ልጥፎች

የእኔ ትእግስት።

ምስል
                    የእኔ ትእግስት ስናፍቅሽ ወይንስ ስመኝሽ                      እሙዬ የትኛው ሥም ይሻልሽ ይሆን?                                      ከሥርጉተ ሥላሴ 05.06.2018 (ከጋዳማዊቷ - ሲዊዘርላንድ።)             „እግዚአብሄር ጥበብን ይሰጣልና፤ ከአፉም እውቀትና ማስተዋል ይወጣሉ፤ እርሱ ለቅኖች ደህንነትን ያከማቻል፤                 የፍርድን ጎዳና ይጠብቃል፤ የቅዱሳኑንም መንገድ ያጸናልና። ( መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፪ ቁጥር ከ፮ እስከ ፰ ) ·          በር። አቶ ዛሬ እምር ብሎበት ነበር የዋለው በገበርዲን በከረባት ሽቅርቅር ብሎ ወሸቤም የቆዬ መስሏል። ንግሥቲቱም ፏ ብላ በሠረገላ ተኮፍሳ አገር ምድሩን እያፍነከነከችው ነው። እልፍኟ ኑብኝ ይላል። አልባብ ባልባብ፤ ታዲያንላችሁ ሥርጉትሻ ምኗ ሞኝ። እሷም የአቶ ዛሬን ግምጃ ቤት ለመታደም በልክ በሆነ ዝነጣ ወጣ አለች። ግን ምን አለ ሁልጊዜ እንዲህ ብትሆን ይህቺ የአውሮፓ ቅምጥል። ሰዉ ይስቀላ። ቀሎታል። ደስ ብሎታል። ታውቃላችሁ አይደለም? የሆነ አውሮፓ የሚጫን ደመመን ነገር አለው። ክብድ የሚል። ግን ዛ...

ፍቅር ቁጥር አይደለም።

ምስል
           የፍቅር ተፈጥሯዊ መርህ                 ቁጥር አይደለም።                                          ከሥርጉተ ሥላሴ 03.06.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።)                        „የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሄርን መፍራት ነው። ሰነፎች ግን ጥበብን ተግሳጽን ይንቃሉ።“                                         (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፯) ፍቅር ቁጥር አይደለም፤ አንድ ሁለት ሦስት እዬተባለ በጥቁር ሰሌዳ ላይ በጠመኔ የሚጻፍ። ፍቅር መስፈሪያ የለውም። ፍቅር ዳርቻ ዲካ የለውም። ፍቅር ስፋት እና ቁመት የለውም። ፍቅር ቅርጽም ፎርምም ሊወጣለት አይችልም። ፍቅር አልፋ እና ኦሜጋ ነው። ፍቅር ነፍስ ነው። ፍቅር ደም ነው አብሮ የተፈጠረ። አብሮ የሚኖር። ልባም ከሆንክ ለትውልድ የምታወርሰው ቋሚ ቅርስ ነው። ትውልድንም የምታስቀጥልጥ...