To Toni Loba, Good Luck Wishes!
· Toni Loba የፍቅር ጠይም ዕንቁ! ሌላው በሦስተኛ ደረጃ አሁን የፊታችን ሃሙስ እንደ አውሮፓወያኑ አቆጣጠር ግንቦት 24. 2018 ወደ 15ሺህ ተመልካች ታዳሚ በሚገኝበት የጀርመን የ2018 የሞድ አሸናፊ Germeny Next Topmodel 2018 (GNTM) ውድድር በደም ሐረግ ዘሯ አፍሪካዊ ናይጀሪያዊቷ በጀርመን ሽቶትጋርድ የምትኖረውን ቶኒ ትሆናለች ብዬ ነው እማስበው፤ ሦስት ተጨማሪ ተፈታኞችም አሉባት አንዷ እንደሷ ከጠይምነት ወደ ዳማነት ያደላች ናት። ለነገሩ ጥርጣሬም የለኝም ። ይህ ውድድር ለረጅም ጊዚያት ከቦታ ቦታ እዬተነቀሳቀሱ በጋራ በመኖር የሚካሄድ ሲሆን ወላጆች ሥራቸውን በአግባቡ ስለማይሰሩ ፕሮጀክቱን ለሚመረቱ ለዓለም አቀፍ ሞዴሏ፤ የቴሌቪዠን ሞደሬተሯ፤ ለዳኛዋ ለወይዘሮ ሃይዲ ክሉም እና ለአጋር ዳኞቻቸው እንዲሁም ለተሳታፊ የካሜራው ቲም ሁሉ ብዙ ፈተና በዬዘመኑ ይገጥማል። ሰብዕናቸው ያልጠኑ ተወዳዳሪዎች ከዘርኝነቱ ጋር ተዳምሮ ወይንም ከበታችነቱ ጋር ታክሎ ፈተናው በጣም ያዬለ ነው። ለዚህም ነው እኔ ወላጆች ልጆቻቸውን እንዴት ማሳደግ አለባቸው፤ የልጆቻቸውን ራዕይ ለማሰካት ምን ላይ ቢያተኩሩ መልካም ይሆናል የሚለውን „ የተስፋ በርን“ እንድጽፍ የተገደድኩበት አብዩ ምክንያት። ልጆች የማይገኘውን ዕድላቸውን በሥነ - ምግባር አቅም ማነስ፤ ወይንም ራስን ችሎ በመቆም አቅም መሳሳት፤ ወይንም በህሊና እንጻ ድህነት ምክንያት ወርቁን አጋጣሚ ያጡታል። እኔ ስለመጪው ነገረ ዓለም ያስጨንቀኛል። ትውልድ በአግባቡ ካልተገነባ አህጉርም፤ ዓለምም፤ አገርም እንዳለ አይቆጠርም። እኔ የማዬው ግድፈት በሠለጠነው አለም ይሁን ባልሰለጠነው ...