመሬት መንቀጥቀጥ እና #ድብ ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ።

ምስል
  የሌሊቱ የመሬት መንቀጥቀጥ እና #ድብ ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"     በክርስትና ሆነ በእስልምና መሠረቷ በጸናው ኢትዮጵያ አገራችን በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እዬታዬ ነው። ዘለግ ላለ ጊዜ የቆዬ ንዝረት ሌሊት እንደ ነበረ ዘገባወቹ ይናገራሉ። #ሰውኛነቱ ፈተና ውስጥ ያለው የኢትዮጵያ ሁኔታ ደግሞ በሰው ሰራሽ ድሮን የአማራን ህዝብ #እያፈለሰ ፤ #እያሸበረ ፤ #መጠጊያ እያሳጣ ነው።   ዛሬ ሌሊት የአዲስ አበባ ነዋሪወችን በማስደንገጥ የቀሰቀሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ብዙ የአገራችን በዕቶች እንደነዘረ ባለሙያወች ይናገራሉ። በአዲስ አበባ አካባቢ የሚገኙትን ከተሞች እና እንዲሁም በአዋሽ፦ ጭሮ ዙሪያ፤ በድሬድዋ፤ ናዝሬት፤ ደብረዘይት፤ ደብረብርሃን፤ መተሃራ፤ ከሚሴ፥ ደሴ ወዘተ ተከስቷል።    ይህን ሰማያዊ የማስጠንቀቂያ #ቃል #ባሊህ ብሎ በፆም በጸሎት፦ በድዋ፦ በሱባኤ ለላይኛው አቤት ማለት ሲገባ በገፍ የአማራ ልጆች #ይታሰራሉ ፤ በገፍም ወደ ጦርነት በሚያመሩ ጉዳዮች ሰፊ ሽፋን እዬተሰጠ ይገኛል። #ጭካኔው ፤ #ጥላቻው ፤ #የአለመደማመጡ ሁኔታ አይሎም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ጎልቶ ይታያል።    ኢትዮጵያ ሰውኛ፤ ተፈጥሮኛ ፖለቲከኛ ቢኖራት አገራዊ የፀሎት ጊዜ ሊታወጅ በተገባ ነበር። አደብ ገዝቶ ይህን ወቅት በራሱ ወደ ዘላቂ #መፍትሄ ለማምራት ትልቅ አጋጣሚ ነበር።    የሰማይ ቁጣ ማስጠንቀቂያ ከመጋቢት 18/2010 ዓም ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ለመምጣት ዋዜማ ላይ እያሉ ነበር ሌሊት በዋዜማው በመቀሌ አቅራቢያ የመሬት ንዝረት የተከሰተው። ከዛም የዶር አብይ የ100 ቀናት ሳይጠናቀቅ ነበር መሰል የሰማይ ማስጠንቀቂያ በጉ...