ልጥፎች

መባቻው አባተ ለመሰንበቻው … ተመስገን አሜኑ!

ምስል
ዕይታ። „ይሁዲም ሦስት ወይንም አራት ዓምድ  ያህል ባነበበ ቁጥር ንጉሡ በካራ ቀደደው፤ ክርታሱም በምድጃ ውስጥ ለላው እሳት  ፈጽሞ እስኪቃጠል ድረስ በምድጃው  ውስጥ ወደ አለው እሳት ጣለው።“ (ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 36 ቁጥር 23) ከሥርጉተ© ሥላሴ 16.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።) ·        በር። በትናንቱ የሚሊዬነም አዳራሽ ዝግጅት ላይ ጠቢቡ ቴወድሮስ ተገኝቶ ነበር። ከዛ በመገኘቱ እና ባቀረባቸው ዝግጅቶች ላይ አንዳንድ አስተያዬቶች ይሰጣሉ። ያ መብት ነው። ሁሉም የተሰማውን መግለጽ። ስለዚህም እኔም የተሰማኝን መግለጽ እሻለሁኝ። በዚህ ቀንበጥ ባለቅኔ ላይ ብዙ መከራዎች አልፈዋል። መከራዎቹ ኢትዮጵያ ተሸክማ ከኖረችው መከራ እንደ አገር ባይሆንም እንደ ግለሰብ ግን የማያንስ መከራ ሲፈራረቅበት የኖረ የጥበብ ሰው ነው። እንደ ሌሎች ተሰዶ አይደለም መከራውን ያስተናገደው „አልሄድ አለኝ እግሬ“ በማለት እዛው ሆኖ መከራዋን ተመግቦ ነው የኖረው። በፈታናውም ሰለጠነበት። ሌሎች የጥበብ ሰዎች እንደ እሱ የጠና ነገር ገጥሟቸው አያውቅም። ሊኖር ቢችል የሚታገዙበት የመንፈስ ሃብት አጥተው አያውቁም፤ ብረት መዝጊያ የሚሆን ሰው እንደ ማለት። ይህ የጥበብ ሰው ግን ከፍ ባለው ፈጣሪ ዝቅ ሲል የትዳር አጋሩ እና ቤተሰቦቹ በስፋት አድናቂዎቹ ካልሆኑ በስተቀር ሁነኛ የእኔ የሚለው የሚመካበት ባለሥልጣን የለውም። እንዲህ ዓይነት ቀንጣ ሰዎች በዚህ መሰል የጥበብ መድረክ ሲመጡ ከጎናቸው ሰው ከሌለ ፈተናው እጅግ ግዙፍ ነው። አንድ ሰው ሌላ ደጋፊ ትክሻ የሆነ ሰው ከሌለው የማናቸውም ጥቃት ሰለባ መሆኑ የታወቀ ነው። ይህን በእኔ ...

የደህሚት መሳቂያ ቀረርቶ በኔት ሲሰለቅ ...

ምስል
የደህሚት ቀልድ። የሌባ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያወልቅ፤ ለነገሩ ከነፍጠሩቱ ነው … ከሥርጉተ ሥላሴ 14.07.2018 (ከጭምቷ ሲወዘርላንድ) „እግዚአብሄርን እንዲህ በሉት፣--- ሥራህ ግሩም ነው፤ ሃይልህ ብዙ  ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ“ (መዝሙር ምዕራፍ ፷፭ ቁጥር ፭) ·        መነሻ። https://www.zehabesha.com/amharic/archives/92907  „ደህሚት የትጥቅ ትግል አቆመ“ ·        የማተብ ወለምታ እንደ መግቢያ። ወይ ቀልድ፤ ስንት ቧልተኛ፤ ስንት አላጋጭ፤ ስንት ስንጥቅ፤ ስንት ትርትር፤ ስንት ብልዝ፤ ስንት ዝብርቅ፤ ስንት ጥንዙል፤ ስንት ማድያታዊ ወግ ይሆን ዘንድሮ የሚደመጠው። ትናንት ተዚህም ተዚያም ስል ቆያይቼ በደከመኝ ሰዓት ነበር ዘሃበሻን እንዴት አመሸህ ስል አዳዲስ ዜናዎች ይዞ የጠበቀኝ። ልቤን ሳብ ያደረገኝ የአላጋጩ የደህሚት የማተብ ወልምታ ነው። ሳቅ በሳቅ ነው የሆንኩት የእውነት ልቤ ፍርጥ እስኪል ድረስ ሳቅኩኝ። ቀልድ አይሉት መቦጫረቅ፤ መቦጫረቅ አይሉት መንጨባረቅ፤ መንጨባራቅ አይሉት መዛቀጥ፤ መዛገጥ አይሉት ማንዳላጥ ቅጥ አንባሩ ግርም ይላል፤ ቡጭቅጭቅ አንባርጭቃ! ·        የላ ንቁሶ ልግጫ። እንዲህ ይለናል ትራሱን ከፍ አድርጎ  ሲያለግጥ የከረመው ደህሚት  … . „ድርጅታችን ይህ አሁን በአገራችን ወደ ስልጣን የወጣው በዶር አበይ የሚመራው የለወጥ ሃይል የድርጅታችን እና የመላ የኢትዮጵያ ህዝብ የትግል ውጤት መሆኑን ...