ልጥፎች

ጋዜጠኛ ተምስገን ደሳለኝ እንኳን ወደ አማራ ተጋድሎ መንፈስ መጣህልን!

ምስል
„ጀግንነት ሰው መሆን ከሚለው ሲነሳ ትውፊት ይሆናል።“   „ኤርምያስ ባሮክን እንዲህ ሲል አዘዘው … አንተ ግን ሂድ ከአፌም የጸፍኸውን የእግዚአብሄርን ቃል በፆም ቀን በእግዚአብሄር ቤት በህዝቡ ጆሮ በክርታሱ አንበብ ደግሞም ከከተሞቻቸው በሚወጡ በይሁዳ ሰዎች ሁሉ ጆሮ አንብበው“ (ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፴፮ ቁጥር ፮)  ከሥርጉተ© ሥላሴ 23.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።) ·        መነሻ። „ወይ ባልዘፈንሽ ከዘፈንሽ ደግሞ ባላሳፈርሽ ነው።“ ምነው የአማራ ብዙሃን የመገናኛ ወኪል ቁርጥ አደረጋችሁት ጎመዳችሁት ፍሰቱን። ሙሉ ቢሆን ለዳኝነትም ይረዳም ነበር።  ይህ ግን ቁንጽላዊ ነው የሚሆነው፤ ቢሆን ግን ሁለት ነገሮችን ማንሳት ግድ ይላል። ሙሉ ስዕል ለማዬት ባልችልም በአገላለጹ ላይ ጋዜጠኛ ተምስገን ደስለኝ የአማራን ተጋድሎ እና የገዱን መንፈስ ውስጥነት ዕውቅና የመስጠት ዝንባሌው ለእኔ ድንገቴ ነበር።  እንደሚመስለኝ ያላባራው የአማራ መፈናቀል እና ማዕከላዊ መንግሥት የሰጠው ተባደግ አያያዝ ወደ ራሱ እንዲመለከት ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለነፍሱ ድንግልዬ መልዕክት እንደላከችለት አስባለሁኝ።  እኔንም ወደ አማራ ተጋድሎ ጥቅልል ብዬ እንድገባ ያደረገኝ የቪዥን ኢትዮጵያ የጉባኤ አመራር አሳታፊነት፤ እንዲሁም ሚዛናዊነት አድሏዊ አያያዝ ስነበረው ነው። አንዳንድ አጋጣሚዎች አትኩሮትን የሚስቡ ብቻ ሳይሆን ዘላቂ አቅም በመፍጠር ረገድም እጬጌዎች ናቸው። https://www.youtube.com/watch?v=_CNYkBGZseM&t=2s ደራሲና ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከአማራ...

የኢትዮ አፍሪካኒዝም ህሊና ፕ/ ማሞ ሙጭ አትዮጵያ መንፈስ ሰጥታናለች" ይላሉ ...

ምስል
„ኢትዮጵያ መንፈስ ሰጥታናለች! ለዓለምም የመንፈስ ጸጋ የሰጠች አገር ናት!“ አባቶቻችን አንተን ተማመኑ፤ ተማመኑ አንተም አዳንህቸው። (መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፳፩ ምዕራፍ ፬) ከሥርጉተ© ሥላሴ 2.07.2018 (ከገደማዊቷ ሲዊዘርላንድ።) ኢትዮጵያ ካሏት ዓራት ዓይናማ ሊሂቀ ሊሂቃን አንዱ ናቸው። ኢትዮጵያዊነት ብቻ ሳይሆን አፍሪካዊነት ከሚንገበግባቸው ጥቂት የምርምር ሊሂቀ ሊሂቃን ቤተኛም ናቸው። ችግሩ አለተጠቀምንብትም። ድህነታችን ማን ታቅፎ ይኑርልን? እኒህ እውቅ ኢትዮ አፍሪካዊ ሐዋሪያ እኛ ጥበባቸውና እና ዐውቀታዊ ክህሎታቸውን ባንጠቀምበትም ሌሎች ብልሆች ግን ከልጅነት እስከ ዕውቅት በአህጉራዊ እና በሉላዊ ጉዳዮች ላይ ሁለገብ ትውልዳዊ ድርሻቸውን ተወጥተዋል። በዕውቀታዊ ብቃታቸውም ተጽዕኖ ማሳረፍ የቻሉ ብርቅዬ ኢትዮጵያዊ ናቸው። ፕሮፌስር ማሞ ሙጬ በማናቸውም አገራዊ ሆነ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ተሳትፎ የሚያደርጉ፤ ያደረጉም ቅን ሊቀ ትጉሃን ናቸው። ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት ህሊናችን እና መንፈሳቸውን ግን ዕውቅና ከመስጠት በታዕቆቦ የቆዬ ቢሆንም፤ ታሪክ ግን ምንግዜም ሲያስባቸው የሚኗሩ ባለውለታችን ናቸው። የሆነ ሆኖ እኛ ባናውቅበትም አፍሪካውያን እንደ ልዩ ዓርማቸው የሚዮዋቸው፤ ልክ እንደ የቅኔው ልዑል ብላቴው ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን፤ እንደ የእግር ኳስ እስፖርት ልዑል አቶ ይድነቃቸው ተሰማ አፍካዊነትን አጉልቶ በማውጣት፤ ጉልበት እንዲያገኝ በማድረግ እረገድ ድርሳን የሆኑ የአፍሪካውያን የጸሎት መጸሐፍ ናቸው። እኒህ ታላቅ ኢትዮ አፍሪአካዊ የኢትዮጵያኒዝም ፍልስፍናንም በልዩ ክህሎት አቅሙ በልጽጎ፤ ጎልቶ እና ጎልበቶ እንዲታይ ሙሉ ጊዜያቸውን በመሰጠት ላይ ይገኛሉ። ትልቁ ጸጋቸው ዕውቀ...