እማዋይ የዘመን የኔታዊት!
የጥቁር ለባሿ ልዩ ጀግና! የዘመን የኔታዊት ገናና! ሥርጉተ ሥላሴ 17.02.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።) "በተቸገረ ጊዜ እግዚአብሄርን ወደ መፍራት የሚመለስ ሰው አለ ሰውነተም በተድላ በደስታ ታርፋለች።" (መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ፳ ቁጥር ፳፩) · እፍታ። እንደም ነሽ ውርሰ ጽናት እማዋይ? ደህና ነሽ ወይ? እህት ዓለም እንኳን ለዚህ አበቃሽ። ግን እንዴት ነሽ የጥቁር ለባሿ ጀግና ብቋዊት? እንደተፈታሽ ገጽሽን ሳዬው ውስጤን በጠበጠው። ተረባበሽኩኝ። ለረዥም ጊዜ በጸጥታ ውስጥ ነበርኩኝ። እኔ ጫካ በገባሁበት ጊዜ ተገናኝትን ቢሆን ኖሮ የወላጆቼን የምህረት ጥያቄ አልቀበልም ነበር። ስቃዩን እንጋራው ነበር በዱር ቤቴነት። አንድ አጋር አንስት በማጣቴ ምክንያት ነበር የተመለስኩት። በምህረት ከገባሁ በ ኋ ዋላ ም ቀዮዋን በር አይቻታለሁ። ስፈታም በቁም...